2016-04-04 16:18:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ መኃሪነት ብርታትን ይጠይቃል


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤአ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. ሚያዝያ ሦስት ቀን 2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በዓለ መለኮታዊ ምኅረት አክብራ መዋሏ ሲገለጥ። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዚያኑ ዕለት በሮማ ሰዓት አቆጣጠ ከጠዋቱ 10 ሰዓት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ከውጭና ከውስጥ የመጡ ምእመናን ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ ሲሆን። ይኸንን በዓል ምክንያት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ስድስት ሰዓት የሚገፉትን ለተሳዶ አደጋ የተጋለጡትን ለዓለማዊነት አስተሳሰብ ምርኰኞች ስለ ሆኑት ክርስትያኖች በተለያየ ምክንያት ለዓመጽና ለብዝበዛ የተዳረጉት ስለ ተፈናቃዮችና ስደተኞች ዓመጽኞን ጥላቻ የሚዘሩትን የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ለሚረግጡ ሁሉ የእግዚአብሔር ምኅረት እንዲገለጥላቸውና ይደርሳቸውም ዘንድ መጸለዩ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትዊተር በተሰየመው የማኅበራዊ ግኑኝነት ድረ ገጽ ዘንድ ባለው አድራሻቸው አማካኝነትም፥ መኃሪ መሆን ማለት ተጨባጭና አድርግልኝ ላድርግልህ የማይለው የሚሰዋ ፍቅር ለመኖር መማር ብርታትን ይጠይቃል ማለት መሆኑ የሚገልጥ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ቀን ጀምረው መኃሪ መሆን ብርታት የሚጠይቅ መሆኑ ካለ መታከት በማስተማር የምኅረት ዓመት በማወጅ መኃሪ መሆን ማለት ደካማነት ሳይሆን ብርታት መሆኑና፡ መኃሪ ለመሆን የሚሻ ሁሉ ጽኑንና ልበ ብርቱ እንዲሆንና ያለው አስፈላጊነት በተለያየ ወቅት በሰጡት አስተምህሮ ያሰመሩበት ሃሳብ መሆኑ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው እግዚአብሔር መኃሪ ነው። መኃሪ መሆን ጽናትና ብርታት ይጠይቃል። በመማር በማፍቀርና የሰላም መሣሪያ በመሆን ሰላም አድርጎ ለመኖር ብርቱ መሆን እንደሚያስፈልግ በዴሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ማእከላዊት አፍሪቃ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ዑደት ባካሄዱበ ወቅት እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀ 2015 ዓ.ም. ለአገሪቱ ወጣቶች ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበትና ክፉ ላደረገንን መማር ይቻላልን የሚል ጥያቄ በማቅረብ። አዎ ይቻላል። በፍቅርና በመማር ብቻ ነው በእውነት አሸናፊ ለመሆን የሚቻለው። ፍቅር ፈጽሞ ተሸናፊ አያደርግም። በፍቅር ከፍቅር ስለ ፍቅር ስትኖሩ የምትኖሩት ሕይወት አሸናፊ ይሆናል ስለ ፍቅር ሕይወትን አሳልፎ ለመሰጠትም ያበረታታል፡ ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ለዚያች አገር ወጣቶች ለማመ ብርቱዎች ለማፍቅር ብርቱዎችና ሰላም ለማረጋገጥ ብርትዎች ሁኑ እንዳሉ በማስታወስ ገልጠዉታል።

በቤተሰብ ውስጥ የምኅረትና የማኃሪነት ብርታት መኖር

እ.ኤ.አ. ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የዕለተ ረቡዕ ትምህርተ ክርስቶስ በለገሱበት ዕለት አንዲት ቤተሰብ ወደ ፊት እንድትል የሚያደርጋት መኃሪነትን ስትኖር ነው፡ መኃሪነት ውጣ ውረድ የተሞላው ዕለታዊ ሕይወት በጽናት ተጋፍጦ ወደ ፊት ለማለት የሚይጋጥም መሥዋዕትነ ሁሉ በመወጣት ሳይሸነፈ ለመሆር ተማምሮ ዳግም ሕይወት ባዲስ መንፈስ ለመኖር የሚያበቃው ብርታትን ያሰጣል። መኃሪነትን ይቅርታ እባክህን የእኔ ወንድም የእኔ እህት እየተባለ በሚኖር ሕይወት የሚገለጥም መሆኑ በስፋት እንዳብራሩ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ጂሶቲ በማስከተል፥ በቤተሰብ ውስጥ በአባትና በእናት በወላጆችና በልጆች መካከል ፍቅር የሚያጸናው የምኅረት መንፈስ በተጨባጭ መኖር ነው እንዳሉ በማስታወስ ያመለክታልኡ።

ኃጢተኛ መሆንህ ለመታመንና ይቅርታን ለመጠይቅ ብርታት ያስፈልጋል

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንጻ በሚገኘው ቤተ ጸሎት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባስደመጡ ስብከት ኃጢአተኛ ነኝ ብሎ ለመታምንና ኃጢአተኛ መሆንህ ለማወቅ ብርታትን ይጠይቃል። እንዲህ ባለ ጉዞ ነው የእግዚብሔር መሃሪነት ልንነካ የሚቻለን። የእግዚአብሔር ምኅረት ዘወትር በሮቻችንን ያንኳኳል ሊጎበኝንም ይመጣል። እንዲገባና ምኅረቱን እንዲጸግወን በሩን የመክፈቱ ነጻነትና መልካም ፈቃድ ከእኛ ነው።

ኃጢአተኛ መሆን የማትታመን አልቦ ኃጢአት ነኝ የምትል ከሆንክ ገና ክጅምሩ ትሳሳታለህ። ልባችን እንዳይደነድን የእግዚአብሔር ጸጋ እንለምን። ልባችን ለምኅረቱ ክፍት እንዲሆን የታማኝነት ጸጋውን እንለምን፡ ደካሞች ስንሆን ምኅረትን እንለምን እንዳሉ ጂሶቲ ካጠቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.