2016-03-31 11:15:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በፓኪስታን በሚገኙ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰውን ጥቃት አወገዙ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው ዕለት ማለትም በመጋቢት 29.2016 ፖንቲፍክስ (@pontifex) በተሰኘው የቲውተር አድራሻቸው ባስተላለፉት መልዕክታቸው “የእግዚአብሔር አምላክ ሀይል ጥፋት ሳይሆን ፍቅር መሆኑን ኢየሱስ አስተምሮናል፣ የአምላክ ፍትሕ የበቀል ሳይሆን የምህረት ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ባለፈ እሁድ ማለትም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 27.2016 በተከበረው የፋሲካ በዓል ዕለት ላሆር በተባለ የፓኪስታን ግዛት ውስጥ በሕጻናት መጫወቻ ሥፍራ፣ ታሊባን በተባለ አሸባሪ ድርጅት በክርስቲያኖች ላይ የደረሰው እና  የብዙኋኑን ንጹሐን ሕፃናት እና ሴቶች ነብስ በቀጠፈው የሽብርተኞች ጥቃት በጣም ማዘናቸውን አበክረው የገለጹት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በፓኪስታን የሚገኙ በቁጥር አናሳ የሆኑ ክርስቲያኖች መንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንድያደርግላቸው አጋጣሚውን ተጠቅመው ጥሪ ማድርጋቸውና ጥላቻ ጥፋትን ብቻ ስለ ምያስከትል እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ልወገድ ይገባኋል ብለዋል።

በትላንትናው ምሽት የእዝህ የሽብር ጥቃት ሰለባ የሆኑ ስዎችን ለማሰብ ጥቃቱ በደረሰብት ሥፍራ በመቶ የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች እና ሙስሊሞች ያለምንም ፍራቻ ፀሎት እና የሻማ ማብራት ስነ-ስረዓት መፈጸማቸው እና አንድ አንድ የሙስሊም እምነት ተከታዮች ለክርስቲያን ወንድሞቻቸው ያላቸውን አጋርነት በወቅቱ ማሳየታቸው ታውቅኋል።

“ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ያስተላለፉት መልዕክት በጣም አጽናኝ እና አበረታች ነው” ያሉት በሮም የፓኪስታን ክርስቲያኖች ህብረት ፕሬዝደንት የሆኑት ፕሮፌሰር ሞቤን ሻሂድ “በላሆር በሕጻናት መጫወቻ ሥፍራ የደረሰውን ጥቃት በፍጥነት ቅዱስነታቸው ማውገዛቸው እና በእዝህ አስከፊ የሽብር ጥቃት ሰላባ የሆኑትን ሰዎች በጸሎታቸው ማሰባቸው አስፈላጊ እና ወቅታዊ ክንውን በመሆኑ የጥቃቱ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦች መጽናናትን የፈጠረ ድርጊት ነበር” በማለት ቅዱስነታቸውን አመስግነዋል።

በእዝህ የሽብር ጥቃት ነብሳቸውን ያጡ ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆኑ አንድ አንድ የሙስሊም እምነት ተከታዮችም የጥቃቱ ሰላባ መሆናቸውን ያስታወሱት  በሮም የፓኪስታን ክርስቲያኖች ህብረት ፕሬዝደንት የሆኑት ፕሮፌሰር ሞቤን ሻሂድ፣ ምንም እንኳን ጥቃቱ ክርስቲያኖችን ብቻ ትኩረት አድርጎ የነበረ ቢሆንም፣ ሌሎችም የሕብረተሰብ ክፍሎች የጥቃቱ ሰላባ መሆናቸው የሚያሳየው ጥቃቱ በክርስቲያኖች ላይ  የተቃጣ ጥቃት ብቻ ሳይሆን በመላው የፓኪስታን ማሕበረሰብ ላይ መሆኑንም እንደ ምያሳይ አበክረው ገልጸዋል።

በተጨማሪም “ይህ የደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት አፍጋኒስታን በኮምኒስት ሩሲያ በተወረረችበት ወቅት ይህንን ወረራ ለመቃወም ሲባል በተቀረጸው እና ይሰጥ በነበረው የአክራሪነት ትምሕረት ነጸብራቅ ወይም ወጤት ነው ያሉት ፕሮፌሰር ሞቤን ሻሂድ ይህ ዓይነቱ የአሸባሪዎች ድርጊት መደገም እንደ ሌለበትም አሳስበኋል።

“ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ለጥቃቱ ምላሽ መሆን ያለበት በቀል ሳይሆን ይቅርታ መሆን ይገባኋል ማለታቸውን እርሶ እንዴት ይመለከቱታል?” ተብለው ከጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ  ፕሮፌሰር ሞቤን ሻሂድ ስመልሱ “እኛ ክርስቲያን እንደ መሆናችን እና በተለይም ደግሞ አሁን ያለነው በቅዱስ ልዩ የምሕረት ኢዩበሊዩ ወቅት እንደ መገኘታችን ክርስቶስ ለኛ ያሳየንን ምሕረት ዋቢ በማድረግ በታላቅ እምነት ተደግፈን ይቅርታን ማድርገ ይኖርብናል “ ብለው “ ነገር ግን መረሳት የሌለበት ጉዳይ 31 ልጆቻቸውን እና 8 ሴት እህቶቻቸውን በአጠቃላይ ልጆቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውን፣ እህቶቻቸውን፣ እናቶቻቸውን እና እንዲሁም አባቶቻቸውን በጥቃቱ ያጡ ቤተሰቦች በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ በመሆናቸው ይቅርታን እንድያደርጉ ከተፈለገ የተወሰን ጊዜ ልሰጣቸው ያስፈልጋል” ብለኋል።

የፓኪስታን ፕሬዝዳንት ናዋዝ ሻሪፍ በትላንትና ዕለት ይህንን የአሸባሪዎች ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ ማውገዛቸው የታወቀ ስሆን በተለይም “የነቢዩ መሀመድን ስም ይምያጎድፍ በሞት ይቀጣል የሚለው የፓኪስታን ሕግ” በቁጥር አነስተኛ የሆኑትን ክርስቲያኖች ለማጥቂያ እየዋለ በመሆኑን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰባቸው እና በተጨማሪም  ደረጃ በቁጥር አናሳ የሆኑ የተለያዩ የምህበርሰብ ክፍሎችን የምከላከል ተቁዋም በፌዴራል ድረጃ ማቋቋማቸው በክርስቲያኖች ዘንድ በመልካም የተወሰደ መሆኑን ያገለጹት ፕሮፌሰር ሞቤን ሻሂድ “በእግዚአብሔር እና በነቢዩ ሙሀመድ ስም የምፈጸመውን ሕገ ወጥነትን በፍጹም አንቀበልም” የሚለውን የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስተር አባባልንም ከእዝህ በፊት የነበሩ ባለስልጣኖች በይፋ ያልተናገሩት መግለጫ እና ያልተለመደ በመሆኑ መንግሥት ለጉዳይ ትኩረት መስጠቱን ያሳያል ብለኋል።

በመጨረሻም “ክርስቲያን እንደ መሆኔ መጠን ሁሉም በእዝህ አስደንጋጭ የአሸባሪዎች ጥቃት ነብሳቸውን ላጡ ሰዎች እንድንጸልይ አደራ እላለው “ ብለው “ በእዝህ አደጋ ነብሳቸውን ያጡት ሰዎች ለእምነታቸው የተሰው ሰማዕታት መሆናቸውን ገልጸው ሁሉም በአንድነት በፀሎት አንድያስቡኋቸው ጥሪ በማድረግ ንግግራቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.