2016-03-30 15:19:00

በብራሰልስ ባሸባሪያን ጥቃት ሰለባ ለሆኑት የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ጸሎት


በብራሰልስ እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. አሸባሪያን በጣሉት አሰቃቂው አደጋ የሞት ቀላልና ከባድ የመቁሰል አደጋ የተጋለጡትን ሁሉ ለማሰብ  የተለያዩ ሁሉም ሃይማኖቶች  “እግዚአብሔርን የሚያፈቅር ወንድሙን ያፈቅራል። ክርስቶስ እኵይ መንፈስን አሸንፏል። አመጽ ላይ ድል ነስተዋል። ድሉም ክፋን በግብረ ክፋት አመጽን በግብረ አመጽ ማካኝንት አይደለም፡ በእግዚአብሔር ስም የሚፈጸም ማንኛውም ዓይነት ዓመጽ ቅቡል ሊሆን አይችልም፡ እግዝአብሔ ለገዛ እራስና በማንም ለእራስ ጥቅም መሣሪያ ማድረግ አይቻልም”  የሚል እግዚአብሔር ፍቅር ነው የሚሻውም ፍቅር በልጆቹ መካከል እንዲረጋግጥም የሚመኝ መሆኑ የሚመሰክር በጋራ ጸሎትና ጽሞና ባካተተ መርሃ ግብር እ.ኤ.አ. መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ምላሽ የሰጡ ሲሆን፥ በተካሄደው የጋራ የጸሎት መርሐ ግብር የተሳተፉት የማሊነስና ብራልሰልስ ሊቀ ጳጳት ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ደከስል ባስደምጡት ቃል ያሰመሩበት ሃሳብ መሆኑ ሲር የዚና አገልግሎት ሲያመለክት፡ በዚህ በቅዱስ ሚከለና ጉዱላ ካቴድራል በተካሄደው የጸሎት ሥነ ስርዓ ያነቃቃው በበልጂም የሚገኙት የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት መሆኑ ገልጦ በብራሰልስ የፕሮተስታንት አቢያተ ክርስቲያን ሲኖዳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር መጋቤ ስተቨን ፉይተ። በበልጂም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሜጥሮፖሊታ አተናጎራስ የወንጌላውያን አቢያተ ክርስቲያን ፈደራላዊ ሲኖዶስ ሊቀ መንበር መጋቤ ጊርት ሎራይን እንዲሁም በበልጂም የአንግሊካውያን አቢያተ ክርስትያን አምልኮ ተንከባካቢ ኮሚቴ ሊቀ መንበር ቄስ ጃክ ማኮናልድ፡ በኅብረት ኤውሮጳ የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኣላይን ፓውል ለበኡፒን እንዲሁም በበልጂምና ሉሰበምበር ለቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጃቺንቶ በርቶሎኮ፡ የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ማኅበረሰብ በመወከል በበልጂም የቤተ እስራኤላ ጉባኤ ሊቀ መንበር ፊሊፐ ማርካይዊችና የቤልጂም የምስልምና ሃይማኖት ተከታይ ማኅበረሰብ በመወከል የሙስሊሞች በበልጂም ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሳላሕ ኢቻልዊ መሳተፋቸው የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አያይዞ፥ በተካሄደው የጸሎትና የጽሞና ሥነ ስርዓት ብፁዕ አቡነ ደ ከሰል የጣለው ጥቃት ጸረ ሰብአዊ ጸረ የቤልጂም ኅብረተሰብ መሠረት የሆነውን ነጻነት እኩልነት የባህል የሃይማኖት ልዩነት አክብሮትና ትብብር የሚለውን እሴት የሚቃወም ነው፡ ሰላም ሲባል የዓመጽ አለ መኖር ሁነት ሳይሆን፡ መቻቻል ከሚለው እሴት ሰገር ነው፡ ይኽ ሲባል እውነተኛው የጋራ አብሮ መኖር ሁኔታ ከሌለ ሌላውን ካንተ የተለየውን ቅነኛ አክብሮት የማይሰጥ ከሆነ ሰላም ሊኖር አይችልም። ይኽ መከባበር ለማንኛውም ዓይነት ፍቅር መሰረት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን አፈቅራለሁ ወንድሜን ጎረቤቴን ግን እጠላለሁ ማለት አይቻልም። ግብረ ሽበራውን የጣሉት በበልጂም ኅብረተሰብ ውስጥ መከፋፈልን አንዱ በሌላው ላይ እንዲነሳ የሚያነቃቃ ሰላማዊ ያብሮ መኖር ጥሪ የሚያናጋ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው፡ በመሆኑም አደራ በጽናት ይኸንን ፈተና መቋቋም ይኖርብናል እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ለአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች ድምጽ በመሆን በጸሎቱ መርሐ ግብር በመሳተፍ ንግግር ያስደመጡ አንዲት እናት በበኩላቸውም፥ ሁላችን የአንድ ቤተሰብ አባላት ነን በማለት በዚህ አጋጣሚምው በአውሽዊዝ የተፈጸመውን አሰቃቂው እልቂት የሚያወሳ ታሪካዊ ገጠመኞችን ጠቅሰው፡ ጥላቻ ዓመጽ ወደ ጭለማ ይመራል። ፍቅርና መከባበር ወደ ብርሃንና ሕይወት ይመራል ሲሉ የሙስሊም ሃይማኖት ተከታዮችን ወክለው ቃላችውን ያስደምጡት አንዲት እናትም ከደማው ልቤ አደራ ተስፋ አንቁረጥ ኣላችኋለሁ። ተስፋ በማስቀደም ባንድነት ወደ ፊት እንጓዝ ብለው ወንድም ፒየር “ሁሉም ተስፋ ቢቆርጥም ማመኔን ታንግቤ ወደ ፊት እላለሁ። ሌሎች ጥላቻ ቢዘሩም ማፍቅሬን አላቋርጥም። ሌሎች ለማውደም ቢራወጡም ጦርነት ባለበት ክልልም ይሁን ሰላም ከመገንባት ወደ ኋላ አልልም፡ ሁሉም ዝምታ ቢመርጥም ስለ ፍቅር የሚጮህ ድምጽ መሆን አላቋርጥም ” የሚለውን ጸሎት ደግመው ያስደመጡት ቃል ማጠቃለላቸው የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ የተካሄደው የጸሎት ሥነ ስርዓትም የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ፥ ጌታ ሆይ የሰላም መሣሪያ አድርገኝ የሚለውን ጸሎት በመድገም ሁሉም የሞት አደጋ ስላጋጠማቸው ባሳረጉት የህሊና ጸሎት መጠናቀቁ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.