2016-03-28 15:05:00

ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ፥ የሚታየው የክፋት መንፈስ መልካም የሆነው ነገር ሁሉ አያጠፋም


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጀኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በበዓለ ፋሲካ ምክንያት እ.ኤ.አ. ወደ እሁድ መጋቢት 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በሚያሸጋግረው ቅዳሜ ሌሊት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፥ የትሁታን የተራውና ቅን ሰዎች የዋሆች የቤተሰቦች በታማኝነትና በጽናት መስዋዕትነት የተካነ በዕለታዊ ሕይወት የሚኖሩት መልካም የሆነውን ሁሉ ለማውደም የሚቃጣው የክፋት መንፈስ በብዛት እየታየ ነው። እንዲህ ባለ ሁኔታ እየተኖረ ባለበት በአሁኑ ወቅት የሰማዕታት ስለ እምነታቸው የተገድሉት ክርስቲያን፡ የከፈሉት የሰማዕትነት አብነት እንከተል። ሰማዕትነት የክርስቶስ ከሞት መነሳት ምስክርነት ነው፡ ክርስቶስ የሚመጣው ሕይወትና ዓለም ቀዳሚ ነው፡ እርሱ በታሪክ የሚያብብ እውነት ነው፡ ከሞት ማዶ ትንሣኤና አዲስ ሕይወት አለ ብሎናል በቃልና ከሞት በመነሣትም አረጋግጦልናል።

በዙሪያችን በዓለም ዙሪያ ሁሉ የሚከሰተውን  ግብረ እከይ፡ እየተስፋፋ ያለው አሸባሪነትና ያሸባርያን ድርጊት ስናይ አመጽና ለያይ ግንብ መስፋፋ የመሳሰሉት ጸረ ሰብአውያን ተባሮች ሁሉ ስናይ የባዶነት ባህል እየተስፋፋ መሆኑ እናስተውላለን። ሆኖም በሞት ላይ ድል የነሣው የክርስቶስ ዜጎች ነንና ያንን ጸረ ሞት የሆነው ባህል ባለ ድል እንደማይሆን እናስተውላለን። ሁሉን ነገር የሚለውጠው የሚያድሰው ክፋት ሳይሆን ፍቅር ነው። ፍቅር ደግሞም ገዛ እራስ ኣሳልፎ መስጠት የሚል ስለ ሌላው የሚሰጥ ሕይወት ላይ የጸና ነው። ይኸንን እውነት ክርስቶስ መስክሮታል። አመጽ ስቃይ ግብረ ሽበራ ባጠቃላይ የሞት ባህል በኢየሱ ክርስቶስ ተሸንፏል። የሕይወት ድል አድራጊነት የምንመሰክረውም መልካም የሆነው ነገር ሁሉ በመምረጥና ዕለት በዕለት የሕይወት ባህል በማስፋፋትና በመኖር ነው፡

ኤውሮጳና ዓለማችን እያናጋ ያለው ዘርፈ ብዙ ችግርና ግብረ ሽበራ የሚወገደው በፍትሕና በሕግ ነው፡ ትንሣሴ በሞት ላይ የተሰጠ ምላሽ ነው፡ አለ ፍትሕና ሕግ የሚፈለግ ሥርዓት መሰረት የሌለው ሊረጋገጥም አይችልምም፡ ለተወሰነ ጊዜ ሊቆይ ይችል ይሆናል ነገር ግን ዘላቂነት አይኖረውም። ክርስቶ የሰጠው ሕይወት እውነተኛ ሕይወት ነው፡ የተሰጠን ዘለዓለማዊ ሕይወት ዕለት በዕለት የሚያጋጥመንን ተናንሽ መቃብሮች ፈተናዎች ሁሉ በማሸነፍ በዕለታዊ ሕይወት መኖር ይገባና፡ ያንን የሚጠብቀን የፍጻሜው ትንሣኤ ከወዱሁ ተገልጦልናል በዕለታዊ ሕይወት ከወዲሁ ልንመሰክረው ይገባናል፡ የሞት ባህል ፈጽሞ በሕይወት ባህል ላይ ድል አይነሳም። ይኸንን እውነት አደራ እንመስክር እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.