2016-03-28 15:00:00

ብፁዕ ኣቡነ ሳንቶሮ፥ ለሞት አሳልፎ የማይሰጥ እግዚኣብሔር


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የማኅበራዊ የሥራ የፍትህና ሰላም ጉዳይ የሚከታተለው ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ፊሊፖ ሳንቶሮ በበዓለ ፋሲካ ምክንያት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ በቅርቡ በብራሰልስ አሸባሪያን የጣሉት ግብረ ሽበራ በማሰብ በኤውሮጳ ምንም’ኳ ያንን ኤውሮጳ ያጸናው እውነተኛው ፍትህ ሰብኣዊ ሰላም የተሰኙት እሴቶች ላደጋ የሚያጋልጥ አሸባሪያን የጣሉት ጥቃትና በቀጣይነት የሚሰነዝሩት ዛቻ ቢታይና ያለ ቢሆንም ቅሉ ተስፋን አያጨልምም ብለዋል።

የ2016 ዓ.ም. በዓለ ፋሲካ በዓለማችን በተለያዩ ክልሎች በሚታዩትና በተጣሉት ግብረ ሽበራ ብዙ ሕዝቦች ያስቆጣ ለሐዘን የዳረገ ግጭትና ጥቃት ባጠቃላይ አለ መረጋጋት ፍርሃት ተስፋ መቁረጥ የመሳሰሉት ስሜቶች የሚያስፋፋና ጥርስ በጥርስ ዓይነት በዓይን ለሚለው ባህል የሚገፋፋ ሁነት የሚታይ ቢሆንም ቅሉ በእምነት የተደገፈ ተስፋ አማካኝነት ሰላም መረጋጋት ለሚነሱ ተግባሮች ሁሉ እጅ ባለ መስጠት ሰላም መቀራረብ በማነቃቃት በጋራ ወደፊት ማለቱ ግድ ነው፡ በእነዚህ ቀናት በላቲን ሥርዓት በተገባው በዓለ ፋሲካ ምክንያት የሚከበረው የሚቀበርው ሊጡርጊያዊ ሥርዓት ሁሉ ተስፋ የሚያነቃቃና ኅያው የሚያደርግ ነው ብለዋል።

እንደ ቅድስት ድንግል ማርያም በልጅዋ መስቀል ሥር ሆና የኖረቸው ስቃይ ብዙ እናቶች ቤተሰቦች የተለያዩ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ሰብአዊ እሾኻማ ሁነት ሥር ሆነው ስቃያቸውን ከጌታ ስቃይ ጋር አጣምረው የሚኖሩ እሉ። በሕማማት ሳምንት የጌታን ስቃይ እስተንትነናል ስቃይ በማስተንተኑ ሁነት አልቀረንም ጌታ ተስተዋል። መነሣቱንም ታምነን ትንሣኤን አክብረናል።

በበልጂም በፈረንሳይ በአፍሪካ ክልል አገሮች በእስያ በቅርቡ በየመን የተገደሉት የእናቴ ብፅእት ተረዛ ደናግል ሌሎችም ስቃይ ቅድስት ድንግል ማርያም በስቃይዋ በተስፋ በመስቅል ሥር አኑራዋለች። ከስቃይ ሁሉም እንደምንነሳሣ ጌታ አረጋግጦልናል፡ ተስፋችን በመቃብር የሚዘጋ ሳይሆን ትናሣኤ ነው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የቅርበት የመቀራረብ የመተባበር ባጠቃላይ ለሕዝብ ቅርብ የመሆን መንገድ እያመለከቱ ለድኾች ለተናቁት እንዲሁም የሁላችን መኖሪያ የሆነውን ተፈጥሮ መንከባከብ ያለው አስፈላጊነት በእምነትና በቲዮሎጊያው ሥር ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ሰብኣዊነት ማእከል በማድረግ ለሁላችን ልንከተለው የሚገባንን መንገድ እያሳዩ ናቸው። የክርቶስ ስቃይ ባክኖ አልቀረም። ከክርስቶና ከማርያም ሕይወት ጉዞአችንን አንድ ብለን በታደሰ መንፈስ ለመጀመር የሚያበቃን ኃይል ሁሉ እናገኛለን። በኤውሮጳና ከኤውሮጳ ውጭ የተጣሉት የሽበራ ጥቃቶች ሁሉ ለዘረኝንነት ለእርስ በእርስ መፈራራት ለመሳሰሉት ጸረ ሰብአውያን ምርጫዎች ሊዳርጉን አይገባም። ሆኖም ሌላውን የማስተናግድ ሰብአዊ ተግባር ጭምት መሆን አለበት። በኤውሮጳ ላሸባሪያኑ ኃይል የሆነው የኤውሮጳ በመሠረታዊ ባህልዋ እሴቶች መዳከም ምክንያት ነው፡ እግዜአብሔርን የሚዘነጋ የሚረሳ መኖሩንም ግድ የማይሰጠው በመስፋፋት ላይ ያለው ባህል ለአሸባሪያን ኃይል ነው፡ ለዚህም ነው ኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ዳግማዊ አስፍሆተ ወንጌል በሚል ውሳኔ ሥር የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በማረማመድ ላይ የምትገኘው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋ።








All the contents on this site are copyrighted ©.