2016-03-26 11:30:00

በህማማት ሳምንት "ኢየሱስ እስከ መሰቀል ያደረስውን ፍቅር በጸጥታ የምናስብበት ወቅት ልሆን ይገባል" ።


እንደ አወሮፓዊያን የዘመን አቆጣጠር እና በላቲን የስርዓተ ሉጥርጊያ ስነ-ስርዓት እና ደምብ መሰረት ከመጋቢት 24-27.2016 ያለው ጊዜ በእንግልዘኛው ቋንቋ Triduum የምባል ስሆን መጠሪያውንም ያገኘው ከፋሲካ በዓል በፊት በምገኙት 3 ቀናት ውስጥ ማለትም ሐሙስ፣ ዓርብ እና ቅድሜ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጆችን ለማዳን ብሎ መስቃየቱን፣ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶቱን፣ መቀበሩን እና ከሙታን በመነሳቱን ለሰው ልጆች ሁሉ መዳንን እንዳመጣላቸው እና ከእግዚኣብሔር ጋር እንዲታረቁ ያደረገበትን ታልቅ የፍቅር ሚስጢር የምናስብበት ወቅት በመሆኑ ነው።

በእዚህ የኢየሱስን ስቃይ፣ ሞት እና ትንሳኤ በምናስብበት 3 ቀን በላቲን ስረዓት ሉጥርጊያ እና ደንብ መሰረት የምጀምረው ኢየሱስ ክርስቶስ የሐዋሪያቱን እግር ባጠበበት ወቅት “እኔ እንዳደረግሁላችሁ እናንተም እንዲሁ እንድታደርጉ ምሳሌ ትቼላችኋለው” ባለው መሰረተ እና በእዝያኑ ዕለትም ቅዱስ ቁርባንን መመስረቱ እና ለሐዋሪያቱ፣ ሐጥያትን ማሰር እና መፍታት የምያስችላቸውን የክህነት ሚስጢርን ያስረከበትን ዕለት በምንዘክርበት ፀሎተ ሐሙስ በሚከናወነው ስርዓት ቅዳሴ ይሆናል።

በዚህም ስርዓተ ቅድሴ ላይ “ክብር ላምላክ በስማይ ለሚኖር” ተብሎ በምዘመረው ወይም ከምደገመው ውዳሴ ቡኋል  የቤተ ክርስቲያን ደወሎች እና የሙዝቃ መሳሪያዎች ሁሉ እስከ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ ወይም በቅዳሜ ማታ በሚከናወነው እና የኢየሱስን ትንሳኤ በምያበስረው ስርዓተ ቅዳሴ ላይ “ክብር ለአምላክ በሰማይ ለሚኖር. . .” ተብሎ እስከ ምዘመረው ወይም እስከ ምደገመው ጸሎት ድረስ ሳይደወሉ በጸጥታ ብቻ የጌታችንን ስቃይ በማሰላሰል የምናሳልፍበት ወቅት ነው።

በእነዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስቃይ፣ ሞቶ መቀበሩን እና ከሙታን መነሳቱን በምናስበበት 3 ቀናት ውስጥ መከናወን የምገባቸው ተግባራት የሚጀምሩት በፀሎተ ሐሙስ ይሆናል።  

ቤተ ክርስቲያን በፀሎተ ሐሙስ የምታከናውናቸው መንፈሳዊ ተግባራት የሚከተሉት ይሆናሉ።

< > እራት መታሰብያ የሆነው ስርዓት ቅድሴ በታላቅ መንፈሳዊነት ይከናወናል። በዚህ ስርዓተ ቅድሴ ወቅት የምከናወኑ አበይት መንፈሳዊ ተግባራት መካከል የምከትሉት ይገኛሉ < > ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋሪያቱ ያለውን ጥልቅ፣ የማያልቅ እና የማይለካ ፍቅሩን የገለጸበት እና ኢየሱስ የእኛ አዳኝ ብቻ ለመሆን ሳይሆን የመጣው እራሱን አሳልፎ እስከ መስጠት ድረስ፣ እራሱን ዝቅ በማድርገ ያሳየንን ትህትና የምንዘከርበት “እኔ እንዳደርኩላችሁ እናንተም እንድሁ አድርጉ” ብሎ ባዘዘን መሰረት የትህትና እና የፍቅር መግለጫ የሆነው የእግር ማጠብ ስነ ስርዓት ይከናወናል።< > ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረተው ቅዱስ ቁራባን በጥልቀት ይታወሳል፣ ይከበራል ይሰግድለታልም።< > ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋሪያቱ የሰጠው የሚስጢረ ክህነት ስልጣን በእዚሁ ዕለት ይታወሳል፣ ካህናት የሀገር ስብከታቸው ጳጳስ በተገኘበት የክህነት መኋላቸውን ያድሳሉ።< > ጳጳሳት በስርዓት ቅድሴ ወቅት ለሚስጢረ ጥምቀት፣ ቀንዲል እና ክህነት ሚስጢራት መፈጸምያ የምሆን ቅባ ቅዱስ ይባርካሉ።< > ቅዳሴ ከተጠናቀቀ ቡኋልም የአዲስ ኪዳን ታቦታችን የሆነው እና ጌታችን ኢየሱስ “ይህንን ለእኔ መታሰብያ አድርጉ” ብሎ ባዘዘን መሠረት ዘወትር በስርዓተ ቅድሴ የምንዘክረው እና የሕወታችን ምንጭ የሆነው ቅዱስ ቁርባን፣ ከማደርያው ይወጣና በሌላ ቦታ ወደ ተዘጋጀለት ስፍራ በክብር የወሰዳል በእዚያም ቦታ በፀጥታ የመለካል።< > ቁርባን ማደሪያ የነበረው ስፍራ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መሞትን እና 3 ቀን በመቃብር መቆየቱን ለመዘከር ለ3 ቀን ባዶ እና ክፍት ሆኖ ይቆያል።< > ዓርብ ወይም የጌታች የኢየሱስን መሰቀል እና መሞቱን በምናስብበት ወቅት ቤተ ክርስቲያን የምታከናውናቸው መንፍስዊ ተግባርት በጥቅሉ እንደ ምከተለው ይሆናል።< > በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚገኙ መስቀሎች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቃብር ውስጥ መሆኑን ለመዘከር እና ለማሰብ በጨርቅ ይሸፈናሉ።  < > ኢየሱስ ክርስቶስ ያለፋቸውን የስቃይ መንገዶች ለማስታወስ፣ የመስቀል መንገድ ጸሎት በታልቅ መንፈስዊነት ይከናወናል።< > ዓርብ ዕለት ስርዓት ቅድሴ አይከናወንም ነገር ግን ከመስቀል መገድ ቡኋላ በፀሎተ ሐሙስ ማታ በተደረገው ስርዓተ ቅድሴ የተባረከው ቅዱስ ቁርባን ብቁ ለሆኑ ምዕመናን ይሰጣል።< > በታልቅ መንፈስዊ አስተንትኖ እና ፀጥታ ይፈጸማል።< > ቅድሜ ወይም በግዕዙ ቀዳም ሱር በቤተ ክርስቲያን የምከናወኑ መንፈስዊ ተጋብራት በጥቅሉ እንደ ምከተለው ይሆናል።< > ክርስቶስ በመቃብር ወስጥ በመሆኑ በታላቅ ጸታ ዕለቱ ይታለፋል።< > ተንሳኤ የምያበስር እና በቅዳሜ ማታ ከምከናወነው ስርዓት ቅድሴ ውጭ ሌላ ስርዓተ ቅዳሴ በዕለቱ አይከናውንም።< > ቅዱስ እና ከሌሎችም መንፈስዊ መጽሓፍት የተውጣጡ መንፈሳዊ ምንባባት ይነበባሉ።< > መንፈስዊ ዝግጅት ለትንሳሄ በዓል ይደርጋል በእዚህም ዕለቱ ይጠናቀቃል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በእነዚህ ከፋሲካ በዓል በፊት በሚደረጉ ሦስት የዝግጅት ቀኖች ውስጥ ምዕመናን የኢየሱስን ትንሳኤ በምገባ እና ክርስቲያናዊ በሆነ መልኩ ለማክበር የሚከተሉትን ተግባራት መፈጸም ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በእነዚህ ሦስት ቀናት ውስጥ ኢየሱስ ለሕዝቡ ያለውን ከፍተኛ ፍቅር እና ምህረት አድራጊነቱን በስቃዩ፣ በመሰቀል ላይ ተስቅሎ በመሞቱ ያሳየበት ወቅት በመሆኑ፣ ለእነዚህ ሦስት ቀናት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተን ኢየሱስ ያሳየንን ፍቅር እን ምህረት በታላቅ እምነት እና በጸጥታ ማሰብ ይጠበቅብናል ብለኋል።

በተጨማሪም በእነዝህ ሦስት ቀናት የኢየሱስ የምድራዊ ሕይወቱ ማጠቃለያም ናቸው። ቅዱስነታቸው በተጨማሪም እነዚህን ሦስት ቅዱስ እና የምሕረት ቀናት፣ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ስላላቸው አስፈላጊ መሆናቸውን አበክረው ገልጸዋል።   

በዕለተ ረቡዕ ማለትም በመጋቢት 23.2016 ለጠቅላል አስተምሮ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ከ30ሺ በላይ ለምሆኑ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን እነዚህ 3 ቀናት  በአጠቃላይ ኢየሱስ ለእኛ ያለውን ፍቅር የገለጸበት ቀናት ናቸው ብለዋል።

ሐሙስ ዕለት ጥዋት ማለትም በመጋቢት 24. 2016 ቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ፣ ኢየሱስ የሐዋርያቱን እግር ያጠበበትን፣ ቅዱስ ቁርባንን የመሠረተበትን እና እንዲሁም የክነትን ሚስጢር ለሐዋሪያቱ ያወረሰበትን የጸሎተ ሐሙስ በዓልን  ለመዘከር በተዘጋጀው ስርዓት ቅድሴ ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ካህናት እና የተውሰኑ ምዕመናን በተገኙበት ማከናወናቸው ተገለጸ።

በእዝሁ ዕለት ቅዱስነታቸው ለሚስጢረ ጥምቀት፣ ለሚስጢረ ክህነት እና ለሚስጢረ ቀንዲል የምያገለግል ቅዱስ ቅባት መባረካቸው የተገለጸ ስሆን፣ ዕለቱም ክርስቶስ የክህነትን ሚስጢር የመሠረተበት በመሆኑም፣ ይህንንም ታላቅ ሚስጢር ለመዘከር በስርዓት ቅድሴው ላይ የተገኙ ካህናት ሁሉ “ለክህነት አገልግሎት” የገቡትን ቃል ማደሳቸውም በተጨማሪም ተገልጽኋል።

ቅዱስ አባታችን በስበከተ ወንጌላቸው ላይ “ እኛ ካህናት የተትረፈረፈውን የእግዚአብሔር ምሕረት ለዓለም ለመምሰከር በመጠራታችን፣ ይህንን አስደሳች እና አጽናኝ የሆነውን አገልግሎት ልክ ኢየሱስ እንዳስተማረን ከምሕረት ጋር በማዋሀድ ለምዕመናን መንፈስዊ አገልግሎት ማበርከት ይጠበቅብናል” ብለኋል።

ቅዱስ አባታችን በእግዚአብሔር ምሕረት ላይ ትኩረት ባደርገው ስብከታቸው በተለይም ደግሞ ኢየሱስ ያሳያቸውን ሁለት አበይት የምሕረት ተግባራትን በመግለጽ እንዳስገነዘቡት፣ እኛም ኢየሱስ ባስተማረን መልኩ ያለምንም ገደብ ምሕረትን ማድረግ ዕለታዊ ተጋብራችን ልሆን ያስፈልጋል” በለኋል።

ቅዱስነታቸው ኢየሱስ አሳይቶቸኋል ያሉትን ሁለት አበይት የምሕረት ተግባራትን ስያብራሩም “እኛ ምንም እንኳን የምገባን ባንሆንም፣ የእግዚአብሔር ክብር እና ፀጋ በከፍተኛ ሁኔታ የምጎለን ሁነን ሳለን፣ እግዚአብሔር ግን በደላችንን በመሻር እና ይቅርታን በማድረግ እኛን ለመገናኘት ወዶ አንደኛ ልጁን ወደ ምድር መላኩ የምያሳየው ምንም እንኳን በደለኞች ብንሆንም እኛን ለመገናኘት መምጣቱ በእራሱ የምያስየው በምሕረቱ እንደጎበኘን ዋስትና የምሆነን ጉዳይ በመሆኑ በቀዳሚነት ልገለጽ የሚገባው እግዚአብሔር ለእኛ ያሳየን ምሕረት ነው” ብለኋል ቅዱስ አባታችን።

“በሁለተኛ ደርጃ ልጠቀስ የምገባው እና እግዚአብሔር ለእኛ ያሳየው ምሕረት” አሉ ቅዱስነታቸው “እግዚኣብሔር እኛን ከተገናኘ እና በልጁ መሞት እኛን ካዳነን ቡኋላ የምመጣው ‘ምሕረት’ መሆኑን ገልጸው “እግዚአብሔር ምሕረትን ብቻ ሳይሆን የምያደርግልን ሐጥያትን በምንፈጽምበት ወቅት ያጣነውን የልጅነት መንፈስ እና ክብር መልሰን እንድናገኝም ጭምር ስለምያግዘን ለእዚህ ገደብ የለሽ የእግዚአብሔር ምሕረት መስጠት የምገባን ምላሽ መሆን ያለበት በምያስከብር ኀፍረት እና በአሳፍሪ ክብር መካከል ያለውን ውጥረት በመጠበቅ ልሆን ይገባል” ብለኋል ቅዱስ አባታች።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት “በእዚህ ልዩ የምሕረት ዓመት ኢዩበሊዩ አባታችን ለሆነው እግዚአብሔር ከልብ ከመነጨ ‘ምሕረቱ ዘውትር ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ’ መለመን እና መማጸን እንደ ምያስፈልግ ገልጸው ‘ያጣነውን የልጅነት ክብር’ እራሱን ዝቅ በማድርገ ለእኛ ስል በቆሰልው በኢየሱስ ክርስቶስ መልሰን እንድናገኝ ይረዳን ዘንድም መማጸን እና በርትተን መጸልይ ይገባናል” በልኋል።

በጨረሻም ቅዱሰ አባትችን “ ኢየሱስን ከሐጥያታችን ሁሉ ያነጻን ዘንድ እና ከማንኛውም ክፉ ነገሮች ይሰውረን ዘንድ እጸልያለው” ብለው “በመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ታግዘን የእግዚአብሔርን ምሕረት ለሁሉም ማዳረስ እንድንችል እና እንዝህንም መልካም ተግባራት በምንፈጽምበት ወቅት ሁሉ ተግባራችን በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት እንዲፈጸም እና ለእግዚአብሔር ሕዝብ መልካም እና የጋራ ጥቅምን ያጎናጽፍ ዘንድ እግዚአብሔር እንዲረዳን እጸልያለው” በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቀዋል።  

በተመሳስይ ዕለት ማለትም በመጋቢት 24.2016 አመሻሽ ላይ ፣ ኢየሱስ ከአስራሁለቱ ሐዋሪያት ጋር የመጨረሻ እራቱ ከመብላቱ በፊት የአስራ ሁለት ሐውሪያት እግር ያጠበበትን ምሽት ለማስታወስ፣ ከሮም ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በምትገኘው ካስተልኑዎቮ ዲ ፖርቶ በትሰኘው ከ25 የተለያዩ ሀገራት ለተውጣጡ ስምንት መቶ ዘጠና ሁለት ስደተኞች ግዚያዊ የመጠሊያ አገልግሎት በምሰጠው ማዕከል ቅዱስ አባታችን በመገኘት የአስራ ሁለት ስደተኞች የእግር ማጠብ ስነ-ስርዓት ማከናወናቸው ታውቁኋል።

ቅዱስነታቸው ለእነዚህ ከተለያዩ ሀገራት ለተውጣጡ ክርስቲያኖች፣ ሙስሊሞች እንዲሁም የህንዱ እመንት ተከታዮች የስነ-ስረዓቱ አካል በሆነው ስብከታቸው አንደ ገልጹት፣  “ለስደተኞች ፍልሰት መባባስ ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክተዋል” ያሉኋቸውን “የጦር መሳሪያ አምራቾችን እና አክፋፋዮችን” በድጋሚ ያወገዙ ስሆን፣ “ደም ለማፍሰስ የሚያገለግለውን መሳሪያ፣ ትርፍ ገንዘብ ለማጋበስ ስባል መነገድ ተገቢ አይደለም” ብለኋል።

“ሁላችንም በእዚህ የምንገኝ የየራሳችን የሆነ ታሪክ አለን” ያሉ ቅዱስ አባታችን “ምን አላባት የ አንድ አንዳችን ታሪክ በምስቀል የተሞላ፣ የ አንድ አንዳችን ታሪክ ደግሞ በሐዘን የተሞላ ልሆን  ይችላል” ብለው “ ነገር ግን በአጠቅላይ በልባችን የውንድማማችነት መንፈስ ይሰርጽ ዘንድ ልባችንን ክፍት ልናደርግ ይገባል” በማለት አሳስበኋል።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው “የወንድማማችነት መንፈስ በሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ወስጥ ይሰርጽ ዘንድ፣ በተጨማሪም ሰላም እና መግባባት፣ ሰላምን በምፈልጉ እና በምመኙ ወንድም እና እህቶች መካከል ሰላምን እና መረጋጋትን ለማምጣት ይቻል ዘንድ፣ እንዲሁም በተለያዩ ባህሎች እና የሐይማኖት ተቋማት መካከል የስላም ምንጭ የሆነው መግባባት ይፈጠር ዘንድ፣  በውይይት ላይ የተመሠረት ግንኙነት አስፈላጊ” መሆኑን የገለጹት ቅዱስነታቸው “ሁላችንም በእየ ግላችን መንፈሳዊ ቋንቋ፣ ለወንድም ገዳይ መግዣ የዋለው 30 የብር ሳንቲም ተወግዶ፣ በአንጻሩም ወንድማማችነት እና መልካምነት ይሰፍን ዘንድ እና ይህ የወንድማማችነት መንፈስ በዓለም ሁሉ ውስጥ ይስፋፋ ዘንድ እግዚአብሔር እንለምን” በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን አተናቀዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.