2016-03-25 16:24:00

የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ኅብረት


አሸባሪያን እውን እንዲሆን ለሚሹት የሕዝብ ልማዳዊ ሕይወት የመለወጥ ፍርሃትና እርስ በእርስ የተጠራጣሪነት አዝማሚያ የመሳሰሉት ሰላም አደፍራሽ ምርጫዎች ሁሉ እንዳይታይ ሁሉም ለሰላምና ለመግባባት ለመወያየትና ለመቀራረብ እንዲተጋ የጠቅላላ የኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳ ምክር ቤት ኅብረት ዋና ጸሓፊ ክብሩ አባ ፓሪክ ዳልይ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ የምክር ቤቱ የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤት ኅብረት ጥሪ በማስተጋባት በርግጥ እየታየ ያለው ግብረ ሽበራ ምክንያት ፍርሃት ሊያድርብህ ባህርያዊ ነው። ነገር ግን ፍርሃቱን በጥንቁቅነትና እርስ በእርስ የመደጋገፍና በመተሳሰብ መንፈስ መመራት ይኖርበታ። ካልሆነ ፍርሃቱ ይገዛናል ያሸባሪያን ፍላጎትም ለእርስ በእርስ ተጠኣጣሪነትም ለሚዳርገው ፍርሃት እንድንገዛ ብለዋል።

የብራሰልስ የጸጥታ ኃይል መግለጫ ሁሉም ንቁና ጥንቁቅ በመሆን አካባቢው እየቃኘ ዕለታዊ ኑሮው መፈጸም ይኖርበታል የሚል ሃሳብ አዘል መሆኑ የጠቀሱት ክቡር አባ ዳልይ ሆኖም ዕለታዊ ሕይወት በርታ ብሎ መኖር ግድ ነው፡ ኤውሮጳ በዓለም ከተከሰቱት አበይት የዓለም ጦርነቶች ወዲህ ክብርና ሥርዓት የሚያረጋግጥ ሁነት ለመሆንር ጦርነት ሊከሰት የሚደርግ ሁሉን ነገር ከወዲሁ ለመግታት እነዚያ እሴቶችና ሥርዓት ሁሉ ከተጋርጦዎ የበርቱ መሆናቸው በመታመንና በመመስከር ያጸናችው ኅብረተሰብ አለ መደናግጥ ያንን እሴት ዛሬም ህያው ማድረግ ይኖርበታል። የኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ኅብረትም ይኸንን ነው የሚያነቃቃው። በመተባበር በመቀራረብ በመተሳሰብ መኖር ግብረ ሸብራና አሸባሪያንን ለመለየት ያግዛል። በመተባበር በመደጋገፍና በመቀራረብ ሰላም በማስፋፋት ረገድ የአሸባሪያን የሚሹት ሁከትና ጠብ ሁሉ ማክሸፍ ይኖርብናል ብለዋል።

ካቶሊካውያን ክርስቲያኖች በጠቅላላ የሚያምኑባቸው እሴቶች ለኤውሮጳ ባህል መሠረት መሆኑ ማንን የማይክደው ሓቅ ነው፡ ስለዚህ ይኽ ለኤውሮጳ ባህል ማኅበራዊ ሰብአዊ ሕይወት መሠረት የሆነው እሴት የዛሬ 70 ዓመት በፊት ለተጀመረው ለኤውሮጳ ኅብረት መረጋገጥ መሠረቱ እሴቱ ነው፡ ይኽንን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ራእይ ሥር ስንመለከተውም እኚሕ ኤውሮጳዊ ያልሆኑት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ኤውሮጳን ለየት ባለ አይን በመመለከት ኤውሮጳ ኤውሮጳ የሚያስብላ እሴቶች የሚያስታውስ ነው። የውህደት አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያ የበላይ መንፈሳዊ መሪ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳሳት የተጣለው ያሸባሪያን ጥቃት ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ፍርሃትን በጽናትና በብርታት በመደጋገፍና በመቀራረብ እንዲገታ ሁሉን ይተባበር ዘንድ አደራ ብለዋል፡ በዚህ ለበዓለ ፋሲካ በመቀራረብ ላይ በምንገኝበት ወቅትም ያ ኢየሱስ ክርስቶስ ያረጋገጠው ተስፋ ለኤውሮጳ የማንነት መለያዋ መሠረት ነው፡ ይኸን መለያ መኖር ችግሮችን እንዲቀረፉ ያደርጋል ያበረታል ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.