2016-03-25 16:19:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ ከፓሪስ በኋላ በብራሰልስ የተከሰተው የሽበራ ጥቃት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ሮማ በሚገኘው የጸጥታ ኃይል አባላት ዋና ሕንጻ አቅራቢያ በሚገኘውን የቅዱስ ሳን ቪታለ ባዚሊካ በምኅረተ ዓመት ምክንያት ቅዱስ በር ለመክፈት በመሩት ሊጡርጊያዊ ሥነ ሥርዓት ባሰሙት ስብከት እዚያ ለተገኙት ለመላ የጸጥታ ኃይል አባላትና የሮማ የእሳት አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት የደን ሃብት ጥበቃ ኃይል አባላት የከተሞችና የዜጎች ጸጥታና ደህንነት በማስከበር ተልእኮ እየሰጡት ያለውን አገልግሎት በአድናቆት አመስግነው፡ በተለይ በዚህ በአሁኑ ወቅት እጅግ እየሰፋ ያለው ግብረ ሽበራ የመሳሰሉትን አሰቃቂ ጥቃት ሁሉ እንዳይከሰቱ ከወዲሁ እያካሄዱት ያለው ጥብቅና ጥንቁቅ ክትትል ሰላማዊ

ያብሮ መኖር ጥሪ ማኅበራዊ ኑሮ የዴሞክራሲ ሥርዓት ነጻነትና የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ያለመ ተግባር እየመሰከሩ ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ብፁዕነታቸው የሊጡርጊያውን ሥርዓት አጠናቀው እንዳበቁም እዛው ከተገኙት የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች በብራሰልስ አሸባሪያን የጣሉት ግብረ ሽበራ ርእስ ዙሪያ ላቀረቡላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፥ በፓሪስ ቀጥሎም በብራሰልስ የተጣለው ግብረ ሽበራ በእውነቱ ፈረንሳይ የተጣለባት ያሸባሪያን ጥቃት ያስከተለው ቁጣና ኃዘን እየበረደ ሕዝቡ ወደ ልሙድ ሕይወቱ በመመለስ ላይ ባለበት ወቅት ተመሳሳይ ግብረ ሽበራ በብራሰልስ ሲጣል ማየቱ በውእውነቱ እጅግ የሚያሳዝንና ግብረ ሽበራ ሁሉም እንዳይረጋጋ በሰላም ዕለታዊ ሕይወቱን እንዳይመራ እያደረገ ነው፡ ሸበራና አሸባኢያን ኃይሎች ሰላማዊ የጋራ ኑሮ የሚያናጉ ጸረ ሰብአዊ ተግባር ናቸው በማለት ገልጠው ያሸባሪያን ጥቃት ዙሪያ እየተሰጠ ያለው የጸጥታና ደህንነት ግብረ መልስ ሁሉ ጥንቃቄ እንዲከወን የሚያነቃቃ ነው፡ ይኸንን በመመልከትም በአገረ ቫቲካንና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካና በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ የሚካሄዱ ሊጡጊያዊ መርሃ ግብሮችና አሸባሪያን አደጋ ይጥላሉ በሚለው ሥጋት ምክንያት አይሰረዝም። ስለዚህ ሥጋቱ ያለ ቢሆንም ቅሉ የተወጠነው መርሃ ግብር እንደተጠበቀው ክውን ይሆናል በማለት መልስ እንደሰጡ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.