2016-03-23 16:27:00

የብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን የቡልጋሪያ ሐዋርያዊ ጉብኝት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ.ኤ.አ. መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም. የጀመሩት የቡልጋሪያው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን እ.ኤ.አ. መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. እንዳፈጸሙ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ  አክሎ ብፁዕነታችው እ.ኤ.አ. መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ከአገሪቱ ርእሰ ብሔር ፕለቭነሊየቭ ጋር በመቀጠልም ከፓትሪያክ ብፁዕ ወቅዱስ ነኦፊት ጋር መገናኘታቸው ገልጦ፡ በዚህ ባካሄዱት ግኑኝነትም በቡልጋሪያና በቅድስት መንበር መካከል እ.ኤ.አ. በ 1925 ዓ.ም. በቅድስት መንበር በኩል ብፁዕ አቡነ አንጀሎ ሮንካሊ ልኡክ በማድረግ የተጀመረው ክሌአዊ ግኑኝነት ሰፋ ባለ የስምምነት ደረጃ ባይሆንም አንድ ማለቱን ዘክረው። ብፁዕ ካርዲናል ሮናካሊ የቅዱስ ጴጥሮት ተከታይ ር.ሊ.ጳ. ዮሓንስ 23ኛ ከሆኑም በኋላ ቡልጋርያ በልባቸው አቢይ ሥፍራ የነበራት አገር ሆናለች። በሁለቱ አገሮች ማለትም በአገረ ቫቲካንና በቡልጋሪያ መካከል በይፋ ልኡካን በመለዋወጥ ደረጃ ክሌአዊ ግኑኝነቱ የጀመረው የኮሙኒዝም ሥርዓው በወደቀበት በትክክልም ከ 1990 ዓ.ም. ወዲህ መሆኑና፡ በዚያኑ ወቅት ቅድስት መንበር ብፁዕ አቡነ ማሪዮ ሪዚ በቡልጋሪያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብላ መሽሟንም አስታውሰው። ግኑኝነቱ ጥንታዊና ታሪካዊ መሆኑ አጠር ባለ መልኩ በሰጡት ታሪክ ጠቀስ ንግግር የግኑኝነቱ ታሪክ መዳሰሳቸው አስታወቀ።

ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ቡልጋሪያ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በዚያች አገር እ.ኤ.አ. በ 2002 ዓ.ም. ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ያካሂዱት ታሪካዊ ሐዋያዊ ጉብኝት ዘክረው፡ እሳቸው ያካሄዱት ጉብኝትም በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ግኑኝነት መልካምና አመርቂነቱንም የሚመሰክርና በሁሉም መስክ እድገት እንዲያረጋግጥ አድርገዋል።

ቡልጋሪያ የምዕራብና የምስራቅ ባህሎች ሃይማኖቶችና ሕዝቦች የምታገናኝ አገር ነች መሆንዋ ባስደመጡበት በሶፊያ በተካሄደው ዓውደ ውይይት በዚያች አገር የሚገኙት የተለያዩ አገሮች ልኡካን የተለያዩ ሃይማኖቶች የበላይ መንፈሳዊ መሪዎች የባህልና የማኅበረሰብ የመንግሥት አካላት ጭምር በክብር እንግድነት መሳተፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.