2016-03-21 16:17:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ዓይንን በማየት ልብን መመልከት


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እ.ኤ.አ. መጋቢት 19 ቀን ዓመታዊ የቅዱስ ዮሴፍ በዓል ባከበረችበት ዕለት በደቡብ አፍሪቃ፡ ቦትስዋና፡ ሎሴቶና በናሚቢያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ እንዲሆኑ ለሸሟቸው የኔታ ፒተር ብሪያን ወልስና እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ የኔታ ሚገል አንገል አዩሶን ማዕርገ ጵጵስና በሰጡበት መስዋዕተ ቅዳሴ፥ “አቡን ሳያቋርጥ የሚጸልይ ቅርቡ ለሆኑት ካህናቶቹ ቅርብና ጥንቃቔ እንክብካቤ የያደርግ የእያንዳንዱን ሰው ልብን ለመመልከት የእያንዳንዱን ሰው ዓይን የሚያይ ዘወትር በአገልጋይነት መንፈስ የሚኖር ማለት ነው” የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ ስብከት መለገሳቸው የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደካሮሊስ ገለጡ።

ያንድ አቡን ያንድነት መመዘኛው አገልግሎቱ ነው። ለዚህም ነው ብፁዓን አቡናት ዝቅ እንዲሉ ትሑታን እንዲሆኑ የተጠሩት። ከሁሉም ያነሱ ለመሆን የተጠሩ፡

የሁሉም አገልጋይ፡ ዘወትር አገልጋይ

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ እ.ኤ.አ. መጋቢት 13 ቀን 2013 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡ በኋላ መጋቢት 19 ቀን 2013 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልታናቸውን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ያስጀመሩበት ዝክረ ሦስተኛ ዓመት በሚታሰብበ ቀን በሰጡት ማዕርገ ጵጵስና፥ ኤጲስ ቆጶስ አገልጋይ ለመሆን የሚሰጥ ክብር ነው፡ ያገልጋይነት ክብር ነው። “….ከእናንተ መካከል ትልቅ የሆነ እንደ ትንሽ ይሁን፡ አለቃ የሆነም እንደ አገልጋይ ይሁን…” ይኽ ነው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ትእዛዝ፡ የሁሉም አገልጋዮች፡ ዘወትር አገልጋዮች፡ ለሚመቸን ብቻ ሳይሆን ‘ለሁሉም’ እንዳሉ ደካሮሊስ አስታወቁ።

በቅድሚያ ጸሎት

ጳጳጳስ ሰባኬ ክርስቶስ ሲሆን በጳጳሱ አማካኝነት በቀጥታ ሰባኪው ክርስቶስ ነው፡ ቤተ ክርስቲያንን በየዋህነት በአሳቢነትና በአንቀጸ እምነት የሚያቆማትና ሠሪው መሪው ክርስቶስ ነው፡ ስለዚህ በውስጧ ጉልበቱን አጥፎ የማይጸልይ አቡን ሊኖራት አይገባም። ሊኖርም አይችልም።

የአንድ አቡን ተቀዳሚው ኃላፊነት ጸሎት ነው፡ ሰባት ዲያቆናት ሲመረጥ ይኸንን ምዕዳን ያሳሰበውም ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። ሁለተኛው ሃላፊነቱም ቃልን ማበሰር ነው፡ ይኸንን ተከትለው ሌሎች ሃላፊነቶች ይመጣሉ። የማይጸልይ አቡን ባዶ ነው።

ለካህናቱ ቅርብና ከካህናቱ ጎን የሚሆን

ለካህናቱ ጊዜና ቦታ የሌለው አቡን ሊኖር አይገባም። ሊያናግሩት የሚፈልጉት ካህናቱን ቀርበው ሊወያዩት የሚሹትን ካህናታቹን ቀጠሮ መስጠት ሳይሆን። ለእነርሱ ጊዜና ቦታ ሊኖረው የገባዋል፡ ለአንድ አቡን ተዳሚው ቅርብ ካህናቱ ናቸው፡ ስለዚህ ቅርብ ያለው ጎረቤትህን የማታፍቅር ከሆንክ ሌሎችን ማፍቅር አትችልም። አፈቅራለሁ ብትልም ትዋሻለህ።

አይንን የሚመለከት

ለመንጋው እጅግ ቅርብ የሆነ እረኛ። ከሁሉም መዝገቦች ወረቀተቾ ዝክረ ነገር ባሻገር ሰው አለ። ስለዚህ ሰው ማስቀደም ያስፈልጋል። ለድኾች ቅርብ በድኽነት ለተጠቁት ድጋፍ ለሚያስፈጋቸው ቅርብ፡ የምእመናኑን ልብ ለመመልከት አይናቸውን የሚያይ። ካህን ዲያቆን ምእመንም ይሁን በልብ መመልከት ይኖርበታል እንዳሉ ደካሮሊስ አስታወቁ፡








All the contents on this site are copyrighted ©.