2016-03-19 16:05:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ ኢዮቤልዩ የምሕረት ዓመት ለሶሪያ ሰላም


ሮማ ከተማ በሚገኘው በጁስቲኒያኒ ሕንጻ ባለው የትርኢት አዳራሽ እ.ኤ.አ. ከ 1300 ዓ.ም. እክሰ 2016 ዓ.ም. በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የታወጁት ኢዮቤልዩ ዓመታት  የሚተርክ የስእል የቅብ የቅዱሳት ዓመታት መወሰኛ አዋጅ በአርእስተ ሊቃነ ጳጳሳ እጅ ጽሑፍና ፊርማ የተኖረበ የድንጋጌው ብራናዎች ያጠቃለለ እ.ኤ.አ. እስከ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቅ ትርኢት እ.ኤ.አ. መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካዲናል ፒየትሮ ፓሮሊናን የኢጣሊያ የሕግ መወሰኛው የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ፒየትሮ ግራሲ በጋራ መርቀው እንደከፈቱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ከምረቃው ሥነ ሥርዓ በኋላ ባስደመጡት ንግግር፥ ዕለቱ በሶሪያ የተቀሰቀሰው ጦርነተ አምስተኛ ዓመቱን ያስቆጠረበት ቀን መሆኑ ዘክረው፡ በዚህ 5 ዓመት ባስቆጠረው ገና ዕልባት ባላገኘው ጦርነት ሳቢያ ለሞት ለስደት የተዳረገው የአገሪቱ ሕዝብ ሥፍር ቁጥር የለውም። ሆኖም በቅርቡ በሶሪያ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደግፍ መንገድ ለማፈላለግ በጀነቭ የተካሄደው የሰላም ውይይት እንዲሁም የሩሲያው መንግሥት የአገሪቱ የመከላከያ ኃይል አባላት ከሶሪያ ለማስወጣት የወሰደው ውሳኔ በእውነቱ መልካም እርምጃ ነው፡ የሶሪያ ሕዝብ ስቃይና መከራ የሚያዳምጥ ለዚህ ሕዝብ ስቃይ ጆርውን የሚሰጥ ፖለቲካ እንዲረጋገጥ እማጠናለሁ ብለው፥ በዚህ አጋጣሚም ብፁዕነታቸው እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ መቄዶኒያ ለሐዋርያዊ ግብኝት እንደሚሄዱ ጠቀስ በማድረግ በዚያች አገር የሚገኙት የሶሪያ ስደተኞችና ተፈናቃዮች የሚገኙባቸውን መጠለያ ሰፈሮችንም እንደሚጎበኙ ገልጠዋል ሲል የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቆመ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን ኢዮቤልዩ የምኅረት ዓመታት የሚያወሳው ታሪክ ዘንድሮ እየተኖረ ያለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት የምኅረት ዓመት አቢይ ግምት የሰጠ ሲሆን በዚህ ምክንያትም ሮማ ለሚገቡት መንፈሳዊ ነጋድያን ጥሩ አጋጣሚ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.