2016-03-19 16:13:00

ስደተኞችን ላለ መቀበል የሚገፋፋ ስሜት ለመስፋፋት የመገናኛ ብዙኃን ሚና


በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች በጠቅላላም በዓለም አቀፍ ደረጃም ሊባል ይቻላል፡ ስደተኞች ወይንም መጤውን ላለ መቀበል ፍላጎት የሚያስፋፋ ወይንም የሚያነቃቃ በመገናኛ ብዙኃን ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተመለከተ የሚሰራጨው ዜና መሠረት ነው፡ የመገናኛ ብዙኃን የሚያካሂዱት የውይይት አምድ የሚያነቃቃው ጭምር መሆኑ ሌላውን እንድትጠላ የሚያደግ ንግግር ወይንም ድምጽ በሚል ርእስ ሥር ስደተኛውና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ በተመለከተ በቅርቡ የተጠናቀረው የጥናት ሰነድ እንደሚያረጋግጠው የቫቲካን ርዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ ገልጠው፡ ስደተኞች ተፈናቃዮችና ኅዳጣን የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚነዛው የጥላቻ የውንጀላና ስደተኞች የሚገቡባቸው አገሮች ላለባቸው ለሚያጋጥማቸው የተለያየ ችግር ተጠያቂው ስደተኛው እንደሆነ የሚያደርግና የሚያስገምት አመለካከት ነው፡ እንዲህ እንዲሆን የሚያደርገውም በጠቅላላ ባይሆንም አብላጫው የመገናኛ ብዙኃን ስደተኛው ጉዳይ በተመለከተ የሚሰጡት ዜና የሚፈጥረው ስሜት ነው፡ በተለያዩ ማኅበራዊ የመገናኛ ድረ ገጾች አማካኝነት በትዊተር በፈይስቡክ እንዲሁም ዩቲዩብ አማካኝነት በ 2014 ዓ.ም. ብቻ ሃሳብህን የመግለጥ ነጻነት ጀርባ ጸረ ስደተኛው ዜጋ ላይ ያነጣጠረ የሚሰነዘሩ የዘረኝነት ጽሑፎች እጅግ ከፍ እያለ መምጣቱ ይነገራል።

ስለዚሁ ጉዳይም በተመለከተ በኢጣሊያ ያለው ሁኔታ ምን ተመስሎው ለማብራራት ጥናቱን ያካሄደው አንቀጽ 21 የተሰየመው መንግሥታዊ ያልሆነ ማኅበር አባል ጥናቱን የመሩት ኤሊሳ ማሪኖላ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ፈይስቡክ ትዊተር የመሳሰሉት ማኅበራውያን ድረ ገጾች በኩል አድራሻ ላለው ሁሉ መልካምም ይሁን መጥፎ ሃሳቡን የሚለጥፍባቸው ሰሌዳዎች ናቸው የግል አስተሳሰብና አመለካከት ማስታውቂያ የሚለጠፍባቸው ሰሌዳዎች ናቸው። እንዲህ በመሆኑም በእውነቱ የሚለጠፉት ጽሑፎች ለመቆጣጠር እጅግ ያዳግታል። ለመቆጣጠር ላለመቻሉ አንዱ ምክንያትም በእነዚህ ማኅበራዊ ድረ ገጾች የተለያዩ የማስታወቂያ መልእክቶች የሚተላለፍ በመሆኑ ክፍት አድርጎ ለመተው ግድ ይሆናል። ገቢ የሚያኙት በድረ ገጾቹ አማካኝነት በሚያስተላልፉት የድርጅቶች ኢንዳስትሪዎና ተቋሞች የሚያቀርቡት የግዥ ማስታወቂያ ነው። ሆኖም ይላሉ የሕትመት ጋዜጦች ቴሊቭዥን ራዲዮ የመሳሰሉት የመገናኛ ብዙኃን የአድማጭ ብዛት እንዲኖራቸው አወታዊም ይሁን አሉታዊ ግጽታ ሳያመዛዝኑ የሁሉንም ነው የሚያሰራጩት። ጥራት እውነት ፍትህ የተሰኙት መመዘኛዎች ወደ ጎን እያተደረጉ ናቸው። አንዳንድ የመገናኛ ብዙህንም ታዋቂነት ስለ ሌላቸው በአሁኑ ሰዓት እጅግ አንገብጋቢ ርእስ ሆኖ ያለው የስደተኛነት ጸዓት ጉዳይ ላይ ተንተርሰው በአሉታዊ መንገድ በማቅረብ ታዋቂነት ከማግኘትም አልፈው የጥላቻውን ስሜት እንዲስፋፋ እያደረጉ ነው፡ ስለዚህ በመንግሥት ሥር የሚተዳደሩ የመገናኛ ብዙኃን በአሁኑ ወቅት የመከባበር የመቀባበልና የመቀራረብ ባህል ዘመቻ እያፋጠኑ ናቸው። የሚመሰገን መርሃ ግብር ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.