2016-03-17 09:57:00

ቅ.አ. ፍራንችሄስኮ “ፍቅር በቃል ብቻ ሳይሆን የሚገለጸው እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅራችንን በተግባር ማሳየት ይገባናል”።


እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 12,2016 ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት ኢዩበሊዩን አስመልክቶ ዘወትር ቅዳሜ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚካሄደው ሳምንታዊ አስተምሮ ላይ ለተገኙ ከሃምሳ ሺ በለይ ለሚሆኑ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች “ፍቅር በቃል ብቻ ሳይሆን የሚገለጸው እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅራችንን በተግባር ማሳየት ይገባናል” ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ማለታቸውን ጋዜጠኛችን አሌክሳንድሮ ጂዞቲ ዘገቡኋል።

ኢየሱስ የሐዋሪያቱን እግር ባጠበበት ወቅት ለሐዋሪያቱ እና ለክርስቲያኖች ሁሉ እምነታቸውን በተግባር በተደገፈ አገልግሎት እና ፍቅር መግለጽ እንዳለባቸው አሳስቡኋቸውል በማለት አስተምሮኋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን፣ ኢየሱስ በዚህ ያልተጠበቀ ድርጊቱ እራሱን አሳልፎ እስከመስጠት ድርስ እንደ ወደደን ሁሉ እኛም  እርስ በእርሳችን እንዋደድ ዘንድ አዲስ የሆነ ትዕዛዝ ስለሰጠን ይህንን ትዕዛዝ በተግባር በተደገፈ አገልግሎት መግልጽ እንደሚገባ አሳስበኋል።

“ለሰዎች ያለንን ፍቅር በተግባር ጭምር መግለጽ ያስፈልጋል በማለት አስተምሮኋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን፣ ፍቅር መገለጽ የሚገባው በቃላት ብቻ መሆን እንደ ሌለበት በማስረዳት በተግባር በተደገፈ አገልግሎት እና እርዳት ለተቸገሩት ሁሉ በማድረግ መሆን እንዳለበት ገልጸው፣ ይህንን የፍቅር መገለጫ የሆነውን መንፈሳዊ ተግባር በምንፈጽምበት ወቅት ግን ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል በምዕራፍ 6,3 ላይ “እናንተ ግን ለድኾች ስትመጸውቱ ቀኝ እጃችሁ የሚያድረገውን ግራ እጃችሁ አይወቅ” ብሎ እዳሳሰበን፣ መልካም ተግባራትን በምንፈጽምበት ወቅት ለታይታ ሳይሆን ማድረግ የሚጠበቅብን በስውር ለሚያየን የሰማዩ አባታችን ክብር ብለን ማድረግ ይጠበቅብናል ብለኋል።

መልካም ተግባራትን መፈጸም ለክርስቲያኖች ብቻ የተተወ ተግባር መሆን የለበትም በማለት አስተምሮኋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን፣ መልክም ተግባርትን መፈጸም ሰባዊ ተግባር በመሆኑም ጭምር መሆኑን አስረድተዋል።

ኢየሱስ የሓዋሪያቱ እግር ባጠበበት ወቅት “እኔ ጌታችሁ እና መምህራቹ ሆኜ ሳለው እራችሁን ካጠብኩ፣ እናንተም እንደ እዚሁ እርስ በእርሳችሁ ልትተጣጠቡ ይገባችኋል” ባለው መሰርት እርስ በእርሳችን ልንደጋገፍ እና ይቅር ልንባባል እንደ ሚገባም አውስተው፣ በተለይም አንዱ ለአንዱ መጸለይ እንድሚገባ ገልጸው ፍቅርን፣ በጎነትን እና መልካም አገልግሎትን አንዱ ለአንዱ ማበርከት እንደሚገባ ገልጸኋል።

የታመሙትን ቤተሰቦቻቸውን እና የማህበረሰብ ክፍሎችን በመንከባከብ ላይ የተሳተፉ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ ይህ በመልካም ተግባር የተደገፈ ተግባራቸው የምያስታውሰን “እኔ እንዳደረኩላችሁ እናንተም እንዲሁ አድርጉ” ያለንን የኢየሱስን ቃል በመሆኑ ሁላችንም የተቸገሩትን ሰዎች በማገዝ ለክስቶስ ያለንን ፍቅር እና ታማኝነት በተግባር መገለጽ ይጠበቅብናል በማለት በለኋል።

በመጨረሻም “የሰማይ አባታችሁ ይቅር እናዳልችሁ እናንተም ይቅር ተባባሉ” የሚለው የእግዚኣብሔር ቃል እንደ ምያሳስበን እኛም ወንድሞቻችን እና እህቶቻችንን ይቅር ማለት እንደ ሚጠበቅብን ገልጸው በተለይም ደግሞ ወጣቶች ትክክለኛውን የሕይወት ጎዳና መያዝ እንዳለባቸው እና የሰው ልጅ እሴቶችን በመጠበቅ እምነታቸውን በተግባር መግለጽ እንዳለባቸው ገልጸው እና ቡራኬ በመስጠት አስተምሮኋቸውን አጠናቅቀዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.