2016-03-17 10:22:00

ቅ.አ. ፍራንቼስኮ “እግዚኣብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ለማወቅ ከፈለግን የኢየሱስን መስቀል ማየት ብቻ በቂ ነው”።


በትላንትናው እለት ማለትም በመጋቢት 15,2016 ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ  የጸሎት ቤተ በምያሳርጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ “እግዚኣብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ለማወቅ ከፈለግን የኢየሱስን መስቀል ማየት ብቻ በቂ ነው” በስበከታቸው ወቅት  ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ማለታቸው ጋዜጠኛችን አሌክሳንድሮ ዲ ካሎስ ዘግቡኋል።

የመጀመሪያው የመጻሓፍ ቅዱሳችን ክፍል በሆነው ኦሪት ዘፍጠርት፣ እንዲሁም በመጨረሻ የመጻሓፍ ቅዱሳችን  ክፍል በሆነው የዩሓንስ ራዕእ ላይ በተጠቀስው መሰረት የሰው ልጆች ጠላት እና አሳሳች ተደርጎ የተወሰደው እባብ መሆኑን ያወሱት ቅዱስ አባትችን፣ እባብ በሰው ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ የሚያስከትል እና ሚስጢራዊ በሆነ መልኩ ሰዎችን በማሳሳት የሚታወቅ አደገኛ እንስሳ መሆኑን  በስብከታቸውን ወቅት አስረድተዋል።

በኦሪት ዘኍልቍ ላይ እንደተጠቀስው፣ በሙሴ መሪነት ከግብጽ የባርነት ቀንበር ሥር ነጻ ወጥተው ወደ ተስፋይቱ ምድር ይጓዝ የነበረ የእስራኤል ሕዝብ በበርሃ ውስጥ በውሃ ጥምና በረሀብ በመጎሳቆላቸው፣ በእግዚአብሔር እና በሙሴ ላይ መቆጣት እና  በማጉርምረም መጀመራቸውን እና በእግዚኣብሔር ላይ ያልቸውን ተስፋ እና እምነት በመሰረዝ ሌላ በወርቅ  የተሰራ ጥጃ ምስል ሰርተው ማምለክ በጀመሩ ጊዜ እግዚኣብሔር በእባብ ተነድፈው እንዲሞቱ እንዳደረጋቸው የመጀመሪያው ምንባብ እንደ ሚገልጽ ያወሱት ቅዱስ አባታችን፣ ነግር ግን ብዙም ሳይቆይ እግዚኣብሔር በቃላት ሊገለጽ በምያዳግት ምህረቱ እንደጎበኛቸው እና ሙሴን በነሓስ እባብ ሰርቶ በእንጨት ላይ እንዲሰቅል እና ያንንም የትሰቀለውን በነሓስ መልክ የተሰራዉን እባብ ያዩ ሁሉ ተመልሰው በሕይወት ይኖሩ ዘንድ መግለጹ ደግሞ  የምያሳየው ምንም እንኳን ሁላችንም ሐጥያተኖች ብንሆንም እግዚኣብሔር ግን በምህረቱ ሁል ጊዜ ከእኛ ጋር መሆኑን ያስመሰከረ እውነታ መሆኑንም ቅዱስ አባታችን ገልጸዋል።

በዕለቱ ከዩሓንስ ወንጌል በተነበበው የመጻሓፍ ቅዱስ ክፍል እንደተጠቀስው ኢየሱስ ከፈሪሳዊያን ጋር ያደረገውን ክርክር ያወሱት ቅዱስ አባታችን፣ በዩሓንስ ወንጌል በምዕራፍ 8, 28 ላይ እንደ ተጠቀስው ኢያሱስ ፈሪሳዊያንን “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደርጋችሁት ጊዜ እኔ እንደሆንኩኝ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ” ማለቱን ያውሱት ቅዱስ አባታችን “እኔ እንደሆንኩኝ” የሚልውን ቃል በተመሳስይ መልኩ እግዚአብሔርም ለሙሴ ማናገሩን አስታውሰው እባብ  የሓጥያት እና የሞት መገለጫ እንደ ሆነ ሁሉ ሓዋሪያው ጳውሎስ በመልዕክቱ “ምንም እንኳን ክርስቶስ በባህሪው ከእግዚኣብሔር ጋር እኩል ቢሆንም እኛን ለማዳን ስል ተሰቅሎ ማሞቱን” እንደ ገለጸው ሁሉ ያዛሬው የእግዚአብሔር ቃል እንደ ምያስታውሰን ምንም እንኳን ሓጥያተኞች ብንሆንም ኢየሱስ በትህትናው እራሱን እስከ ማዋረድ ድረስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞቶ እንዳዳነን ግን ማመን ይጠበቅብናል በማለት አሳስበዋል።

ይህ ኢየሱስ የፈጸመው ተጋባር የሚያሳየን ለእኛ ያለው ፍቅር እና የደህንነት ታሪካችንን የምያስመሰክር ተጋብር መሆኑን ነው፣ ያሉት ቅዱስ አባታችን “እግዚአብሔር ለእኛ የላውን ፍቅር ማውቅ ከፈለግን ቀና ብለን መስቀሉን በማየት ለእኛ ስል እራሱን ባዶ ያደረገውንና የተሰቃየውን ስቃይ መገንዘብ ይጠበቅብናል” ብለዋል።

በመጨረሻም “ሓጥያት ሁል ጊዜ ከሰይጣን የሚመጣ ተጋብር ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን “ኢየሱስ ግን ይህንን የሓጥያት ምንጭ የሆነውን ሰይጣን በማሸነፍ እኛን ከውደቅንበት እንድምያነሳን” ገልጸው “መስቀልን በምናይበ ወቅት ሁል ትዝ ሊለን የሚገባው ጉዳይ በመስቀሉ ላይ የሚታዩ የአቀራርጽ ጥበቦች እና ውበቱ ሳይሆን ኢየሱስ የተቀበልውን መከራ እና ስቃይ በማስታወስ፣ ሓጥያት በምንሰራባቸው ወቅቶች ሁሉ መልሰን መላልሰን እንድምንሰቅለውም በማወቅ ከሐጥያት ጎዳና መራቅ የምያስችለንን ጸጋ የኢየሱስ መስቀል ይሰጠን ዘንድ እንድያስታውሰን መጸለይ ይግባል” በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቅቀዋል።

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.