2016-03-17 09:26:00

ቅ.አ. ፍራንቼስኮ "ብዙ ምዕመናን በትዳር ወስጥ በሚፈጠር ከፍተኛ ችግር ምክንያት በከፍተኛ መከራ እና መራር ሕይወት ውስጥ ይገኛሉ"።


እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጋቢት 11,2016 በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጳዎሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ትዳርን በተመልከተ እየተሻሻለ ባለው የቤተ ክርስቲያን ሕግል ላይ በሚመክረው ስብሰባ ላይ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ መገኘታቸው የተገለጸ ስሆን እየተሻሻለ የሚገኘው የቤተክርስቲያን ሕግም በተክሊል የተጋቡ ጥንዶች ከአቅም በላይ የሆነ  ችግር በትዳራቸው ውስጥ በሚፈጠርበት ወቅት ችግራቸው በጥልቀት ከተመረመረ ቡኋላ ተክሊላቸውን ውድቅ ወይም የመሻር ስላጣን እንዲኖረው ተደረጎ እየተዘጋጀ መሆኑም ታውቁኋል። 

በጥቅምት ወር 2015 በቫቲካን በተካሄደው የቤተሰብ ጉባሄ ላይ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ “ብዙ ክርስቲያን ምዕመናን በትዳር ወስጥ በሚፈጠር ከፍተኛ ችግር ምክንያት በከፍተኛ መከራ እና መራር ሕይወት ውስጥ እያለፉ በመሆናቸው እና ይህም መከራ እና ስቃይ እምነታቸውን እንዲጠራጠሩ እይደረጋቸው በመሆኑ፣ በተጨማሪም ወቅታዊው የቤተ ክርስቲያን ሕግ ይህንን ቀውስ በተቀላጠፈ እና ወጤታማ በሆነ መልኩ ለመፍታት፣ አለመቻሉን” በጉባሄው ወቅት የገለጹ መሆኑ የሚታወስ ስሆን “ፍቅር እና ምሕረት” ቤተ ክርስቲያንን ይህንን ሚስጥረ ተክሊልን የተመልከተ የቤተ ክርስቲያን ህግ እድታሽል ያስገደዳት መሆኑን እና እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን ከምንጊዜም በላይ በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ምዕመናን ከማውገዝ ይልቅ ቅርብ መሆን እንዳለባት በውቅቱ በግለጻቸውም የሚታወስ ነው።

ይህ እየተሻሻለ ያለው ሚስጢረ ተክሊልን የተመለከተ የቤተ ክርስቲያን ህግ፣ በጋብቻ ውስጥ የተፈጠሩት ችግሮች በተፋጠነ ሁኔታ እና በጥልቀት መርምሮ መፍትሄ ለመስጠት ብቃት እንዲኖረው ታስቦ እየተዘጋጀ ስሆን፣ ቀደም ሲል የነበረውን የተወሳሰበ እና የተጓተተ የፍርድ ሂደትን በማስወገድ፣ በተቀላጠፈ እና ወጤታማ በሆነ መልኩ፣ በሀገረ ስብከት ደረጃ በአቡናት መሪነት በሚቍቋም የበተክርስቲያን ፍርድ ቤት እንዲፈታ መንገዱን የሚያመቻች እና በከፍተኛ ደረጃ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ባለትዳሮች አፋጣኝ መፍትሄ  ያስገኛል ብለው እንድሚያምኑ በስብሰባው ወቅት ቅዱስ አባታችን መግለጻቸው ታውቁኋል።

እየረቀቀ የሚገኘው አዲሱ ሕግ በጥልቀት እና በጥንቃቄ ሊመረመር እንደሚገባ እና እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ እንዲጨመርበት መጸለይ ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በተለይም የቤተክርስቲያን የፍርድ አካላት በከፍተኛ ችግር ለሚገኙት ቤተሰቦች የተፋጠን እና ምህረትን የተሞላ የፍትህ አገልግሎት ይሰጡ ዘንድም አሳስበኋል።

“እንደ እናት የምትቆጠርው ቤተክርስቲያን የእግዚኣብሔርን ምሕረት እና ፍቅር ለሕዝብ ማሳየት ይጠበቅባታል” ያሉት  ቅዱስ አባታችን፣ “በከፍተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ ቤተሰቦች ከማውገዝ ይልቅ መፍትሄ በመሰጠት በችግር ምክንያት ያጡትን ሰላም፣ ደስታ እና ተስፋ መልሰው እንዲያገኙ የማድረግ ምንፈስዊ ተልዕኮም ቤተ ክርስቲያን ስላላት ይህንን ተልኮ በአግባቡ ለመወጣት ይህ ህግ በጣም አስፈላጊ መሆኑን” ቅዱስ አባታችን ለስብሰባው ተካፋዮች አሳስበኋል።  

“በትዳር ውስጥ በተፈጠረው ከፍተኛ ችግር ተጠቂ ለሆኑ ሰዎች መፍትሄ በምናበጅበት በአሁኑ ወቅት፣ ምንም እንኳን ከፍተኛ ችግር በታዳራቸው ውስጥ ቢኖርም ያንን ችግር ተቋቁመው የሚኖሩ ብዙ ምዕመናን መኖራቸውን ገልጸው፣ በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚኖሩ እና ለትዳራቸው ከፍተኛ የሆነ ክብር በመስጠት ለችግሮቻቸው ሳይበገሩ ታማኝ ሆነው ያሉትንም ማድነቅ እና እግዚአብሔር ይረዳቸው ዘንድ መጸለይ ይገባናል” ያሉት ቅዱስ አባታችን “የዚህ ዓይነት የህይወት ምስክርነት የሚሰጡትን ምዕመናን ሁሉ ማበረታታት በጣም አስፈላጊ ነው” ማለታቸው ተውስቱኋል።  

በጨረሻም በችግር፣ በበሽታ እና በመከራ ወቅት ሁሉ ለተዳራቸው ታማኝ የሆኑትን ምዕመናን አድንቀው  እግዚአብሔር ያጸናቸው ዘንድ ተምጽነው ንግግራቸውን አጠናቅቀዋል።

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.