2016-03-17 11:35:00

ቅ. አ. ፍራንቼስኮ የ5 ለቅድስና የታጩ ብፁዕንን ሰነድ ተቀብለው ማጽደቃቸው ታወቀ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በትላንትናው ዕለት ማለትም በመጋቢት 15,2016 በቫቲካን የቅድስናን ጉዳይ የሚመለከትው የመማክርት ቢሮ የቀረበላቸውን የ5 ለቅድስና የታጩ ብፁዕንን ሰነድ ተቀብለው ማጽደቃቸው ታወቀ። የእነዚ ለቅድስና የታጩ የ5 ብጹዓንን ሰነድ ቅዱስ አባታችን ተቀብለው ማጽደቃቸው በመላው ዓለም ለምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልዩ ደስታን የፈጠረ ስሆን በተለይም ደግሞ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በመጭው መስከረም 4, 2016፣ ለእማሆይ ትሬዛ ክብር በሚዘጋጀው ስነ-ስርዓት ቅድስናቸው በይፋ እንደ አንደሚከበር የቫቲካን ሬድዮ ጋዜጠኛ አሌክስ አንድሮ ጂዞቲ ዘግቡኋል።

የተቀሩት የአራት ለቅድስና የታጩት ብጹዕን፣ ማለትም የፖላንድ ተውላጅ የሆኑት እና የኢየሱስ ማሪያም የካህናት ማህበር አባል የነበሩ የአባ ስታንስላው እና የብሪጂድነ ማህበር መስራች የሆኑት ማሪያ ኤሊዛቤታ በሰኔ 5,2016፣ እንዲሁም የተቀሩት የሁለቱ ማለትም በሜክስኮ 1929 የተሰዋው  የብጹዕ አባ ጁሴፔ ሳንኬዝ እና ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በክህነት ሕይወቱ ባሳየው መልካም ተግባር በጣም የምያደንቁት እና የሚወዱት የአርጄንቲናዊው ብጹዕ አባ ሮዛሪዮ ብሮኬሮ የቅድስና በዓል በይፋ በመጭው ጥቅምት 16, 2016 እንደ ሚከበር በተጨማሪም ለማውቅ ተችሉኋል።

በጣም ድሃ የሆኑትን የማህበረሰብ ክፍሎችን በመርዳት የሚታወቁት እና በጥቅምት 19,2003 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ እጅ የብጽዕናን ማእረግ ያገኙት ብጽዕት እማሆይ ትሬዛ፣ ከአስራሶስት ዓመት ቡኋላ የቅድስና ማህረግ ከብጹዕ አባታችን ፍራንቼስኮ መግኘታቸው የሚያሳየው፣ እኝህ የአልባኒያ ተውላጅ የነበሩ ሞኖክሴ  ሀገራቸውን ትተው የወንጌል አገልግሎትን ለማበርከት ወደ ህንድ ሀገር በመጓዝ፣ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ድኾችን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ቀን ከሌሊት ማገልገላቸው እና ከዚያም ቀስ በቀስ በመላው ዓለም እየተስፋፋ በመጣው ድኾችን እንዲረዳ በተቋቋመው ማህበራቸው ምክንያት በዓለም ላይ በበጎ ሥራቸው እንዲታወቁ እና ጎልተው እንዲወጡ ያስቻለቸው ተግባርቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ብጽዕት እማሆይ ትሬዛ “በቁስል የተሞላ የድሀን ሰውነት መንካት ልክ የኢየሱስን ሰውነት እንደ መንካት ይቆጠራል” በሚለው እምነታቸው የሚታወቁ ስሆን በሕይወታቸው ዘመን በመስቀል ላይ ሆኖ “ተጠማው” ለሚለው የክርስቶስ ጥሪ የተራቡትን እና የተጠሙትን በማብላት እና በማጠጣት ለክርስቶስ ጥሪ በተግባር መልስ መስጠታቸው ለቅድስናቸው ከፍተኛ አስተውጾ ማበርከቱ የሚታወቅ ነው።

ለዓለም ባበረከቱት መልካም ተግባራቸው ምክንያት በ1979 የዓለም የሰላም የኖቤል ተሸላሚ የሆኑት ብጽዕት እማሆይ ትሬዛ፣ በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በድኾች ውስጥ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያደርጉ እንደነበረ እና የወንጌልን አስተምሮ በሕይወታቸው በተግባር ያሳዩ የእግዚአብሔር አገልጋይ እንደነበሩም የሚታወስ ነው።

በኢትዮጲያም በ1973 የመጀመሪያው የብጹዕት እማሆይ ትሬዛ ማህበር ቤት በአዲስ አበባ በተለምዶ ስድስት ኪሎ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ መከፈቱ እና በውቅቱ ከ600 በላይ ለሚሆኑ ሕሙማን አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር የሚታወስ ስሆን፣ በአሁኑ ወቅትም በመላው የሀግሪቷ ክፍል ማለትም በአዲስ አበባ፣ በመቀሌ፣ በአድዋ፣ በደብረማርኮስ፣ በጎንደር፣ በባሌ፣ በጂጂጋ፣ በክብረ ማንግስት፣ በዲሬ ዳዋ እና በጅማ በአጠቃልይም በጅቡቲ እና በኢትዮጲያ 19 የድኾች መርጃ ማዕከላት እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ስሆን በእነዚህም ጣብያዎች ከመቶ ሃያ በላይ ደናግላን እና የበጎ ፍቅድ አገልግሎት ከሚሰጡ ሰዎች ጋር በመተባበርም ጭምር፣ በተለያዩ ዓይነት በሽታዎች የሚሰቃዩትን በድኽነት የሚኖሩትን የምህበረሰብ ክፍሎችን በማገዝ እና እንዲሁም ወላጅ አልባ የሆኑትን ሕጻናት በመርዳት ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ እና ማህበርሰባዊ አግልግሎትን ዘር እና አይማኖት ሳይለዩ እያበረከቱ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ነው።

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.