2016-03-16 16:37:00

ማላዊ፥ ብፁዓን ጳጳሳት በአገራቸው የሚታዩትን ግድፈቶችን አወገዙ


“እንደ እረኞች መጠን በአገራችን ያለው የኑሮ ደረጃ ልዩነት፡ የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ እጥረት፡ በድኻውና በሃታሙ መካከል እጅግ እየሰፋ በመሄድ ላይ ያለው የኑሮ ልዩነት፡ ፍትሕ አልቦ የሆነው የመንግሥት የግብር ክፍያ ሕግ፡ ተገቢና ጽኑ የመቆጣጠሪያ ደንብ የሚጠይቀው የገንዘብ ሃብት ቁጥጥር አለ መኖሩ እያስከተለው ያለው ችግር እያየን እንዳላየን ሆነን መኖር አይቻለንም” የሚል ሃሳብ ማእከል ያደረገ የእግዚአብሔር ምኅረት የተስፋ መንገድ ነው በሚል ርእስ ሥር ሐዋርያዊ መልእክት በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ማስተላለፋችው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በኤኮኖሚውና በማኅበራዊ ጉዳይ ብዙ እልፍ አእላፍ እጥረቶትች

ብፁዓን የማላዊ ጳጳሳት በአገራቸው በማኅበራዊ ዘርፍ የተጨበጡት አንዳንድ አወንታዊ ክንዋኔዎች ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት እንደ አብነትም እ.ኤ.አ. በ 2014 ዓ.ም. የተካሄደው ሕዝባዊ ምርጫ፡ በአገሪቱ ተከስቶ ለነበረው ለጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ የተስተካከለ ምላሽ ለመስጠት የተከናወነው ጥረትና የተካሄደው አንዳንድ የፖለቲካ ሕዳሴ  እውቅና በመስጠት ሆኖም በኤኮኖሚውና በማኅበራዊው ዘርፍ ብዙ መኬድ የሚገባው መንገድ አለ ብለው፡ እጅግ የሚያሳዝነው የጤና ጥበቃ ጉዳይ በተመለከተ መንግሥት የወሰደው የባጀት ቅነሳ ውሳኔ የአገሪቱ የሕክምን አገልግሎት መስጫ ማእከሎችን የሚያዳክም ጥራት እንዳይኖረው በማረግ የታማሚው ጤና ላደጋ የሚያጋልጥ ነው። ይኽ የባጀት ቅነሳም ተራ ለሆኑ የሕክምና ምርመራዎች ሳይቀር ሕዝቡ ማለትም ገንዘብ ያለው ወደ የግል ማከሚያ ቤቶች እንዲሄድ ድኻው ለገዛ እርሱ እንዲተው እያደረገው ነው እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የምግብ እጥረት

ምንም’ኳ ተከስቶ የነበረው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ያስከተለው ቀውስ ለመቅረፍ ብዙ ጥረት የተደረገ ቢሆንም ቅሉ፡ አሁንም 2.8 ሚሊዮን የሚገመት የማላዊ ዜጋ በምግብ እጥረተ እጅግ በከፋ ሁኔታ መጎዳቱ ያስታወሱት ብፁዓን ጳጳሳት የሕዝብ ውሎው ማብቂያ የሌለው ወረፋ በመያዝ የበቆሎ ምርት ሽመታ ሆነዋል፡ እናቶች እፍኝ የማይሞላውን የበቆሎ ምርት ለመግዛት እድል እንዲያገኙ በአበይት ሱቆች በር ውጭ ልጆቻቸውን ታቅፈው ሌሊቱን ያሳልፋሉ። ይኽ ሁሉ ማኅበራዊ ችግር እንዲቀረፍ የሁሉም ተሳትፎ በበለጠ መንግሥት ከሕዝብ የተቀበለው ኃላፊነት ሊወጣ ይገባዋል፥

ድኽነት ላለ መረጋጋት አደጋ ያጋልጣል ለቤተሰብ ከባድ ጥቃትም ነው

ብፁዓን ጳጳሳቱ ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት በአገረ ማላዊ እየታየ ያለው ድኽነት እጅግ አስከፊ መሆኑ በማብራራት። ሁኔታው ማለቂያ ለሌለው ለቀጣይ ተረጅነት የሚያጋልጥ ሲሆን፡ በሌላው መልኩም መንግሥት ጽንስ ማስወረድ በሕግ የሚያስቀጣ መሆኑ ቀርቶ የፈለገችው ዜጋ  ጽንስ ለማስወረድ ነጻ ነች፡ የሚል ውሳኔ በተመሳሳይ ጾታ መካከል ጋብቻ የመፍቀድ ሕግ ለማጽደቅ የሚከተለው ምርጫ የሚያሳዝን ብቻ ሳይሆን ቤተሰብ የሚጎዳ ነው። መንግሥት የሕዝብ መሠረታዊ ጥያቄ ማርካት የሚያስችል እቅድ መወጠ እንጂ የማስቀየስ ተግባር መፈጸም የለበትም ብለው ብሔርተኝነት የጎሳዊ የሃይማኖት ልዩነቶች የመሳሰሉ ችግሮች ሁሉ የአገር አንድነት የሚያናጉ ናቸውና እነዚህ ልዩነቶች በፖለቲካው ዘርፍ በመመልከት የአገረ አንድነት ዋስትና ማሰጠት ያስፈልጋል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.