2016-03-12 10:37:00

ቤተሰብ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።


ቅዱስ አባታች ፍራንቼስኮ ክርስቲያኖች በችግር ላይ የሚገኙትን ቤተሰቦች በጤና እና ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ ልጆቻቸውን ያሳድጉ ዘንድ እንዲረዱኋቸው  መማጸናችው ተገለጸ።

በስፓኒሽ ቋንቋ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክታቸው ቅዱስ አባታችን እንደገለጹት፣ የመጋቢት ወር የጸሎታቸው ትኩረት የሚሆነው ቤተሰብ ላይ መሆኑን ገልጸው፣ ማስተንተ የሚፈልጉትም “ቤተሰብ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው” በሚለው ጽንሰ-ሓስብ ላይ መሆኑንም አያይዘው ገልጸዋል።

ቤተሰብ በኢኮኖሚያዊ እና በጤና ወይም በሌላ ተመሳስይ ችግሮች ተጠቂ ስሆን፣ ልጆቻቸው ደስ በማያሰኝ ሁኔታ እንድያድጉ ስለሚገደዱ እና ለተለያዩ የማህበራዊ ቀውሶች ስለሚዳረጉ ይህ አስከፊ ጉዳይ ይቀረፍ ዘንድ በመጋቢት ወር ጸሎቴን ለእግዚኣብሔር በማቅረብ በችግር ላይ የሚገኙ ቤተሰቦች ሁሉ ተገቢውን ድጋፍ ያገኙ ዘንድ እና ልጆቻቸውን በአግባቡ፣ ሰላማዊ እና ጤናማ በሆነ መልኩ ያስድጉ ዘንድ በማድርገው ጥረት እናንተም ከእኔ ጋር በጸሎታችሁ እንድትተባበሩ ጥሪ አቀርባለው በማለት የቪዲዮ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.