2016-03-12 11:23:00

በሃይማኖት ነጻነት ላይ የተቃጣው እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በክርስቲያኖች ላይ እየተከሰተ ያለው አስከፊ ድርጊት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሱኋል።


በሃይማኖት ነጻነት ላይ የተቃጣው እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በክርስቲያኖች ላይ እየተከሰተ ያለው አስከፊ ድርጊት እንዳሳሰባቸው በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ተወካይ የሆኑት ብፁዕ አባ ሪቻርድ ጊያር  በመጋቢት 10,2016 በጄነቫ ትኩረቱን “ሐሳብን በነጸነት መግለጽ እና የሐይማኖት ነጻነት” በሚል አርዕስት በተጀመረው ስብሰባ ማስታወቃቸው ተገለጸ።

ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እና የሃይማኖት ነጻነት እንዲከበር የሚመለከታቸው የዓለም የፖሌቲካ ሀይሎች የራሳቸውን ድርሻ በሚገባ ባለመወጣታቸው ከፍተኛ የሆነ ብጥብጥ በተለያዩ የዓለማችን ክሎች እንዲበራከት አስተዋጾ ማድረጉም በስብሰባው ወቅት የተጠቀሰ ስሆን የሃይማኖት ነጻነት እና አሳብን በነጻ መግለጽ በጣም የተጣመሩ ጉዳዮች በመሆናቸው ትኩረት እንዲሰጠው በተባበሩት መንግሥታት የቅድስት መንበር ተወካይ የሆኑት ብፁዕ አባ ሪቻርድ ጊያር ለተሰብሳቢዎች አሳስበዋል።

ሃይማኖት በማህበረሰብ ውስጥ እያበረከት ያለውን ከፍተኛ አስተዋጾን መቀነስ ልችግሩ መፍትሄ ተደርጎ መውሰድ የለበትም ያሉት ብፁዕ አባ ሪቻርድ “ዓለማን  አንድ መንደር በማድረግ ወጥ የሆነ ስርዓት እናመጣለን  በሚል ፅንሰ ሐስብ ባነገቡ ጥቂት ሰዎች ምክንያት በዓለማችን የሚታዩ እንደ ውበት ልቆጠሩ የሚገባቸው የተለያዩ ባህሎች እና የተለያዩ እምነቶች፣ በተቀነባበረ መልኩ እንዲወገዱ እየተደርገ መሆኑ መጣም አሳሳቢ እና አስከፊ ጉዳይ መሆኑን ብፁዕ አባ ሪቻርድ ለተሰብሳቢዎች አሳውቀኋል።

በአንጻሩም ብዝኋነታችን የውበታችን መገለጫ ሊሆን የገባዋል ያሉት ብፁዕ አባ ሪቻርድ የሰውን ልጅ እንስከብራለን በሚል ሰበብ የሌላውን ሰው ህልውና መጋፋት ግን አስፈላጊ አለመሆኑን ገልጸው የሃይማኖት ነጻነት የሕሊና ነጻነትን ማስከበር እንደሆነ በመረዳት ሁሉም የሰው ልጆች በመከባበር እና በመፈቃቀር መኖር የምያስችላቸውን የማህበራዊ ሁኔታ መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።

የሃይማኖት ነጻነት ለማፈን የሚደረግ ዘመናዊ ጭቆና በተለያየ መልኩ እየተደረግ መሆኑንና ከንዚህም ጥረቶች መካከክል ስላም፣ መቻቻል፣ መከባበር በተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት መካከል እንድይኖር በማድረግ የሃይማኖት ተቋማትን ስም ማጉደፍ፣ በጭካኔ እና አረመንያዊ በሆነ መንገድ ጭምርም እርስ በእርሳቸው እንዲጋጩ በማድረግ፣ የሃይማኖት ተቋማትን ስም ለማጥፋት የሚደርገው እንቅስቃሴ መወገድ እንድለበትም አሳስበዋል።

የሃይማኖት ነጻነት እና ሐሳብን በነጻነት መግለጽ፣ የሰው ልጆች ሁሉ በሰላም እና በፍቅር እንዲኖሩ ወስኝ ነገር በመሆናቸው የሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች ሆነው ኣንዲቀጥሉ ቅድስት መንበር ትፈልጋለጽ ያሉት ብጽዕ አባ ሪቻርድ እያንዳንዱ ሰው የሌላውን መብት ባልተጋፋ መልኩ የእራሱን እምነት በነጻነት የመግለጽ መብቱ ሊጠበቅ እንደ ሚገባ አሳስበው በአንዱ በእግዚኣብሔር ስም መገዳደል አስነዋሪ ነገር መሆኑን በማመልከት በዚህ ዓይነት አስከፊ ድርጊት የተሰማሩ ሁሉ የሃይማኖትን ስም የምያጎድፍ አስቃቂ ድርጊትን ከመፈጸም እንዲታቀቡ አጋጣሚውን ተተቅመው አሳስበዋል።

በጨረሻም ሁላችንም የሃይማኖት ነጻነት እና ሐሳብን በነጻ የመግለጽ መብት እንዲከበር የበኩላችንን ጥረት ማድረግ ይጠበቅብናል ብለው አንዱ የሌላውን ሃይማኖት ሳያጎድፍ፣ በመከባበር ላይ የተመሰረት ማህብረሰብ በመፍጠር እና እንዲሁም እነዚህ ሁለት መሰረታዊ የሰው ልጆች መብቶች ገድብ እንዳልቸውም ጭምር በመረዳት ሁላችንም በአንድነት ለዓልም ሰላም እና ብልጽግና የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ይጠበቅብናል በማለት ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.