2016-03-08 14:39:00

የብፁዕ ካ. ብርሃነኢየሱስ የዓብይ ጾም መልዕክት "ካላችሁም ምግብ ለረሀብተኞች አካፍሉ መጠልያ የሌላቸውን ድኾች በቤታችሁ ተቀበሉ"


ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ ደምረው ሱራፍኤል ሊቀጳጳስ ዘ ካቶሊካዊያን ፣ የኢትዮጲያ ጳጳሳት ጉባሄ ፕረዝደንት እና የምስራቅ አፍሪካ የካቶሊክ ጳጳሳት ጉባሄዎች ህብረት ሊቀምንበር የ2008 ዓብይ ጾምን በማስመልከት ለመላው ካቶሊካዊያን እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ ባስተላለፉት መልዕክታቸው እንደ ገለጹት “ካላችሁም ምግብ ለረሀብተኞች አካፍሉ መጠልያ የሌላቸውን ድኾች በቤታችሁ ተቀበሉ የተራቆቱትን አልብሱ እርዳታችሁን ለሚፈልጉት ሰዎች ፊት አትንሱ” የሚለውን ከትንቢተ ኢሳያስ ከምዕራፍ 58, 7 ላይ ያለውን እግዚኣብሔር በነቢዩ ኢሳያስ በኩል የተናገርውን ቃል በመጥቀስ እና የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የጀመሩት ብፁዕ አባታችን ካርዲናል ብራሃነኢየሱስ ደምረው ሱራፌል “በቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቼስኮ በታወጀው ሊዩ የምሕረት ዓመት መሰረት የሁለት ሺ 8 ዓ.ም. የዓብይ ጾም ወራትን ልዩ በሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት እና ተግባር መጾም እናዳለብን ለመላው ካቶሊካዊያን እና በመንፍስ ልጆቻቸው ለሆኑት ሁሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የጾም ወራት ጥልቅ እምነት፣ ተጋድሎ እና ጸሎትን የሚጠይቅ ጊዜ ነው ያሉት ብፁዕ ካሪዲናል ብርሃነኢየሱስ “መንፈሳዊ ሕይወታችንን ቆም ብለን የምንፈትሽበት የፀጋ ጊዜም መሆኑን” አውስተው ጾም በዘልማድ ከቅባት አህሎች እና መጠጥ መታቀብ ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል” ነገር ግን ትክክለኛውን የጾም እሴቶችን ለመረዳት ከፈለግን በትንቢተ ኢሳያስ 58,1-12 የተጻፈውን እና ሓዋሪያው ፓውሎስ ወደ ገላቲያ በጻፈው መልዕክት ላይ “በጎ ሥራን መሥራት ቸል አንበል በጊዜው እናገኘዋለን እና ጊዜ ስላለን ለሁሉም መልካም ሥራን እንሥራ” (ገላ.6) የሚለውን ጠቅሰው “ጊዜ ወይም ዘመን በዓይን አይታይም ካለፈ ቡኋላ ግን መልካም ለሠሩት በደስታ ላልሠሩት ደግሞ በጸጸት ስለሚታወስ በዚህ የጾም ወቅት ምዕመናን ሕየውታቸውን እንዲመረምሩ እና ክፉን ነገር አውጥተው በመጣል ከአምላካችን ጋር ጥሩ የሆነ ግንኙነት መፍጠር መቻል ይጠበቅብናል ብለዋል።

የጾምን ጊዜን በአግባቡ መጠቀም ይኖርብናል ያሉት ብጹዕ አባታችን ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ፣ በጾም እና በምልጃ በሠራነው ክፉ ሥራ በመጸጸት ዳግመኛ ወደ ሓጥያት አልመለስም ብለን ቁርጥ ፍቃድ የምናደርግበትም ወቅት ሊሆን እንደሚገባም አመልክተው የሰው ልጅ መምድራዊ ሕይወቱ በልቶ፣ ጠጥቶ፣ አጊጦ እና ተደስቶ መኖሩ መልካም ነገር ነው ነገር ግን ቀዳሚው ጉዳይ መሆን የሚገባው እግዚኣብሔርን ማወቅ፣ ለፍቃዱ መገዛት እና እንዲሁም ከሰው ልጆች ሁሉ ጋር በሰላም፣ በፍቅር፣ በመተሳሰብ እና በመረዳዳት እንዲሁም አንድነትን ከግምት ባስገባ መልኩ መኖር ቀዳሚው ተግባር ሊሆን የገባል ብለዋል።

በዚህ የጾም ወቅት በሃገራችን በአየር መዛባት ምክንያት በተከሰተው ድርቅ የተጎዱ ወንድም እና እህቶቻችንን ማሰብ እንደሚገባ አውስተው የእነርሱ ችግር የኛም ችግር መሆኑን በመረዳት በጸሎት ከማሰብ ባሻገር አቅማችን በፈቀደ መጠን ቁሳዊ የሆነ ድጋፍም ማድረግ የጠበቅብናል ብለዋል።

በተለያየ ዓየነት የወንጀል ድርጊት የተሰማሩ ሰዎች ሁሉ የወንጀል ተግባራቸውን አሰውግደው ሓጥያትን ቢጠላም ሓጥያተኛውን ግን ወደ ማይጠላው እግዚኣብሔር እና ወደ መልካም ጎዳና እንዲመልሱ ጥሪ የሚያቀርበውን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ መልዕክት ላይ ተመርኩዘው የተማጽኖ ጥሪ ያቀረቡት ብጹዕ ካርዲናል ብርሃነኢየሱስ የሰው ልጅ ሕይወት የሚለካው ባካበትነው ገንዘብ አለመሆኑ በመግለጽ እና በምንሞትበት ወቅትም ከገንዘብ ጋር እንደማንቀበር አማልክተው ሀብትን ለማካበት ሲባል በደም እና በአመጽ የተነከረ ገንዘብ አንድን ሰው የማይሞት ሀይል  እንደማያደርገው በመረዳት  ዛሬም ሆነ ነገ ሁላችንም ከማናምልጠው የእግዚኣብሔር ፍርድ ፊት እንደ ምንቀርብ መረሳት የለበትም ብለዋል።

በሙስና የተዘፈቁ ሰዎች ሁሉ ሙስና ትልቅ ሓጥያት መሆኑን እና የግል እንድሁም የማህበራዊ ኑሮን እንደ ሚያዛባ ተገንዝበው በተጨማሪም ሙስና ልብን በሓጥያት ማደንደን መሆኑን በመረዳት የጨለማ ሥራ የሆነውን ሙስና ነቅቶ በመጠበቅ እና በልክ በመኖር እንድንዋጋው አሳስበው ታማኝነት እና ግልፅነትን በመፍጠር  ጥፋቶችን በሕብረት ማውገዝ ይገባናል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮስ በዚህ የምህረት ዓመት ያቀረቡልን ጥሪ እንድምያመለክተው አንድ ሰው እግዚኣብሔር እንዲታደስ ያቀረበለትን ጥሪ በመቀበል ወደ ፍታዊ ተግባር መመለስ ይጠበቅበታል ያሉትን በድጋሜ በማስታወስ ልዩነታችንን ሁሉ በውይይት እየፈታን ልብ ለልብ ይቅር እየተባባልን ስለ ሀገራችን ሰላም እና ብልጽግና በጋራ መስራት እንደሚጠበቅብን አሳስበው ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።  

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.