2016-03-08 09:49:00

በሕዳር 5.2016 በየመን የወደብ ከተማ ሄደን 4 የእማሆይ ትሬዛ ማህበር አባል የሆኑ ደናግላን እና ተጨማሪ 12 ሰዎች ተገደሉ


ባለፈ ቅዳሜ ማለትም እንደ አውሮፓዊያን የዘመን አቆጣጠር በሕዳር 5.2016 በየመን የወደብ ከተማ ሄደን የተገደሉ 4 የእማሆይ ትሬዛ ማህበር አባል የሆኑ ደናግላን ጉዳይ የዓልምን ትኩረት ያልሳበ ወቅታዊ ዜና ቢሆንም ቅዱስ ወንጌላችን የሚያዘውን መልካም አገልግሎት በመፈጸም  እግዚአብሔርን በተግባር የመሰከሩ በመሆናቸው በእኛ ዘመን የተሰው ሰማዕታት መሆናቸውን ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ አስታወቁ።

 

በህዳር 6,2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሳማንታዊው የጠቅላላ አስተምሮ ለተገኙ በሺ ለሚቆጠሩ ምዕመናን እና ሀገር ጎብኚዎች ቅዱስ አባታችን እንደ ገለጹት “በዓለማችን የሚታየው ቸልተኝነት ወይም የምን አገባኝ መንፈስ፣ ጦርነት እንዲፋፋም አስተውጾ አድርጕኋል ብለው ለሰላም እና ለይቅርታ ሕይወታቸውን እስከመስጠት የደረሱ እንዚህ ሰማዕታት፣ በዓለማቀፍ መድረክ፣ ጉዳዩ እንደ ዋና ዜና ተወስዶ በተለያዩ የዜና አውታሮች እና በጋዜጦች የመጀመሪያ ገጽ ላይ ድርጊቱ ባይዘገብም፣ በዚህ  አረሜንያዊ ድርጊት ሕይወታቸውን ያጡት 4 ደነግላን ባለንበት ወቅት የወንጌል አስተምሮን በተግብር በሕይወታቸው በማሳየታቸው ምክንያት ብቻ በመገደላቸው እንደ ሰማዕታት እንደ ሚቆጠሩ ገልጸው ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።

እነዚህ 4 ደናግላን ደማቸውን ለቤተ ክርስቲያናቸው አገልግሎት  መስማዕት አድርገዋል በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባትችን ፍራንቼስኮ ለነዚህ ሰማዕታት ሕያወት ተጠያቂ የሚሆኑት አረሜንያዊ በመሆነ መልኩ የገደልኋቸው አሸባሪዎች እና እንዲሁም በየመን ለሚታየው ብጥብጥ አጥጋቢ የሆነ መልስ ያልሰጠው የዓለማቀፍ ምህበረሰብ ጭምር መሆኑን ገልጸው የነዚህን ሰማዕታት ነብስ በገነት ያኖሩ ዘንድ እና ለዚያ ሀገር ሰላም እና ለሰው ልጅ ሕይወት ሁሉ ክብር ይሰጥ ዘንድ በቅድስት እማሆይ ትሬዛ አማላጅነት እንለምናለን ብለዋል።

በዚህ አጋጣሚ በተለያዩ የዓለማች ክፍሎች የሚካሄደውን ጦርነትን ሸሽተው በኢጣሊያ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሚገኙ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች፣ መበለቶች እና አቅመ ደካማ ለሆኑት አዛውንት ስደተኞች የሚደረገው የተቀናጄ ድጋፍ በጣም አስደሳች ነው ብለው በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።

ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 15 የተወሰደው እና ጠፍቶ ስለተገኘው ልጅ በሚገለጸው ታሪክ ላይ ተመስርተው ቅዱስ አባታችን እንዳሳሰቡት ከክፉ ሥራችን እንድንመለስ እግዚአብሔር ሁል ጊዜ እጁን ዘርጎቶ እንድሚጠብቀን ገልጸው ጠፍቶ ከተገኘው ልጅ በተሻለ ሁኔት አባቱ ይቅር ባይ እና ታጋሽ ሆኖ መገኘቱ የሚያሳየው እግዚኣብሔርም እኛን ልጆቹን በምንሳሳትበት ወቅት ሁሉ በትዕግስት ተመልሰን ወደ እርሱ እስክንመጣ ድረስ እንድሚጠባበቀን እና በምሕረቱ አቅፎ ይቅር እንደሚለን በመሆኑ ለፍቅሩ ታማኝ ወደ ሆነው እግዚኣብሔር ክፉ እና አረመኔኋዊ የሆኑትን ተግባራት ትተን ሰላም እና እርካታን ወደ ሚሰጠን እግዚኣብሔር መመለስ ይጠበቅብናል ብለኋል።

በተጨማሪም በየመን የወደብ ከተማ ኤደን የተገደሉ 16 ሰዎች መሆናቸውን የአይን እማኞችን ዋቢ በማድርገ የገለጸው አሶሼትድ ፕረስ ከተገደሉት ሰዎች ውስጥ 1 የህንድ፣ 2 የሩዋንዳ፣ 1 ኬንያዊ  ደናግል እንደ ሚገኙበት ጠቅሶ በተጨማሪም 6 ኢትዮጲያዊያን፣ የተቀሩት ደግሞ የመናዊያን እንደ ሆኑ ገልጾ ሁሉም የተገደሉት እጃቸውን የኋልዮሽ ታስረው በጥይት ጭንቅላታቸን ተመተው መሆኑን አስታውቅኋል።

የቅድስት እማሆይ ትሬዛ ማህበር የሆኑት ደናግላን ከ80 በላይ በላይ ለሚሆኑ በኤደን ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን እ.አ. የዘመን አቆጣጠር በ1998 በቀይ ባሕር የወደብ በምተገኘው ሆዴይዳ በምታባል ከተማ ታጣቂቆች በከፈቱት ተኩስ በተመሳስይ መልኩ 3 የእማሆይ ትሬዛ ደናግላን በጥይት ተመተው መሞታቸው የሚታወስ ሲሆን ቅደም ባለውም ጊዜም በዚህቹ በኤደን ከተማ የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ጥቃት እንደ ደረሰባቸው የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡም አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በነዚሁ አክራሪ የሙስሊም ታጣቂዎች ተቃጥሎ መውደሙ የሚታወቅ ነው። የእማሆይ ትሬዛ ማህበር እ.አ. በ1950 የተመሰረት ስሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ከ4500 በላይ ደናግላን የሚገኙበት ማሕበር ሲሆን በ122 ሀገራት ወስጥ የተለያይ ዓይነት አገልግሎቶችን በተለይም ለድኾች፣ ወላጅ አልባ ለሆኑ ሕጻናት እና አቅመ ደካማ ለሆኑ የምህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል። 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.