2016-03-05 16:18:00

ብፁዕ ካርዲናል ኦለት፥ በማኅበራዊ ሕይወት የካቶሊካውያን ምእመናን ቍርጠኛ ተሳትፎ


በአገረ ቫቲካን ሲካሄድ የሰነበተው የላቲን አመሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በማህበራዊ ሕይወት ላይ የምእመናን ቍርጠኛ ተሳትፎ" ርእስ ዙሪያ የመከረው ይፋዊ ምሉእ ጉባኤ እ.ኤ.አ. መጋቢት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. ተጋባእያኑ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር በመገናኘት መሪ ቃል ተቀብለው መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገልጠዋል፡

የዚህ ጳጳሳዊ ድርገት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦለት ጉባኤው በተወያበት ርእስ ዙሪያ ባስደመጡት ንግግር፥ በቅድሚያ የማወያያው ርእስ በላቲን አመሪካ አገሮች እጅግ አንገብጋነት ያለው እርሱም በማኅበራዊ ሕይወት የምእመናን የተሳታፊነተ እጥረት መሆኑ ግምት በመስጠት ይኽንን ጉዳይ በግብረ ኖልዎ ገጥሞ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ መሆኑ በመገንዘብ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሰጡት ሃሳብ በመከተል መሆኑ አስታውሰው፡

ፖለቲካ በፍትህ አማካኝነት ዜጎችን ለመምራት ያዛል። በዚህ የፖለቲካው ኃላፍነት ዘርፍ ካቶሊክ ምእመን በቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት በመመራት በነጻነታ በኃላፊነት መወጣት ይኖበታል እዳሉ የገለጡት የቫቲካን ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው ብፁዓን ጳጳሳት በማንኛውም ዓይነት መንገድ በፖለቲካዊ ርእዮተ ዓለም ሳይጠፈሩ ጥሪያቸው የሥልጣን ጥሪ አለ መሆኑ ተገንዝበው የማዳን እቅድ ለፖለቲካው ዓለም እንዳያወክፉ አደራ፡ ስለዚህ በፖለቲካው ዓለም ቀንደኛ ተወናያን መሆኑ እንደማይገባቸው አሳስበው፡ እንዲህ ሲባልም ከማኅበራዊ ሕይወትና ከፍትኃ ነገሮች ሁሉ ተገለው ሰብኣዊነት ያረጋገጠ ኅብረተሰብ በመገንባቱ ሂደት ገንቢ አስተዋጽኦ ከመስጠት ይቆጠቡ ማለት እንዳልሆነ ማብራራታቸው አስታውቀዋል።

ይኽ የላቲን አመሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገት ከመላ የላቲን አመሪካና ካሪቢያን አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በተለያየ ክልላዊ ብሔራዊ መሥተዳድር በፖለቲካው ዓለም የሚያገለግሉ ምእመናን ያሳተፈ ዓውደ ጉባኤ ለማካሄድ እቅድ እንዳለ የገለጡት ብፁዕ ካርዲናል ኦለት አክለው፥ እየተኖረ ያለው የምኅረት ዓመት ምእመናን በተሰማሩበት ዘርፍ ሁሉ በቃልና በሕይወት ምኅረት መመስከር ያለው አጣዳፊነት የሚያስገነዝብ ነው ካሉ በኋላ በመጨረሻም ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታትና የካናዳ ብፁዓ ጳጳሳት ጋር በመተባበር በዚህ የምኅረት ዓመት የላቲን አመሪካ ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ድርገትና የመላ ላቲን አመሪካና ካራይቢ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በጋራ እ.ኤ.አ. ከነሓሴ 27 እስከ ነሓሴ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቅ በኮሎምቢያ ርእሰ ከተማ ቦጎታ የምኅረት ዓመት በክፍለ ዓለማዊ ደረጃ እንደሚከበርም መግለጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.