2016-03-03 14:06:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ከሞስኮና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ክርል በጋር ያወጡት ባለ30 አንቀጽ የጋራ መግለጫ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ከሞስኮና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ክርል በጋር ያወጡት ባለ30 አንቀጽ የጋራ መግለጫ።

“የጌታች የኢየሱስ ፀጋ የእግዚአብሔር ፍቅር እና የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችሁም ጋር ይሁን”። (2ቆሮ 13፡14)

  1. የመልካም ስጦታዎች ሁሉ መንጭ በሆነው በእግዚአብሔር አብ ፈቃድ፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና አጽናኝ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ስም እኛ ማለትም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ እና የሞስኮ እና የመላው ሩስያ ፓትርያርክ ክርል፣ በዛሬው እለት (የካቲት 13.2016) በሀቫና ተገናኝተናል። በቅድስት ስላሴ ወስጥ ለከበረው እግዚአብሔር ስለዝህ ታሪካዊ ግንኙነት ምስጋናን እያቀርባለን።በክርስትና እመንታችን ምክንያት ወንድማማቾች የሆንን እኛ ዛሬ “ፊት ለፊት” (2 ዩሓ. 12) ተገናኝተን ከልብ የመነጨ የጋራ ውይይት በማድረግ፣ በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከከል ያለውን ግንኙነት እና ዋና ዋና ችግሮችን ለመወያየት፣ እንዲሁም የሰው ልጅ ስልጣኔ በወደፊቱ የዓልም ሁኔታ ላይ እያመጣ ያለውን ተጽኖ ለመገምገም በመብቃታችን ከፍተኛ የሆነ ደስታ ተስመቶናል።
  2. ይህ ወንድማማቸንት የተላበሰው ውይይታችን የተካሄደው የሰሜንና የደቡብ፣ የምስራቅና የምዕራብ መገናኛ በሆነችው ኩባ ነው። ከዚህች ደሴት ነው የወደፊቱ “አዲስ ዓለም” የተሰፋ ተምሳሌት የሆነውና አስገራሚው የሃያኛ ክፍለ ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት ለላቲን አሜርካ ሀገራት እና ለቀሪውም አሀጉር የተነገረው። የክርስትና እማነት በዚህ አሀጉር አስገራሚ በሆነ ሁኔታ እያደገ በመምጣቱ ደስታ ተሰምቶናል። በላቲን አሜሪካ የሚታየው ጠንካራ የክርስትና እምነት መስፋፋትና ምዕተ አመት ያስቆጠረው የክርስትና ባህል፣ በሚልዮን የሚቆጠር ሕዝብ ውስጥ ያሰረጸው የክርስትና መንፈስ ለዚህ አከባቢ መጭው ትውልድ ስንቅ የሚሆን ነው።
  3. “ቀደም ባለው ጊዜ” የተከሰተውንና ለረጅም ጊዜ ከቆየው ክርክር የተረዳነው አፋጣኝ በሆነ መልኩ የካቶሊክ እና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት በጥንቃቄ እና በመከባበር ላይ በተመሰረት መልኩ እንድናከናውን ለተጠራንበት ጥሪ በጋራ  በመሥራት ተስፋ ለጣለብን ዓለም አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት እንደ ምጠበቅብን ነው (1ጴጥ. 3፡15)።
  4. አንደኛ ልጁን በመላክ ፀጋውን እንድንካፈል የረዳንን እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። አንድ ዓይነት የሆነ የመጀመሪያው ምህተ ዓመት መንፈሳዊ ባህል ተካፋዮችም ነን። ለዚህም የጋራ መንፈሳዊ ባህል የእግዚአብሔር እናት የሆነችው ቅድስት ድንግል ማሪያምና የምናከብራቸው ቅዱሳን ምስክሮች ናቸው። ከእነዚህም መሀል ለቁጥር የምያዳግቱ ለክርስቶስ ምስክርነት አራሳቸውን አሳልፈው የሰጡና “የክርስትናን እምነት ዘር” የዘሩ ሰማዕት ይገኛሉ።
  5. ምንም እንኳኋን በጋራ የምንካፈላቸው መንፈሳዊ ባህሎች ቢኖሩንም ላለፉት ዓሥርተ ዓመታት ብያንስ ለአንድ ሺ ዓመታት ያህል ኮቶሊክ እና ኦርቶዶክስ ቅዱስ ቁርባንን በተመለከተ ያላቸው አመለካከት እንደስፋ ቆይቱዋል። ይህም ልዩነት ሊከሰት የቻለው ቀደም ባለውና በአሁኑም ጊዜ  ከአባቶቻችን በወረስናቸው አመለካከቶች እና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት የምንገልጽበት መንገድ ልዩ ሆኖ በመቆየቱና፣ እግዚአብሔር አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ አንድም ሦስትም ናቸው የሚሉት የእምነት አገላለጾች የታሪክ ጠባሳዎችን እና ግጭቶች ጥለው አልፈዋል። ጌታችን እና አዳኛችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክህነታዊ ጸሎቱ “አባት ሆይ አንተ በእኔ እኔም ባንተ እንዳለው ሁሉም አንድ እንዲሆኑ…እኛ አንድ እንደሆንን እነርሱም አንድ ይሆኑ ዘንድ…” (ዩሓ 17፣21) ብሎ የጸለየውን ጸሎት፣ በሰው ድክመት እና ሐጥያት ምክንያት ችላ በማለታችን ምክንያት የተፈጠረው ልዩነት ክፍተኛ ጉዳት አድርሶብናል።
  6. በቋሚነት የሚኖሩ እንቅፋቶች እንዳሉ ከግንዛቤ በማስገባት፣ የዛሬ ስብሰባችን ክርስቶስ የፈለገውን አንድነት ለማምጣት በእግዚአብሔር እየተመራን ወደ ቀድሞ አንድነታችን እንድንመለስ ከፍተኛ አስተዋጾ እንድምያደርግ ተስፋ አለን። ይህም የእኛ ስብሰባ በዓለም ውስጥ የሚገኙትን ክርስትያኖች ሁሉ፣ የክርስቶስ ሓዋሪያት የሆኑትንም ጭምር በቁዋሚነት አንድ እንዲሆኑ ይጸልዩ ዘንድ እንደምያነሳሳቸው ተስፋ እናደርጋለን።  ይህ በቃላት ብቻ የተገለጸ ሳይሆን በተጨባጭ ምልክቶች የተጀበ ስብሰባችን መልካም ፈቃድ ላላቸው ሰዎች ሁሉ የተስፋ ምልክት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።
  7. ስወርድ ሲዋረድ የመጣው ታሪካዊ ልዩንታችንን ለማስወገድ መወሰናችን የምያሳየው፣ በተቀናጀ መልኩ የክርስቶስን ወንጌል ለመመስከርና ከመከፋፈላችን በፊት የነበሩንን የመጀመሪያዎቹን የጋር ክርስቲያን እሴቶችን በማጠናከር አሁን እኛ ባለንበት ዓለም ለሚታዩ ችግሮች በጋራ መልስ ለምስጠት ነው። ኦርቶዶክስ እና ካቶሊኮች መገንዘብ የሚገባቸው ነገር በአንድ ድምጽ ለዓለም ችግሮች ምስክረነት መስጠት እንደሚቻል እና አስፈላጊ መሆኑን ነው። የሰው ልጅ ስልጣኔ  አዲስ ታሪካዊ የለውጥ ምዕራፍ ከፍቱኋል። ክርስቲያናዊ መሰረት ያለው ህሊናችን እና ሐዋሪያዊ አላፊነታችን፣ የሚታዮትን ችግሮች በቸለተኝነት እንዳንመለከታቸው እና በጋራ መልስ መስጠት እንዳለብን ያስገድደናል።
  8. በቅድሚያ እይታችን ማትኮር የሚገባው ለስደት ተጋላጭ የሆኑ ክርስትያኖች የሚገኙበት አከባቢ መሆን ይኖርበታል። በብዙ የመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍርካ የሚገኙ በክርስቶስ ወንድማማቾች እና እህታማቾች የሆኑ ቤተሰቦች፣ መንደሮችና ከተሞች ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ይታወቃል። ቤተ ክርስቲያናቸው አረመንያዊ በሆነ መልኩ ተቃጥሎ ጠፍተዋል፣ ቅዱሳን ነገሮቻቸው ረክሰዋኋል፣ የተደቀሱ ሀውልቶቻቸው ወድመዋኋል። አሰቃቂ የሆነውና ትኩረት እንዲ ሰጠው የምፈልገው የሶሪያ፣ የኢራቅ እና የሌሎች በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙት ሀገሮች ጉዳይ እና ከሐዋርያት ጊዜ ጀምረው ጠብቀውት የኖሩትን የክርስትና ማህበራት በተጨማሪም የክርስትና እምነታችን መፍለቅያ ከነበረው አከባቢ እየተከሰት ያለው ከፍተኛ የሆነ የክርስቲያኖች ስደት በጥም ያሳስቦናል።
  9. የዓለማቀፍ ማሕበረስብ ይህንን ክርስቲያኖችን ከመካከለኛው ምስራቅ ያማጥፋት ዘመቻ  በአስቸኳይ እንድያስቆም ጥሪ እናቀርባል። ድምጻችንን በስደት ላይ ለሚገኙ ክርስትያኖች በምናነሳበት በአሁኑ ወቅት፣ በተመሳሳይ ስቃይ ወስጥ እያለፉና ለእርስ በእርስ ጦርነት፣ በመከራ እና ለአሸባሪዎች ጥቃት ለተጋለጡ የሌሎች እምነት ተከታዮችም ጭምር የተሰማንን ላባዊ ሀዘን መግለጽ እንወዳለን።
  10. በሶሪያ እና በኢራቅ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውና በሚልዮን የሚቆጠሩ ደግሞ ቤት አልባ በመሆን ለመኖር አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ። የዓለማቀፍ ማሕበረሰብ እየተከሰተ ያለውን ብጥብጥ እና አሸባሪነትን እንድያስቆም እየጠየቅን፣ በውይይት ላይ የተመሰረት መግባባት በመፍጠር ወደ ሰላም እንዲመለሱ ጥረት እንዲያደርጉም እንጠይቃለን። ከፍተኛ የሆነ ሰባዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እና ሰላምን ፍለጋ በጎረቤት ሀገራት ለተጠለሉት የማሕበረሰብ ክፍሎች አፋጣኝ እና በቂ እርዳታ እንዲደረግላቸው እንጠይቃለን። የታገቱ ሰዎች ሁሉ በሚያዝያ ወር 2013 የታገቱት የአሌፖ ከንቲባ የነበሩት ፖልና ጆን ኢብራህም ጭምር እንዲለቀቁ እና በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚገኙ ተጽኖ መፍጠር ለሚችሉ መንግስታት ሁሉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
  11. የመካከለኛው ምስራቅ ያጣውን ሰላም መልሶ ያገኝ ዘንድ ፀሎታችንን የዓለም አዳኝ ወደ ሆነው ክርስቶስ እያቀረብን  “የጽድቅ ፍሬ” (ኢሳ. 35:17) ከተለያዩ የሕበረተሰብ ክፍሎች ጋር በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ አብሮ መኖር እንዲፈጠር ፣ ቤተክርስቲያን እና እምነቶች ተመልሰው እንዲጠናከሩ፣ ስደተኞች ወደ የሀገራቸው እንዲመለሱ፣ የቆሰሉት እንዲፈወሱና ሕይወታቸውን ያጡ ንጹሓን ሰዎች ሁሉ ነብሳቸው በሰላም እንድያርፍ እንማጸናለን። በዚህ ብጥብጥ የተሳተፉት ሁሉ በጠረጴዛ ዙርያ ተሰብስበው ለመወያየት ፋቃደኛነታቸውን ያሳዩ ዘንድ ከልብ እንማጸናለን። በተመሳሳይ መልኩ የዓለማቀፍ ማሕበረሰብ አሸባሪነት ማብቅያ ያገኝ ዘንድ የተቀናጀ የጋራ ጥረት እንያደርጉም እንጠይቃለን። በጸረ-ሽብር የተሳተፉ ሀገሮች ሁሉ ሀላፊነት በተሞላው መልኩ እና በጥንቃቄ ተጋባራቸውን ሊፈጽሙ ይገባል። ክርስቲያኖች እና ማንኛውም በእግዚአብሔር የምያምን ሰው ሁሉ የዓለም ፈጣሪ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ፍጥረትን ሁሉ ከጥፋት ይታደግ ዘንድ እና አዲስ የአለም ጦርነት እንዳይከሰት እንድጸልዩ ከልብ እንማጸናለን። ተጨባጭና ዘላቂ የሆነ ሰላምን ለማምጣት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ላይ የተመሰረት አንድ ያምያደርጉንን እሴቶችን መለየት  ይኖርበናል።
  12. ክርስቶስን ከመካድ ይልቅ ሞትን የመረጡ እና የወንጌልን እውነተኛነት በደማቸው ለመሰከሩ ሰማዕታት ከፍተኛ ክብር እንሰጣለን። እነዚህ ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያንት የተውጣጡ ነገር ግን ሁሉም የአንድ መከራ ገፈት ቀማሽ የሆኑ፣ በእኛ ጊዜ የተሰው ሰማዕት ክርስትያኖች ሕብረት እንድንፈጥ አደራ ይሉናል። ለክርስቶስ ብላችው መከራን እያያችው ላላችሁ ሁሉ ሓዋሪያው እንድህ ይላል፣ “ወዳጆች ሆይ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ በመቀበላችሁ እንግዳ ነገረ እንደደረሰባችሁ በመቁጠር አትደነቁ፤ ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጌዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋይ በመሆናቸው ደስ ይበላችሁ” (1ጴጥ. 4:12-13)።
  13. በነውጥ እየታመሰ የሚገኘው እኛ የምንገኝበት ወቅት በሐይማኖት ተቋማት መካከል ውይይት መደረግ እናዳለበት ያሳስበናል። በተለያዩ የሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚንጸባረቁት ሐይማኖታዊ እውነታዎች፣ አመለካከቶች እና ልዩነቶች የተለያየ ሐይማኖት የያዙ የማሕበረሰብ ክፍሎች በሰላም እና በአንድነት እንዳይኖሩ ማድረግ የለበትም። አሁን ባለንበት ሁኔታ የሁሉም የሐይማኖት መሪዎች ምዕመናኖቻቸውን የሌላውን አማኝ መንፈሳዊ እሴት ያከብሩ ዘንድ የማስተማር አላፊነት አለባቸው። ሐይማኖታዊ መፈክሮችን አንግቦ ወንጀልን መፈጽም ተቀባይነት የለውም። “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አማልክ አይደለም” (1ቆሮ 14:33)። ስለዝህ ምንም ዓይነተ ወንጀል በአንዱ በእግዚአብሔር ስም መፈጸም የለበትም።
  14. በመጀመርያ ደረጃ ለሐይማኖት ነጻናት ከፈተኛ ቦታ እንደምንሰጥ እያሳውቅን፣ በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ ለአስሥርተ -ዓመታት ሕይማኖት አልባ በሆኑ መንግስታት ይመሩ የነብሩ የሩስያና የተለያዩ የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት ማህበረሰብ ውስጥ የክርስቲያን ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ለእግዚአብሔር ምስጋናን እናቀርባለን። ዛሬ የሐይማኖት አልባ ሰራዊት በመደምሰሱ በብዙ ቦታዎች ክርስቲያኖች እማነታቸውን በነፃነት ለመግለጽ ችለዋል። ካለፉት ሃያ አምስት አመታት ወዲህ በሺ የሚቆጠሩ አዳዲስ አብያተ ክርስቲያናት ተገንብተው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ገዳማትና የሐይማኖታዊ ትምህርት መስጫ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። የክርስቲያን ማህበረሰብ ተጠቃሽ የሆኑ የተለያዩ የእርዳታ መስጫ ተቋማትን እና የማህበራዊ እደገት ተቋማትን በመክፈት የተለያዩ አገልግሎቶችን ለተቸገሩ ሰዎች እያቀረቡ ይገኛሉ። ኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ በአንድነት ስራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ።በጋራ የተሰጣቸውን የወንጌልን አስተምሮ እየመሰከሩ የሐይማኖታቸው መሰረት የሆነውን አብሮ መኖርን እየተገበሩ ይገኛሉ።
  15. በተመሳሳይ መልኩ በብዙ ሀገራት ክርስቲያኖች እምነታቸውን በነፃነት መግለጽ እዳይችሉ መሰናክሎች እየተደቀኑባቸው እና ያመኑበትን ነገረ በተግባር መመስከር እንዳይችሉ እየተደረጉ  መሆኑ በጣም አሳስቦናል። አንድ አንድ ሀገራት ለየት ባለ ሁኔታ ክርስቲያናዊ እሴቶችን በማስወገድ፣ ከክርስቲያናዊ ወደ ዓለማዊ ማህበረሰብ እየተቀየሩ መጣታቸውንና እግዚአብሔርን እና የእርሱን እውነት መመርኮዝ እያቆሙ መምጣታቸው ከፍተኛ የሆነ ስጋትን በሐይማኖት ነጻነት ላይ ደንቅሩዋል። በአሁኑ ጊዜ በክርስቲያኖች ላይ በአንድ አንድ ጠንካራ ዓለማዊ ርዮተ ዓለም በሚያራምዱ ሰዎች የተመሩ የፖለቲካ ሃይሎች ምክንያት ክርስቲያኖች ከፍተኛ የሆነ መገለል እየደረሰባቸው መሆኑም አሳስቦናል።
  16. ከብዙ ደም አፋሳሽ ግጭቶች ቡኋላ የተፈጠረው የአውሮፓ ሕብረት በብዙዎቹ ዘንድ ሰላምንና ደህንነትን አንደሚያረጋግጥ ተስፋ የተጣለበት ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ሕብረት የሐይማኖት ህልውና ላይ አደጋ እንዳይፈጥር ነቅተን መጠበቅ አለብን። ምንም እንኳን ሌሎች የሃይማኖት ተቋማት ለአውሮፓ ስልጣኔ የበኩላቸውን አስተውጾ አንዳደርጉ ብናውቅም አውሮፓ ስር መሰረቷ ለሆነው የክርስቲያን አምነት ታማኝ ሆና መኖር ይኖርበታል። ለምስራቅ እና ለምዕራብ አውሮፓ ሀገራት ክርስቲያኖች  የምናቀርበ ጥሪ ቢኖር፣ ክርስቶስን እና የእርሱን ወንጌል መመስከር የምንጋራቸው የክርስቲያን እሴቶች በመሆናቸው፣  የሁለት ሺ ዓመት ባሕል ያለውን አንኳር የሆነውን የክርቲያንዊ እሴቶችን አውሮፓ ጠብቆ መቆየት አንዲችል በጋራ መስራት ይጠበቅበናል።
  17. ዓለም በኢኮኖሚ እያደገ በመጣበት በአሁኑ ወቅት በከፍተኝ ችግርና ድኽነት የሚሰቃዩ ወገኖች ትኩረት አንዲሰጣቸው አንሻለን። የሀብታም ሀገራትን በር እያንኳኩ ለሚገኙ ጥገኝነት ጠያቂዎች እና ስደተኞች ጥሪ፣ ችላ ሊባብል አይገባውም። እያደገ የመጣው “በቃኝ የማያውቀው” በኢኮኖሚ ያደጉ ሀገሮች ፍጆታ፣ ቀስ በቀስ የዓለማችንን ሀብት አያሟጠጠ ይገኛል። እያደገ የመጣው ፍታዊ ያልሆነው የኢኮኖሚ ክፍፍል የሚያሳየው፣ ፍታሀዊ ያልሆነ ዓለማቀፋዊ ስረዓት እያደገ መምጣቱን ነው።
  18. የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት የተጠሩት፣ ፍትህ አንዲሰፍን፣ የሕዝቡ ባህላዊ እሴቶች አንዲከበሩ እና በችግር ለሚሰቃዩ ሰዎች ሁሉ እውነተኛ ወንድማዊ አጋርነት አንዲኖር ጥሪ ለማቅረብ ነው። እኛ ክርስቲያኖች ማወቅ ያለብን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገረ መረጠ፣ እግዚአብሔር ሞኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ። እግዚአብሔር የተከበረውን  አንደሌለ ለማድረግ፣ በዚህ አለም ዝቅ ያለውንና የተናቀውን ነገር ቦታም ያልተሰጠውን ነገር መረጠ፣ ይሄውም ማንም ሰው በእርሱ ፊት አንዳይመካ ነው። (1ቆሮ 1,27-29)
  19. ቤተሰብ ተፈጥሮአዊ የሰው ልጅና የማሕበረሰብ ማህከል ነው። በብዙ ሀገሮች በቤተሰብ ህልውና ላይ የተደነቀረው አደጋ በጣም አሳስቦናል። የኦርቶዶክስና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያናት ተመሳሳይ የሆነ የቤተሰብ አሰተምሮ ስለሚጋሩ በጥንዶች መካከል በመተማመን ላይ የተመሰረት ግንኙነት አንዲኖር፣ ዘር አንዲተኩና ልጆቻቸውንም ስርዓት ባለው መልኩ አንድያሳድጉ፣ በሰው ልጆች መሀል ወንድማማችነት እንዲሰፍን እና አነስተኛ ተደርገው የሚቆጠሩትን ሁሉ አንድያከብሩ  እነዚህን የተቀደሱ አላማዎች ለመመስከር በጋራ ተጠርተዋል።
  20. ቤተሰብ የሚመሰረተው በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መካከል፣  ያለማምን አስገዳጅነት በነጻና ታማኝ በሆነ ፍቀር ላይ በተመሰረት ጋብቻ ነው። ሕብረታቸውን የሚያጠናክርና አንዱ ለአንዱ የተሰጠ ስጦታ ሆኖ እንዲሰማቸው የሚያደረገው በመካከላቸው ያለ ፍቅር ነው።  በተመሳስይ መልኩ የተቀደስውንና በመጻሐፍ ቅዱሳችን የተጠቀሰውን በጋብቻ ውስጥ ሊንጸባረቅ የሚገባው አባትነት እና እናትነት፣ በተለየ መልኩ ለወንድና ለሴት የተሰጠ ጥሪ መሆኑ ከብዙሀኑ አህምሮ እየተፋቀ መምጣቱና አብሮ መኖር ልክ እንደ ጋብቻ እየተቆጠር መምጣቱ አሳዝኖናል።
  21. መተክያ ለሌለው ለሰው ልጅ ሕይወት ትኩረት እንዲሰጠው ጥሪ እናደርጋለን። በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ተወልደው ዓለምን የመቀላቀል መብታቸውን እየተነፈጉ ይገኛሉ።  ያልተወለዱ ሕጻናት ደም ወደ እግዜብሔር ይጮሃል (ኦ. ዘፍ. 4,10)። እየጨመረ የመጣው ስቃይ የበዛባቸው እና የማይድኑ ሰዎችን ለማሳረፈ የሚደረግ ግድያ፣ የእድሜ ባለጸጋ እና አካለ ጎደሎ የሆኑት የማህበረሰብ ክፍሎች፣ የቤተሰብንና በአጠቃላይ የማሕበረሰቡ ሸክም እንደ ሆኑ እንዲሰማቸው አያደርገ ይገኛል።
  22. እየተስፋፋ የመጣው በሰው ሰራሽ ዜዴ የሰው ዘርን የማራባት ሂደት፣ በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠርውን የሰው ዘር የመኖር ሕልውና ላይ የተቃጣ አደጋ እየሆን መምጣቱ ያሳስበናል።  ግለሰባዊ መብትን ከግምት ባስገባ መልኩ ሊለወጡ የማይችሉ የክርስትና የስነ-ምግባር መመሪያዎች በእግዜአብሔር እቅድ መሰረት ይጓዙ ዘንድ ጥሪ የማድረግ ግዴታ አለብን።
  23.  ለየት ባለ ሁኔታ ዛሬ ለወጣት ክርስቲያኖች ጥሪ እናቀርባለን። እናንተ ወጣቶች ከእግዚአብሔር የተሰጣችሁን ችሎታ በመሬት ውስጥ አትሸሽጉ (ማቴ. 25,25) ነገር ግን እግዚአብሔርንና ጎረቤቶችህን ወደድ የሚለውን የወንጌል ትዕዛዝ ከሕይወታችሁ ጋር በማዛመድ  እግዚአብሔር የሰጣችሁን ችሎታ በመጠቀም ክርስቶስ እውነት መሆኑን ለዓለም እንድታረጋግጡ ያስፈልጋል።  በወቅቱ ዓለማዊ ሕጎች ማረጋገጫ እየተነፈገው የመጣውን የእግዚአብሔር እውነትነት ያለምንም ፍራቻ ነባራዊ እንቅፋቶችን በመጋፈጥ ለእውነትነቱ ማረጋገጫ ልትሰጡ ያስፈልጋል። 
  24. እግዚአብሔር እያንድ አንዳችሁን ይወዳል የእርሱም ሐዋሪያና ደቀ መዝሙር እንድትሆኑ ይፈልጋል። በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች መልካም ሥራችሁን አይተው የሰማይ አባታችሁን (ማቴ 5:14, 16) ያከብሩ ዘንድ የዓለም ብርሃን ሁኑ። ከወላጆቻችሁ እና ከቅድመ አያቶቻችሁ የተቀበላችሁትን እንደ ዕንቁ (ማቴ 13:46) እጅግ ወድ የሆነውንና ብዙ ዋጋ የተከፈለበትን የክርስትና እምነትን በማስተማር ልጆቻችሁን አሳድጉ። ሰውና አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመሞቱ (1 ቆሮ 6:20) "እናንተን በታላቅ ዋጋ እንደገዛ” አስታውሱ።ኦርቶዶክስ እና ካቶሊኮችን አንድ የሚያደርጋቸው ከመጀመሪያው ምዕተ ዓመት ጀምሮ የሚጋሩኋቸው የቤተክርስቲያን ባህል ስላላቸው ብቻ ሳይሆን፣ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን የክርስቶስን ወንጌል ለዛሬው ዓለም እንዲሰብኩም በመጠራታቸውም ጭምር ነው። ይህን ተልዕኮ የወረሱ የክርስቲያን ማህበረሰብ አባላት፣ እርስ በእርስ መከባበር አስፈላጊ መሆኑን ያካተተ ሲሆን አንዱ የአንዱን እምነት አንዲቀይር ማድረግን ግን አያካትትም።እኛ ወንድማማቾች እንጂ ተፎካካሪዎች ባለመሆናችን፣ ይህ ጽንሰ-ሐሳብ የጋራ እርምጃዎቻችንን ወደ ሌላው ዓለም እንድናደርግ ይመራናል። በመላው ዓለም የሚኖሩትን ካቶሊኮችንና ኦርቶዶክ ሁሉ፣ የሰላም፣ የፍቅር እና “በመካከላቸው የአንድነት መንፈስ እንዲኖራቸው” (ሮሜ 15,5) እናሳስባለን።  በዚህ ምክንያት የተለያየ እምንታቸውን እንዲክዱ የምያደርግ ዜዴን በመጠቀም የአይማኖት ነጻነታቸውንና ባህላቸውን በሚጋፋ መልኩ አንዱ አማኝ ወደ ሌላው ቤተ ክርስቲያን እንዲለውጥ ማግባባት ተቀባይነት የለውም። እኛ የተጠራነው ሐውርያው ጳውሎስ ያዘዘንንና ያስተማረንን “ ሌላው በጣለው መሰረት ላይ እንዳልገነባ ብዬ ክርስቶስ ባልተጠራበት ስፍራ ወንጌልን መስበክ የዘወትር ምኞቴ ነበር” (ሮሜ. 15.20) የሚለውን ለመተግበር ነው።
  25. ስብሰባችን በማንኛውም ቦታ ለሚገኙ የግሪክ ካቶሊኮች እና ኦርቶዶክስ መኋል ያለውን ውጥረት ለማርገብ አስተዋጾ ያደርጋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ድሮ እንከተል ከነበረው ከ“Uniatism” ዘዴ የተረዳነው፣ አንድ ማሕበረስብን ከሌላ ማሕበረሰብ ጋር ማዋሀድን በመሰለ መልኩ፣ አንድን ቤተ ክርስቲያን ከመሰረቱ ለይቶ ከሌላው ጋር መቀላቀል ሕብረትን ለመፍጠር አመቺ ዘዴ እንዳልነበር ተርድተናል። ያም ሆኖ በእነዚህ ታሪካዊ ሁኔታዎች ውስጥ ያለፉ የቤተ ክርስቲያን ማህበራት የመኖር ሕልውናቸው የተጠበቀና  የምዕመናኖቻቸውን መንፈሳዊ ፍላጎት ለማሟላት አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ የማድረግ መብት እንዳላቸው እንዲሁም ከጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም ለመኖር ፍላጎት ማሳየት አለባቸው።  በኦርቶዶክስ እና የግሪክ ካቶሊኮች እርቅ ሊፈጥሩና የጋራ ተቀባይነት ላይ የተመሰረተ አብሮ መኖርን ልያዳብሩ ይገባል።
  26. በዩክሬይን የተከሰተው ጦርነት የብዙ ሰዎችን ነብስ ሰላባ ያደረገ እና በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ልገመት የማይችል ጠባሳ በመጣል ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቀውስ አስከትሉዋል። በዚህ ግጭት የተሳተፉት ሁሉ፣ ማህበራዊ አንድነትን በመፍጠር እና ገንቢ የሆነ የሰላም ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ እናቀርባለን። በዩክሬይን የሚገኙ አብያተ ክርስቲታናት ሁሉ ለማህበራዊ አንድነት እንዲሠሩ፣ በዚህ ግጭት እንድይሳተፉና ጠብን ከሚፈጥሩ ነገሮች ሁሉ እንዲታቀቡ ጥሪ እናቀርባለን።
  27. በዩክሬይን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች  መካከል የተፈጠረው መከፋፈል እና ግጭት ተወግዶ በዩክሬይን የሚገኙት የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በስለም  እና በአንድነት ይኖሩ ዘንድ አሁን ያለው ሕገ-ቀኖና ለችግሩ መፍትሄ ይሰጣል ብለን ተስፋ እያደረግን፣ የካቶሊክ ማህበረስብም ይህ ግጭት ይወገድ ዘንድ የራሳቸውን አስተዋጾ በመድረግ ክርስቲያናዊ ወንድማማችነታችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በግልጽ ልያሳዩ ይገባል።
  28. መድበለ ቅርፅ ባለው እና ነገር ግን አንድ እጣ ፋንታ በምንካፈልበት አሁን ባለንበት ዓለም፣ የካቶሊኮች እና የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በጋራ፣  በወንድማማችነት፣ የመዳን ምንጭ የሆነውን መልካም ዜናን ለዓለም እንዲያውጁና የሥነ-ምግባር ክቡርነትን እና  እውነተኛውን የሰው ልጅ ነጻነት “ዓልም ያምን ዘንድ” (ማቴ. 17,21) እንዲመሰክሩ ተጠርተዋል። በዚህ ዓለም የሰው ልጅ ህልውና አምድ የሆኑ ምንፈስዊ እሴቶች ቀስ በቀስ እየጠፍ ስለሚገኙ አማኝ ክርስቲያኖች ሁሉ በግልና በማሕበራዊ ሕይወታቸው መንፈስዊ እሴቶችን መመስከር ይጠበቅባቸዋል። የወደፊቱ የሰው ልጅ ዕልውና የተመሰረተው፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት እኛ ተባብረን የእውነትን መንፈስ ለመመስከር በምናሳየው ጥረት ላይ ተመርኩዞ ነው።
  29. የእግዚአብሔር እውነትነትና እና የመዳን ምንጭ የሆነውን መልካም ዜናን ድፍረት በተሞላበት መልኩ መመስከር እንድንችል ሰውም-አምላክም የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በማይነጥፍ የተስፋ ቃሉ “እናንተ አነስተኛ መንጋ የሆናችሁ መንግስትን ሊሰጣችሁ መልካም ፍቃድ ነውና አትፍሩ” (ሉቃ. 12.32) በማለት ያበረታታናል።ክርስቶስ ደስታ እና ተስፋ ምንጭ ነው። በእርሱ ማመን የሰውን ሰባዊ ሕይወት ይቀራል ትርጉም ያለው ሕይወት  እንድንኖርም ያደርጋል። ይህ እምንት የመነጨው ከሐዋሪያው ጴጥሮስ ተሞክሮ እና  በቃሉም “ቀድሞ የእርሱ ወገን አልነበራችሁም፣ አሁን ግን የእግዚብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፣ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፣ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል” (1ጴጥ.2,10)  ብሎ እንዳመለከተው ነው።  
  30. በስብሰባችን ወቅት የጋራ መግባባት ላይ እንድንደርስ ለተሰጠን የጸጋ ስጦታ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እያቀርብን፣ የእግዚአበሔርን እናት  ተስፋ በማድረግ “የእግዚአብሔር እናት ሆይ የአንቺን የምሕረት ጥበቃ እንፈልጋለን” በሚለው ጥንታዊ ጸሎት እንማጸናታለን። ለማይነጣጠለው ቅድስት ስላሴ ክብር  ይሆን ዘንድ፣  እርሷን የምያከብሯት ሁሉ የወንድማማችነት ስሜት እንዲሰማቸው እንድታነሳሳ እና  እግዚአብሔር በፈቀደው ጊዜ፣ ወደ ቀድሞ አንድነታችን በመመለስ፣ በሰላም አንድ የእግዚአብሔር ሕዝብ እድንሆን ትረዳን  ዘንድ፣ በቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነትን እንማጸናለን።

 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቼስኮ                                    የሞስኮ እና የጠቅላላ ሩስያ ፓትሪያርክ ክርል

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.