2016-03-03 09:24:00

ቅ.አ. ፍራንቼስኮ “ከሚያለያዩን ነግሮች ይልቅ አንድ የሚያደርጉን ነግሮች እንደሚበዙም ለመታዘብ ችለናል”።


በኢትዮጵያ  የኦርቶዶስክ ተዋህዶ  ቤተ  ክርስትያን  ሊቀ ጳጳሳት  ዘ አኽሱም ወ እጨገ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ  ብጹዕ ወቅዱስ  አቡነ ማትያስ  ቀዳማዊ  ለመጀመርያ ግዜ ሮምን  መጎብኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በተለይም በየካቲት 29.2016 በቫቲካን ከቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው ስለ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት የወደፊት ግንኙነት ላይ ትኩረት አድርገው መነጋገራቸው ታውቁኋል።

በግንኙነታቸው ወቅት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ ለፓትርያርክ  ብጹዕ ወቅዱስ  አቡነ ማትያስ  ቀዳማዊ ሊቀ ጳጳሳት  ዘ አኽሱም ወ እጨገ ተክለሃይማኖት እና አብሮዋቸው ለተገኙትን እንግዶች እንደ ገለጹት “በቫቲካን ተገኝተው ጉብኝት ለማድረግ በመብቃታቸው ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልጸው በጉብኝቱ ወቅት ከፍተኛ የሆነ መንፈስዊ የወንድማማችነት ስሜት እንደተሰማቸውም በመግለጽ ወደ ሀገራቸው ማለትም (ኢትዮጲያ) በሚመለሱበት ወቅት ለመላው የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አቡናት፣ ካህናት እና እንዲሁም ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ሰላምታቸውን እንድያቀርቡላቸው ተማፅነዋል።

“የፓትርያርክ  ብጹዕ ወቅዱስ  አቡነ ማትያስ  ቀዳማዊ  ጉብኝት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተውን ግንኙነት እንደ ምያጠናክር ገልፅው እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር ከ2004 ጀምሮ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከምስራቃዊ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጋር የተለያዩ ዓለማቀፋዊ ስብሰባዎችን በማዘጋጀት በነገረ መለኮት ላይ የተመሰረተ ውይይቶችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ አውስተው በተለይም ደግሞ የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተውህዶ በተክርስቲያን በእነዚህ ዓለማቀፍ ጉባሄውች ላይ ያላት ተስትፎ እየጨመረ መምጣቱን መገንዘብ መቻላቸውንም” ገልጸዋል። 

“በዓለማቀፍ ስብሰባዎች እና ወይይቶች ላይ መገነዘብ እንደቻልነው”፣ አሉ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ “የአንድ ቤተክርስቲያን መሰረታዊ ጽንሰ-ሐሳብ የሆነው በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለው ኅብረት መረዳት ስሆን ይህን መሰረታዊ ጽንሰ-ሐሳብ  ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት የሚጋሩኋቸው እውነታዎች መሆናቸውን በመግለጽ በተለይም ደግሞ አንድ እምነት፣ የክርስቶስ አካል እንድንሆን በምያደርገን አንድ ጥመቀት ማመናችን እና ጌታ እና አዳኝ ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ማመናችንም አንድነታችንን ያጠናክራል” ብለዋል።

በተጨማሪም አሉ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ “የምንኩስና ሕይወትን በተመለከተ የምንጋራቸው ወጎች እና ሃይማኖታዊ ልማዶች እንዳሉ ገልጸው፣ በተጨማሪም በስርዓተ-ሊጡርጊያ ስነ- ስርዓቶችም ላይ በጋራ የምንጋራቸው እሴቶች እንዳሉ” በመግለጽ “ከምያለያዩን ነግሮች ይልቅ አንድ የምያደርጉን ነግሮች እንደሚበዙም ለመታዘብ ችለናል” ብለዋል።

በእርግጥም “አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ፣ ሌሎችም የአካል ክፍሎችም አብረው ይሰቃያሉ፣ አንዱ የአካል ክፍል ሲከበር ሌሎችም የአካል ክፍሎች አብረውት ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ” (1ቆሮ. 12,26) የሚለው የሐዋርያው ጳውሎስ ማሳሰብያ በእኛ ላይ ተግባራዊ እንደሆነ ይሰማኛል ብለዋል።

ልክ በጥንት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የፈሰሰው ሰማዕታት ደም ለአዲሱ ክስቲያን ዘር እንደ ሆነ ሁሉ ዛሬም ቢሆን የሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሆኑ ሰማዕታት ደም፣ ክርስቲያናዊ አንድነት ይፈጠር ዘንድ ዘር ሆኖኋል ምክንያቱም በቤተ ክርስቲያን ባህል ሰማዕታት እና ቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ አንድ መሆናቸው ስለ ምታመን ነው ብለዋል። “እርሶ የሚመሩት ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ በሰማዕታት የተገነባ ቤተ ክርስቲያን ነው” ያሉት ቅዱስ አባታችን “ዛሬም ቢሆን በመካከለኛው ምስራቅ እና በአንድ አንድ የአፍሪካ ሀገራት በቁጥር አናሳ በሆኑት ክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ የሆነ ጥቃት ብዙዎቹን ክርስቲያኖች የሕይወት ዋጋ እያስከፈላቸው መሆኑን ገለጸው ዓለምን በፖሌቲካ እና በኢኮኖሚ የሚመሩኋት አካላት ሁሉ ሰላም እንዲሰፍን እና አብሮ፣ ተቻችሎ መኖር የምያስችል መግባባት እንዲፈጠር በማድረግ፣ እርቅ እንዲፈጠር፣ የተፈጸመ በደል  በይቅርታ እንዲታለፍ እና የአንድነት መንፈስ እንዲፈጠር የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ አጋጣሚውን ተጠቅመው ጥሪ አደርገዋል።

በመቀጠልም ኢትዮጲያ የሕዝቦቹኋን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ረገድ ከፍተኛ የሆነ እምርታን እያሳየች እና ሕግን መሰረት ያደረገ ፍታዊ ማሕበረሰብ እንዲመሰረት በተለይም የሴቶች ሚና በተለያዩ መስኮች እያደገ እንዲመጣ ጥረት እያደረገች መሆኑ  እንዳስደሰታቸው ገልጸው፣ በአብያተ ክርስቲያናት መካከል በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረት ትብብር እየጨመረ መምጣቱ መልካም ጅምር መሆኑን አስረድተው በዚህ ረገድ የኢትዮጲያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጋር ተባብራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑኋን በዚህ አጋጣሚ ላረጋግጥሎት እወዳለሁ ብለዋል።

በጨረሻም “ይህ ጉብኝት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን መንፈስዊ  ግንኙነት እንዲጠናከር አዲስ ምዕራፍ እንደ ከፈተ ተስፋ አደረጋለው ብለው” በታሪክ አጋጣሚዎች ለተፈጠሩት ስህተቶች፣ አለመግባባቶች እና አለመተማመን  ሁሉ የእግዚአብሔርን ምሕረት እና ፈውስ እየጠየቅን የቅዱሳን እና የሰማዕታት ጥበቃ እንዳይለየን እየተማጸንን በተለይም ደግሞ ከእናንተው ሀብታም ከሆነ ስርዓተ አምልኮ ከተወሰደው “የጥበብ ምንጭ የሆንሽ ኦ ድንግል፣ ከልጅሽ ክርስቶስ በሚመነጨው የወንጌል ጅረት እጠቢን። በመቀሉ የጠብቀን። ምሕረቱ ይጋርደን፣ በቅባቱ አድሶን በመልካም ፍሬ ይከበንም ዘንድ የምህረት እናት በሆነችው በቅድስት ማሪያም አማላጅነት እንለምናለን በማለት በመጨረሻም “ቅዱስነቶ እግዚአብሔር ለኢትዮጲያ ኦሮቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን አገልግሎት ይባርክ ዘንድ ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.