2016-03-02 16:13:00

ቫቲካን፥ የሕንጸት መርሃ ግብር በጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ


በየዓመቱ እንደሚከናወነው ሁሉ ይኸው ጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው መራሔ መንግሥት ተብሎ በሚጠራው ሕንጻ ባለው የጉባኤ አዳራሽ በሚሥጢረ ንስኃ ዙሪያ እ.ኤ.አ. መጋቢት 4 ቀን ተጋባእያኑ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል በመቀበል የሚጠናቀቀው 27ኛው የውስጠ ሕንጸት መርሃ ግብር እ.ኤ.አ. የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. መጀመሩ ጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳት

ሲቻል፡ 450 ተጋባእያን እያሳተፈ ያለው ዓውደ ሕንጸቱን በንግግር የከፈቱት የጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ አቢይ አበ ነፍስ ብፁዕ ካርዲናል ማውሮ ፒያቸንዛ የዘንድሮው ዓውደ ሕንጸ ለየት የሚያደርገው የተገባው የምኅረ ዓመት  መሆኑ ገልጠው፡ የሕንጸቱ ማእከል የንስኃ ምስጢር ነው፡ ንስኃ የዕርቅ ምስጢር ነው፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የምኅረት ገጽ በሚል ርእስ ሥር የምኅረት ዓመት ለማወጅ ባወጡት ሰነድ ላይ እዳሰመሩበት ምኅረት ሁሉን ነገር የሚፈርደው የሁሉም የቤተ ክርስቲያን የአያንዳንዱ ሰው ፍርድ ነው፡ ከንስኃ የሚመነጭ ምኅረት ስለዚህ የንስኃ ሚሥጢር የክርስቶስ ቀጣይ ኅላዌ መዚህ ምድር የሚያረጋጥ ነው። ወንጌል ዕለት በዕለት እንድንለወጥ ይጠራናል። ይኸንን የዛሬ 2 ሺሕ ዓመት በፊት በክርስቶ እውን የሆነው ምኅረት ቀጣይነቱ የሚያረጋግጥ ቅዱስ ሚሥጢር ነው። እግዚአብሔር በክርስቶስ ከእኛ ጋር ብቻ ሳይሆን ስለ እኛ ለእኛ ሆነ ለሚለው ፍቅር ማረጋገጫ ነው። ስለ እኛ ኃጢአት የሚሰዋ በግ ሆነ። አሁን በአባቱ ቀኝ ለመቀመጡ የምንመሰክርበት ቅዱስ ሚሥጢር ነው እንዳሉ ጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ ያሰራጨው መግለጫ አስታወቀ።

ይኽ ቤተ ክርስቲያን የምታውጀው ምኅረት በንስኃ ከእግዚአብሔ ጋር ከባለንጀራ ጋር ከገዛ እራስ ጋር የሚያስታርቀው ቅዱስ ሚሥጢር ያንን ጥንታዊው እባብ ለለቀቀው መርዝ የፍቱን መድሂት ቅዋሜ ነው፡ ያንን ክርስቶ ያጋለጠውና የገሰጸው የክፋትና የኃሰት መንፈስ ዛሬም ህዝብና ዓለም ለማጥመድ ሽርጉድ ይላል። በሚሥጢረ ንስኃ አማካኝነት እናጋልጠዋለን በእርሱ ላይ የክርስቶስ ድል አድራጊነትን እንመሰክራለን በክርስቶስ ድል መንሳት ድል እንነሳለን እንዳሉ የጳጳሳዊ ቤተ ኑዛዜ መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.