2016-03-02 16:10:00

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ፥ ለተፈናቃዮችና ስደተኞች የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ለማድረስ


የቤተ ክርስቲያን ፍቅርና የቅዱ ጴጥሮስ ተከታይ ቅርበት ለመመስከር በፊሊፒንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሰብአዊ እርዳታ ማኅበራት ለሚያጠራንፍ የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ልዊስ አንቶኒዮ ታግለ ሊባኖስ የስደተኞችና ተፈናቃዮች መጠለያ ሠፈር እየጎበኙ መሆናቸው የካሪታስ ኢንተርናዚዮናሊስ መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕነታቸው ከሚገኙበት በሶሪያ በካሪታስ ለሚጠራው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበር ቅርንጫፍ ሥር ለሚተዳደረው ከሚገኙበት የበቃዕ ስደተኞች ምጠለያ ሠፈር በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱ ቃለ ምልልስ፥ በሊባኖስ በሚገኙት በተለያዩ መጠለያ ሠፈር የሚረዱት ስደተኞና ተፈናቅዮች ሥርወ ስቃይ ኤኮኖሚያዊ ብቻ ሳይሆን በበለጠው ፖለቲካዊ ጉዳይ ነው። ከጦርነት ከቅትለት ከአድልዎ ከሃይማኖት ነጻነት ረገጣ የገዛ እራሱንና የቤተሰቡን ሕይወት ለማትረፍ ክልሉን ለቆ የወጣ ህዝብ ነው። በክልሉ ሰላም ማረጋገጥ አስቸኳይና የማያሻማ ምርጫ ነው፡ ምንም’ሏ የእርዳታ አቅርቦ አስፈላጊነት ያለው ቢሆንም ቅሉ ዘላቂው መፍትሔ የሚያስገኘው ሰላም ለማረጋገጥ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከውይይት የመነጨ መፍትሔ ማፈላለግ ይኖርበታል። ሰላም ሲገኝ የተቀረው ችግር መፍትሔ በቀላሉ ሊያገኝ ይችላል ብለዋል።

የክልሉ ሕዝብ ተፈናቃዩ ስደተኛውም ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ለድጋፋቸው መጠመድዋ የሚያውቁት ከመሆኑም ባሻገር አድናቆቱም እንዳላቸው ቀርበው የተገነዘቡትና ከተገናኙዋቸው ስደተኞ የእርዳታ ማኅበር አባላትና አካላት የተመሰከረላቸው መሆኑ ገልጠው፡ ሁሉም አለ ምንም የሃይማኖ ልዩነት ሰብአዊ ድጋፍ የሚያገኙበት መጠለያ ማእከል ተገኝተው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍቅር ይቅደም ፍቅር ይቅደም ቤተ ክርስቲያን ለፍቅር። ክርስቶስ በፍቅር ሁሉን ነገር እንደሚሸነፍ አረጋግጦልናልና በፍቅር ብቻ ነው የሰውን ልጅ ችግር ለማቃለል የሚቻለው። ስለዚህ የዚህ ፍቅር መስካሪ መሆን እንዴት መታደል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.