2016-02-29 15:21:00

ቅድስት መንበርና አርጀንቲና


እ.ኤ.አ. የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አገረ ቫቲካን ለመጎብኘት ቅድስት መንበር የገቡትን የአርጀንቲና ርእሰ ብሔር ማውሪሲዮ ማክሪን ተቀብለው ማነጋገራቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ርእሰ ብሔሩ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ግኑኝነት ተሰናብተው በቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ፖውል ሪቻርድ ገላገር ከተሸኙት ከቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘታቸው ይጠቁማል።

የተካሄደው ግኑኝነት በቅድስት መንበርና በአርጀንቲና መካከል ያለው ክሌአዊ ግኑኝነት የተዋጣለት መሆኑ ያበከረና በሁለቱ አገሮች የጋራ ጥቅም ላይ በተመለከተ ርእሰ ጉዳይ ብሎም የተሟላ እድገት ለማረጋገጥ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ድኽነት ለመዋጋትና ያደንዛዥ ዕጸዋት ዝውውርና የዚህ የሞት ባህል ምክንያቶችና ያደንዛዥ ዕጸዋት አንቀሳቓሽ የወንጀል ቡድኖች ለመቆጣጠር በሚደረጉት ጥረቶች ያለው ትብብር እውቅና ከመስጠትም አልፎ ቅድስት መንበር የአገርና የሰው ልጅ የተሟላ እድገት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የምትሰጠው አገልግሎት በአርጀንቲና መንግሥት በኩል እውቅናና አድናቆት የተሰጠው መሆኑ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ በተካሄደው ግኑኝነት አንገብጋቢ ናቸው በሚባለቱ በዓለም አቀፍ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሃሳብ ልውውጥ መካሄዱ ይፋ አድረገዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለአርጀንቲናው ርእሰ ብሔር ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክትና እንዲሁም ወንጌላዊ ሓሴት በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን እንደ ገጸ በረከት ሲለግሱ የአርጀንቲናው ርእሰ ብሔር በበኩላቸውም በአርጀንቲና የኢየሱሳውያን ልኡካን ወንጌል በአገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጌል በማስፋፋት በአገሪቱ ወንጌል ያስገቡበት ሁነት የሚያስታውስ ልዩ መስቀልና በተጨማሪም አንዳንድ የአርጀንቲና ባህላዊ ሙዚቃ ሸክላዎች እንደ ገጸ በረከት መለገሳቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.