2016-02-29 15:18:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአደንዛዥ ዕጸዋት ተጠቂ ዜጎች ማገገሚያ ማእከል ጎበኙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበርና የምኅረት አመት አስተባባሪ ኰሚቴ ሊቀ መበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊሲከላ ተሸኝተው በነፍሴ ኄር አባ ማሪዮ ፒኪ የተመሠረተው በአደንዛዥ ዕጸዋት የተጠቁት ከዚህ አደገኛው የባርነት ሱስ ለማላቀቅ የሚደገፉበት  ሮማ አቅራቢያ በምትገኘው ካስተል ጋንዶልፎ ከተማ ክልል የሚገኘውን Ceis-የቅዱስ ካርሎ የኢጣሊያ የትብብር የማገገሚያ ማእከል እ.ኤ.አ. የካቲት 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በምህረት ዓመት ምክንያት እንደጎበኙ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን በማገገሚያው ማእከል የሚረዱትን 60 የቀድሞ ያደንዛዥ ዕጽዋት ተጠቃሚ ወጣቶችና የዚያ ማገገሚያ ማእከል የበጎ ፈቃድ ሠራተኞች የህክምና ባለ ሙያዎችና የስነ ልቦና ሊቃውንት ጋር በመገናኘት መሪ ቃል ለግሰዋል ያሉት የቫካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይሊኖ አያይዘው ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ከዛም ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በዚያኑ ማእከል ሐዋርያዊ ጉብኝት አካሄው እንደነበር አስታውሰው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለማእከሉ የቅድስት ማርያም ዘሉኻኖ የተቀሰለ ኅቡር ቅዱስ ምስል መለገሳቸው አስታውቀዋ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ስላ አካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት አስመልክተው የማእከሉ ሊቀ መንበር ሮበርቶ ሚነዮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ሐዋርያዊ ጉብኝቱ ያልተጠበቀ እንደነበርና እንዲህ በመሆኑም ሁሉም በዚያ የማገገሚያ ማእከል የሚደገፉትም የማእከሉ ሠራተኞች በዕለታዊ ሥራ ተጠምደው እያሉ ነው ቅዱስ አባታችብ የተገኙት። በእውነቱ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡ የተደረገ ምንም ዓይነት ቅድመ ዝግጅት አልነበረም። ቅዱስነታቸው ሁሉንም ሰላም ብለው ማእከሉን ጎብኝተው ለማእከሉና በማእከሉ ለሚገኙ የምኅረት ጸጋን ለግሰዋ።

በማእከሉ ከሚረዱት የአደንዛዥ ዕጸዋት ተጠቃሚ ወጣቶች በእምነትና በወንጌል ዙሪያ ስለ ሱሰኝነት በሚመለከቱ ርእሰ ዙሪያ ያቀረቡላቸው ጥያቄ ማእከል በማድረግ ምዕዳን መለገሳቸው ሚነዮ አስታውቀዋል።

ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ በበኩላቸውም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በማእከሉ የተገኙት በማገገም የሚገኙት ወጣቶች መክሰስ ላይ እያሉ ልክ ከሰዓት በኋላ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር 4 ሰዓት ተኩል ላይ እንደነበር ገልጠው ማንም ያልጠበቀው ጉብኝት እንደነበር የሚያረጋግጥም ነው፡ እዛው ከወጣቱ ጋር ተገናኝተው ተካፍሎና ያብሮ መኖር ምስክር መዓድ ሲያዩ በእነቱ ደስ ነው የተሰኙት። ምክንያቱም መዓድ ቤተሰብ የመሆን ምልክት ነውና ብለዋል።

ከወደቁበት አሰቃቂው የሞት ባህል ከሚያስፋፋው ተግባር አንዱ ያደንዛዥ ዕጸዋት ሱሰኝነት መሆኑና በዚህ የሞት ባህል የተጠቁት ዜጎች ከወደቁበት ችግር ለማላቀቅ አገልግሎት የሚሰጡት የቤተ ክርስቲያን ማእከሎች በሁሉም የሚደነቁ በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች መልካም ፍላጎትና ጥረት የተቋቋሙ ናቸው። የሞት ባህል በሕይወት ባህል ድል እንድሚነሳ ወንጌላዊ ሕይወት በማቅረብ የሚመሰክሩ ናቸው፡ አለ ምንም የሃይማኖት የባህል የዜግነት ልዩነት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው በማለት ያካሂዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.