2016-02-23 09:35:00

ቅ. አ. ፍራንቼስኮ “የእኛ ሕይወት የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ መሆን ይኖርበታል”


እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 20.2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ከ25 ሺ በላይ ለሚሆኑ ከተለያየ የኢጣሊያን ግዛቶች ለተውጣጡ የደም ለጋሾችና በዚያው ለተገኙ የሀገር ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን እነደ ገለጹት “ኢየሱስ ከእግዚአብሔር የተላከው በምህረቱ የሐጥያተኛውን ልብ በመንካት ወደ ትክክለኛው እግዚአብሔር ወደ ሚፈልገው መንገድ እንዲመለስ ለማድረግ ነው” ማለታቸውን ጋዜጤኛችን አሌክስአንድሮ ጂዞቲ ዘግብዋል።

“የእኛ ሕይወት የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫ መሆን ይኖርበታል” ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ “ሁሉም ክርስቲያኖች የተጠሩት ይህንን የክርስቶስ ፍቅር ለመመስከር በመሆኑ ሳንሰለች እግዚአብሔር ለሚፈልጉት ሁል ቅርብ መሆኑን በትግባር ልንመሰክር ይገባል” ብለዋል። ይህንንም መተገበር የምንችለው ለጋሽ በመሆን፣ የታመሙትን በመንከባከብ፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር መሆኑንና መሓሪ መሆኑን በመግለጽ ወደ ንስሓ አንዲመለሱ ማድረግ አና የመሳሰሉትን የፍቅር ተግባራት በመፈጸም ጭምር መሆን ይኖርበታል በማለት አስገንዝበዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከው እኛን የፍቅር ሚስጢር አንድያስተምረን በመሆኑና የተላከበትንም ዐላማ በአግባቡ እንደፈጸመና እኛ እያወደምን የምነገኘውን አለም ለማስተካከል ጭምር በመሆኑ የኛም የክርስቲያኖች ጥሪ መሆን የሚገባው ጉዳይ ደግሞ የኢየሱስን አርአያ በመከተል ዓለምን ለማዳን የበኩላችንን ጥረት ማድረግ እንደ ሚጠበቅበን አሳስበዋል።

“ኢየሱስ ለኛ የሚያሳየው ፍቅር የሓጥያተኛን ልብ የመቀየር ሀይል አለው” ያሉት ቅዱስ አባታችን “እኛ እንደ ምናስበው ሓጥያተኛ ሰው የኢየሱስ ጠላት ሳይሆን ኢየሱስ የመጣው ሓጥያተኞችን ወደ እርሱ እንዲመለሱና በታልቅ ፍቅር ልባቸውን በመንካት ወደ ትክክለኛውን መንገድ እንጊመርጡ መሆኑን ተገንዝበን ያልምንም ፍርሀት ወደ ኢየሱስ በንስሓ ልንመለስ ይገባል” ብለዋል።

“ሁላችንም በእግዚአብሔር ፊት የምያስወቅሰን ሓጥያት አለን” በማለት አስተምሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ “ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ላይ ያለን መተማመን አንድ አንዴ ቢቀንስም እንደ ሰው ያልሆነው እግዚአብሔር ግን እኛን በመቅረብ መጽናናትንና ምህረትን እንደ ሚለግሰንና የምሕረት ምንጭ የሆነውን የፍቅር በር እንደሚከፍትልን ግን ማመን ይጠበቅብናል” ብለዋል።

በጨረሻም ቅዱስ አባትችን እዳሳሰቡት “እግዚአብሔር ለእኛ የከፈተልንን የፍቅር እና የምሕረት በር ከግንዛቤ በማስገባት፣ ክርስቲያን በመሆናችን የተሰጠን መምፈሳዊ ተልዕኮ ክርስቶስን መመስከር በመሆኑ፣ ሕይወታችንን ከክርስቶስ ሕይወት ጋር እንዲዛመድ በማድረግ ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች፣ በተለይም በስቸጋሪ ሁኔታ ለሚገኙት ሰዎች የእግዚአብሔር ፍቅር ሁል ጊዜ ከእንርሱ ጋር መሆኑን በማስገንዘብና በመርዳት የበኩላችንን ጥረት ልናደርግ ይገባል” ብለው አስተምሮዋቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.