2016-02-18 09:17:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ለመክሲኮ ወጣቶች፦ ክርስቶስ ተስፋችሁ ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ መክሲኮ የሚቾአካን ግዛት ወደ ምትገኘው የሞረላ ከተማ ልክ በአገሪቱ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ ስምንት ሰዓት ከ 45 ደቂቃ እንደደረሱ ከክልሉ የመንግስት አካላት ከውሉደ ክህነት አባላት ከስራተኛ ማኅበራት ጋር ተገናኝተው በቨኑስቲኣኖ ካራንዛ የስፖርት ሜዳ ከክልሉ ውሉደ ክህነት አባላት በጠቅላላ የውፉይ ሕይወት አባላትና የውሉደ ክህነት ተማሪዎች ያሳተፈ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው በመክሲኮ ሰዓት አቆጣጠር ልክ እኩለ ቀን ከ 15 ደቂቃ ወደ ሞረሊያ ርእሰ ሰበካ በመሄድ ምሳ ከተቋደሱ በኋላም ከሰዓት በኋላ ልክ 16 ሰዓት ከ 30 ደቂቃ በሞረሎስ ይ ፓቮን የእግር ኳስ ሜዳ ከመክሲኮ ወጣቶች ጋር ተገናኝተው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

ቅዱስ አባታችን ወጣቶች የአገራቸውን ባህል የሚያንጸባርቅ መንፈሳዊ መዝሙሮችን በማቅረብ ላደረጉላቸው የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አመስግነው አንዳንድ ወጣቶች የአንድ አገርና ኅብረተሰብ ሞት ምክንያት እየሆነ ያለው አመጽ የአንደንዛዥ ዕጸዋት ዝውውር የወንጀል ቡድኖች የሚያስፋፉት ጸረ ሰብአዊ ተግባር ምግባረ ብልሽት የሥራ እጥነት ብሎም ሰብአዊነት ልክ የሌለው የሥነ ጾታዊ ትምህርት በተያያዘ መልኩም ሰብአዊ ግኑኝነት ርእሰ ጉዳዮች ማእከል በማድረግ ባቀረቡላቸው ጥያቄ መሠረት ጥልቅ ምዕዳን መለገሳቸው ችራዞ ገልጠው፦

ወጣት የአገር ሃብት፣ ክርስቶስ ተስፋችሁ ነው

ለብ ያለ መሆን፣ ፍርሃት አስመሳይነት እውነትን ላድር ባይነት መሠዋት የማድረግ ተግባር ለማሸነፍ የምንፈልግ ከሆንን ወደ ጥጋ ጥግ የከተሞቻችንና የህልውናው ክልል ማቅናት መሄድ መውጣት የምንፈልግ ከሆን በዚያ ተስፋችን በሆነው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ መጣበቅ ይኖርብናል። የሁሉም መልካምነት መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

እናንተ የአገራችሁ መክሲኮ ሃብት ናችሁ፣ የቤተ ክርስቲያን ሃብት ናችሁ እንዲህ ስላችሁ ለይስሙላና ወጣት ተስፋ ነው የሚለውን ልሙድ ተደጋጋሚ አነጋገር ለመድገም አይደለም፣ ልክ እንደ ጥሬ ሃብት እንደ አንድ ማዕድን ያንን ተስፋ የመሆናችሁ ኃብት ለመልካም ነገር መለወጥ ይኖርባችኋል። የተገባ ርእሰ ግምት የሌለህ ከሆንክ ለመሆንህ አቢይ ግምት የማትሰጥ ከሆንክ ያለህ ክብር አሳንሶ ለሚመለከት ለያሚያገል ሁለተኛ ወይንም አራተኛ ዜጋ በማድረግ ለሚመለክትህ እንዳውም ወጣትነትህንና ሰብአዊ ክብርህን ለሚነጥቅ እስከ መግደል ለሚቃጣው ባህል፣ ሃብት ካለህ ብቻ ለሚለው አመለካከት እጅህን እንድትሰጥ ለሚያደርግ ሁሉ አሜን የምትል ከሆንክ ተስፋ የሌለህ ትሆናለህ፣ ይኸንን ተስፋ የሚነጥቁ ብዙ ጸረ ሰብአዊ ተግባሮች አሉ፣ ወጣትነትህን አክብር ተስፋ መሆንህም እወቅ።

እርባና የሌላችሁ ሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርግ ፈተና ኢየሱስ ለይቶ አጋልጦታል

የተገባ ክቡር ሥራ ከሌለህ ሰብአዊ መብትህና ክብርህ ካልተከበረ የአገር ሃብት ነኝ ብሎ ለመናገር ያዳግት ይሆናል፣ ነገር ግን ማንኛውም ችግር የአገር ሃብት የመሆናችሁ እውነት ሊሰርዘው አይችልም።

ምክንያቱም እንደ እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ፣ ሃብትን ወደ ተስፋ የሚለውጠው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ የተገባ አወንታዊ ህልም የሚያነቃቃው እርሱ ነው። የመኖር አግባብ ድኽነት አደንዛዥ ዕጸዋት አንቀሳቓሽ መሆን ማለት እንዳልሆነ እውነት መንገድና ሕይወት የሆነው ኢየሱስ ያረጋግጥልናል።

ክርስቶስ በምንወድቅበት ጊዜ መጠጊያችን እርሱ ብቻ ነው

እርሱን እቀፉ በእርሱ እቅፍ ሥር ገዛ እራሳችሁን አኑሩ፣ ሁሉም ከባድ ሆኖ ሲታየንና በላያችን ላይ እንደ ቀንበር ሲጫነን እርሱን እቀፉ፣ መጠጊያው እርሱ ነው። ብትወድቁም ያነሳችሁ ዘንድ ፍቀዱለት።

ድል አድራጊነት ወደ ላይ መመንጠቅ ሳይሆን በተወደቀበት ተዘሮ አለ መቅረት ነው። ስለዚህ ድሉ በመሬት ላይ ወድቆ በወደቁበት መሬት አለ መቅረት ነው። ስለዚህ መቼም ቢሆን ወድቃችሁ አትቅሩ፣ በወደቅንበት አንኑር አደራ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እጆቹን ይዘረጋላችኋል፣ አንድ ወንድም ወደ መውደቅ ሲያዘግምና ሲወድቅ አደራ ከጎኑ ሁኑ፣ ማዳመጥ ለግሱለት፣ በኢየሱስ ስም ኃይል ስጡት፣ ኢየሱስን ማካፈል ያስፈልጋል። እርሱ ትልቅና ወደር የሌለው ድጋፍ ነው።

ወጣት የቤተ መቅደስ ገንቢ፦ ቤተሰብ የአገር መሠረት ነው

እንደ እባብ ብልሆች እንደ እርግብ የዋሆች ሁኑ፣ የቤተ መቅደስ ገንቢዎች እንጂ የሃሰት ቤተ መቀደስ እትገንቡ፣ ማኅበረሰብ ቁምስናዎች በተለይ ደግሞ ያ ተካፍሎ መኖር እውነተና ፍቅር የሚኖርበት የሕይወት ምርጫ የምትለዩበት የቤተሰብ ገንቢዎች መሆን ይገባል፣ ቤተሰብ የመጀመሪያ ትምህርት ቤትና ለአንድ አገር ግንባታ የመሰረት ድንጋይ የሚኖርበት ሥፍራ ነው በማለት ያሳሰቡት ቅዱስ አባታችን ተስፋ ሃብትና ክብር ማእከል ያደረገው ስልጣናዊ ምዕዳናቸውን ሲያጠቃልሉ፣ እግዚአብሔር የሰጠንን ወደር የማይገኝለት ጸጋ ለይተን እንድናስተውል የምትደግፈን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘጓዳሉፐ ኢየሱስ ሞትን አሸንፎ መነሳቱን የሚያረጋግጥልን በክርስትያን የመሆን ክብር የተካነው ሕይወት ከጐናችን ሆኖ የሚሸኘን ተስፋ በእኛ ውስጥ እንዲያድግ ታደርጋለች በማለት እንዳጠቃለሉ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.