2016-02-09 10:01:00

ጸሎት ማለት መንፈሳዊ የምሕረት ሥራን በመፈጸም ሁሉንም የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር ልብ ማቅረብ ማለት ነው።


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ6.2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅዱስ የምሕረት አመትን አስመልክቶ በተሰየመውና ቅዱስ የምሕረት አመት እስክጠናቀቅ ድረስ በሳምንት አንድ ጌዜ በእለተ ቅዳሜ በምደረገው ሳምንታዊ የወንጌል አስተምሮ ላይ ለተገኙት ከአሥር ሺ በላይ ለምገመቱ ምዕመናንና ሀገር ጎብኝዎች ቅዱስ አባታችን እንደገለጹት “በዓለም የምገኝ ሕዝብ ለመኖር የምያስፈልገው ምግብ ብቻ ሳይሆን መንፈስዊ ርሃቡን ለማስታገስ የእግዚአብሔር ምሕረት ያስፈልገዋል” በለዋል።

በአስተምሮ ላይ ለተገኙ ከተለያየ የአለም ክፍሎች ለመጡ የቅዱስ ጲዮ ወዳጆች በተለየ ሁኔት እንደገለፁት “ከቅዱስ ጲዮ የተማራችሁትን የይቅርታ አድራጊነት መንፈስን በመላበስ የፍቅርን ሃይል የምያላብሰውን ይቀርታን የሕይወታችሁ አካል በማድርግ የሰላምንና የይቅርታ አድራጊነትን መንፈስ በቤተ ክርስቲያንና በዓለም ውስጥ ልትዘሩ ያስፈልጋል” በለዋል ስል ጋዜጠኛችን አሌሳንድሮ ዴ ካርሎስ ዘግቡዋል።

ይቅርባይነት የሚሰጠውን ደስታ በየቀኑ በሕይወታችን ልንለማመድ ይገባል በማለት አስተምሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “ቅዱስ ጲዮ የምስጢረ ንስሓን አገልግሎትን ለብዙሃን ምዕመናን ያለምሰላቸት በታልቅ ትዕግስት እና ጠበብ በመለገስ የብዙሃኑን ምዕመናን በሓጥያት የቆሰለ ልብ በንስሓ በመፈውስ ወደ እግዚአብሔር መንገድ እንደመለሱና በእግዚአብሔር ፍቅር በመታቀፍ የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖራቸው በማድርጋቸው ዘወትር እንደ ምውሱ ገልጸው እኛም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል የተቀበልነውን መንፈስዊ ፀጋ ለወንድሞቻችንና እህቶቻችን በማስተላለፍ የእግዚአብሔር ፀጋ ተካፍይ እንዲሆኑ ልናደርግ ይገባል በለዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮስ በማስከተልም ስለ ጸሎት አስፈላጊነት ስገልጹ “ጸሎት የምናደርገው ልክ ጤናችን በምታወክበት ወቅት መድሓኒት ወስደን ከህመማችን እንደምንፈስ ሁሉ የምንጸልየውም ጸሎታችን መልካም ጤናን እንድያስገኝልን በማስብ ብቻ ሊሆን አይገባውም ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ መሆን የምገባው እውነታ ግን ጸሎት ማለት መንፈሳዊ የምሕረት ሥራን በመፈጸም ሁሉንም የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር ልብ ማቅረብ ሊሆን ይገባዋል።

በመጨረሻም ጸሎት በሕይወታችን ወስጥ ታምራት እንድከሰቱ የማድርገ ሓይል እንዳለው ገልጸው በተጨማሪም ጸሎት ያልተወሳሰበና ብዙ የደህንነት መጠበቅያ የሌለውን እንደ ማንኛውም መልካም አባት የማይሰለቸውን የእግዚአብሔርን ልብ የምከፍት ቁልፍ በመሆኑ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል መጸለይ ይጠበቅብናል ብለው እናንተም እዚህ የተሰበስባችሁ የቅዱስ ጲዮ ወዳጆች በሙሉ የሳቸውን ፈለግ በመከተል የእግዚአብሔርን ብርሃን በሕይወታችን እንዲበራ የምያደርገውን ጸሎት በማዘውተር፣ የቤተ ክርስትያን ወዳጅ በመሆን ጸሎት በሕይወታችን ታምራትን የማስከሰት ሀይል እንዳለው በማመን፣ በታልቅ መንፈሳዊነት እለታዊ ኖሮዋችንን ልንመራ ያስፈልጋል በማለት አስተምሮዋቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.