2016-02-05 15:45:00

ስሪላንካ፦ ብፁዕ ካርዲናል ራንጂት ለአገር ሰላምና አንድነት ጥሪ


እ..ኤ.አ. የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የተከበረው የስሪላንካ የነጻነት ቀን ምክንያት በማድረግ የኮሎምቦ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ማልኰልም ራንጂት ሰላም አንድነት ውህደት የተሰኙትን እሴቶች ማእከል ያደረገ መልእክት ማስተላለፋቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የስሪላንካ መላ የፖለቲካ አካላት ላንድነት

ብፁዕ ካርዲናል ራንጂት የአገሪቱ ሕዝብ ነጻነት አልሞ በአንድነት በመቆም የታላቅዋ ብሪጣንያ ቅኝ ግዛት መክቶ ያጎናጸፈው ያገር ሉኣላውነት በማስታወስ፣ አንድነት ኃይል ነው፣ ሆኖም ከቅኝ ግዛት ነጻ ከተወጣ በኋላ ያንን ውህደትና አንድነት አቅቦ ለመኖር ምንኛ እንዳዳገተ የቅርብ ታሪክ ትውስት ነው። በፖለቲካ ርእዮተ ዓለምና በጎሳ በመለያየት የአገር አድነት ተፈረካክሶ ቆይቷል፣ በአሁኑ ሰዓት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ቢኖር ሁሉም የፖለቲካ መሪዎችና የሃይማኖት መንፈሳውያን መሪዎች በጋራ ለአገር አንድነትና እድገት መጣበቅና የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የአገር ባህል ነጻነት እኩልነት ፍትሕ እውነት ላይ የጸና ሰላማዊ የጋራ ኑሮ በማረጋገጡ ሂደት አብነት ሆነው መገኘት ነው። ስለዚህ አደራ የአገር አድነት እንንከባከብ እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ጠቅሶ ሁሉም በፖለቲካ ዓለም የተሰማሩት የበላይ አካላት ሕዝብ በጠቅላላ እንደየ ኃላፊነቱ ግዴታው በመወጣት ያንን የከበረውን እሴት ዋስትና ያሰጡ ዘንድ አደራ እንዳሉ ያመለክታል።

ለነጻነት ተገቢ ክብር መስጠት

ነጻነት ኃላፊነት ነው። በመሆኑም ተገቢ ክብር እንዲሰጠውና ያንን ሲሪላንካ የተቀዳጀችው ነጻነት እንዳይደፈርስ እግዚአብሔር ይርዳን በማለት ብፁዕ ካርዲናል ራንጂት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.