2016-02-04 10:19:00

ቅ. ፒዮ እና የቅ. ሊሆፖልዶ ቅዱስ አጽም ለሕዝብ ለእይታ ቀረበ


ልዩ የምሕረት አመት ኢዩበሊዩን በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል። የህንን የምሕረት አመት በተለያዩ መንፈሳዊ ክንውኖች በመዘከርና የታቀደውን መንፈሳዊ ለውጥ ለማምጣት ይቻል ዘንድ ብዙ ጥረቶች በአለም ዙሪያ በምገኙ የካቶሊክ አባያተ ክርስትያናት እየተከናወነ እንድምገኝ ይታወቃል።

የዝህም መንፈሳዊ ዝግጅት አካል የሆነውና እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከየካቲት 5-11 2016 በቅዱስ ጴጥሮስ ባዝሊካ የሁለት ቅዱሳን ማለትም ቅዱስ ፒዮ ፐትራልቺና እና የቅዱስ ሊሆፖልዶ ማንድቺ ቅዱስ አጽም ለሕዝብ የእይታ እንደምቀርብና በነዝህ የሚስጢረ ንስሓ አፍቃሪ በነበሩ ቅዱሳን አማልጅነትም ምዕመናን ወደ ንስሓ ይመለሱ ዘንድ መንፈሳዊ ፀጋን የምያገኙበት አጋጣሚ በመሆኑ እንድሉን በአጋባቡ መጠቀም እንደሚገባ አባ ፍላቪያኖ ጆቫኒ አስታውቀዋል ስል ጋዜጠኛችን ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ዘግቡዋል።

ቅዱስ ሌሆፖልዶ ማንድች በሞንተኔግሮ ዳልማዝያ በምትባል ከተም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር 1866 ተወለደው ለሰላሥ አመታት ይህል በፓዶቫ በፍራንችስካዊያን ገዳም ሕይወታቸው እስካለፈበት 1942 ድረስ የምስጢረ ንስሓ አገልግሎት ለምዕመናን በመስጠት እናዳሳለፉ ከሕይወት ታሪካቸው ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስ ሌሆፖልዶ የቅድስና ማረጋቸውን ያገኙት ከቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ስሆን በጣም ጠበበኛ፣ አስተዋይና መንፈሳዊ የነበሩ ስሆን ለቅድስና ማእረግ ያበቃቸው ሁለት ዋና ዋና  ተጋብራት መካከል በቀዳሚነት የምፈረጀው ለምስጢረ ንስሓ ያላቸው ልዩ ፍቅርና ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ደከመኝ ሰላቸኝ ሳይሉ በታላቅ ጥበብና ትዕግስት በብዙ ሺ የምቆጠሩ ሰዎችን በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንድመለሱ በማድረጋቸውና ለተጠሩበትና ለተሰጣቸው መንፈሳዊ ስጦታ እስከ መጨረሻ ታማኝ አገልጋይ ሆነው በመገኘታቸው መሆኑ ታውቋል።

ለማረገ ቅድስና በሁለተኛ ደረጃ ያበቃቸው ተግባር ደግሞ መንፈሳዊ ህብረት በቤተ ክርስትያን እንድኖርና ቤተ ክትስትያን በታላቅ እምነትና በእግዚአብሔር በመተማመን ያለምንም ፍርአት ወደ ፊት መጓዝ እንዳለባት በአጽኖት ይገልጹና ያስተምሩ ስለነበረና በተለይም ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ በእግዚአብሔር በመተማመን እግዚአብሔር የፍቅር አምላክና መሓሪ መሆንንም በመግለጽ ሕዝቦች ሁሉ ያለማቋረጥ እጁን ዘርግቶ እንደ አባት ወደ ምጠብቃቸው  እግዚአብሔር እንድመለሱና በፍቅርና በሰላም ልኖሩ እንደምገባ ያሳስቡ ስለነበርና በተግባር በሕይወታቸው ያሳዩም መሆናቸው ለዝህ ለተከበረ ይቅድስና ማዕረግ በቅተዋል።  

በተያያዘ ዜና በዝህ ለ5 ቀን ያህል በምቆየው ልዩ የጸሎት ስነ ስረዓት ላይ የንስሓን አገልግሎትን ሳይሰላቹ ለምዕመናን ይሰጡና ለሓጥያተኛ ሰው ልዩ ትኩረት በመስጠት የምታወቁት ቅዱስ ፒዮ ፐትራልቺና ቅዱስ አጽም እንደ ምገኝ የታወቀ ስሆን የነዝህ ሁለት ቅዱሳን አጽም በቀዳምነት የተመረጠበት ምክንያት በሕይወት በነበሩበት ወቅት ሓጥያተኛ ሰው በሓጥያቱ በመጸጸት ወደ እግዚአብሔር እንድመለስ ባደርጉት ከፍተኛ መንፈሳዊ ተጋድሎ አማካኝነት ስሆን ይህ ተግባራቸው ደግሞ አሁን ከያዝነው የምህረት አመት ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ይህንን እንድል ምዕመናን ተጠቅመው ወደ እግዚአብሔር መንገድ በንስሓ እንድመለሱ ለማግዝ መሆኑ ታውቋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.