2016-01-30 10:33:00

የህማማት ሳምንት ለእኛ ለክርስትያኖች መንፈሳዊ ለውጥን እንድናመጣ አጋጣሚን የምፈጥር ወቅት ነው


እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በየካቲት 10.2016 ለምጀመረው የህማማት ሳምንት ምህመናን በቅድምያ በመንፈሳዊነት ይዘጋጁ ዘንድ ቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት ቅድመ መልእክት እንደገለፁት “የህማማት ሳምንት ለእኛ ለክርስትያኖች መንፈሳዊ ለውጥን እንድናመጣ አጋጣሚን የምፈጥር ወቅት ነው” ብለው ለዝህ የህማማት ሳምንት ላስተንትኖ እንዲሆን የተመረጠው መሪ ቃል “ከመስዋዕት ይልቅ ምህረትን እወዳለው” የምለው በማቴዎስ ወንጌል 9፣13 መሆኑን ገልፀዋል።

በተጨማሪም ምህረት ማድረግ የምያስችለን መንፈሳዊ ለውጥን በማምጣትና የተቸገሩትን በተለይም ደግሞ በራችንን ለምያንኳኩ ድኾች ምላሽ በመስጠት አካልዊ ምህረትን ማድረግ የምንለማመድበት ወቅት በሆኑ ይህንን ስንፈፅም ደግሞ የምህረት መልዕክተኞች በመሆን የእግዚአብሔር ምህረት መስካሪዎች እንሆናለን ማለት ነው ብለዋል ስል ዘጋብያችን አለሳንድሮ ጂዞቲ ዘግቧል።

በማስከተልም “የእግዚአብሄር ምህረት የሰውን ልብ በመለወጥ የእርሱን ማለትም የእግዚአብሔርን ፍቅር በምገባ እንድናውቅ ያደርጋል” ያሉት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር ደግሞ ይቅርባይ እንድንሆን አይልን ይሰጠናል” ብለዋል። የህማማት ሳምንት አዳዲስ ታምራትን በሕይወታችን በማስከሰት የእግዚአብሔርን ፊት በተቸገሩ እና በተጨነቁ ሰዎች ላይ እንድናይና ርህራሄን እንድኖረን ጉልበት የምናገኝበትና እመነታችንን በተግባር እንድናሳይ እድሉን የምሰጠን ወቅት ጭምር መሆኑን አመልክተው እግዚአብሔር የምፈርደን በሰራነው መልካም ሥራ ላይ ተመስርቶ በመሆኑ ለመንፈሳዊ እና ለአካልዊ ለውጥ ትኩረት መስጠት የጠበቅብናል ብለዋል።

የተቸገሩትንና ድኾችን በመርዳት ምህረትን በትግባር ማሳየት ህሊናን የምያነቃና የምያስደስት ተጋብር ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን በድኾች ፊት ላይ የምናያቸው ጉስቁልና የክርስቶስን መከራና ስቃይ መገለጫዎች በመሆናቸው፣ እነዝህን የተቸገሩትን የህብረተሰብ ክፍል መርዳት ማለት ክስቶስን መርዳት ማለት ስልሆነ እግዚአብሔር ምህረቱንና ፍቅሩን የምለግሰን እኛም መሀሪና ፍቅርን በተግባር የምናሳይ ስንሆን ብቻ ምሆኑን ተረድተን እግዚአብሔር ምህረቱንና ፀጋውን እንድሰጠን ለድኾች ተኩረት ልንሰጥ ይገባል ብለዋል።

በእራስ ወዳድነት ላይ የተመሰረት ሀብትና ስልጣን ማካበት ሕይወታችን ደስተኛ እንድትሆን አያደርጋትም ያሉት ቅዱስ አባትችን በአንጻሩ ሀብትን ለግል ጥቅም ብቻ ማጋበስ ሕይወታችን መራራ እድትሆንና ትርጉም የለሽ ሕይወት እንድንኖር ያደርጋል ብለዋል። ይህንን ለመረዳት ብዙ ርቀት ሳንሄድ በቀላሉ በሉቃስ ወንጌል በምዕራፍ 16፣19-31 የተጠቀሰውን በሐብታም ሰው ደጅ ቁጭ ብሎ ይለምን የነበረውን የአላዛርን ታሪክ ማወቅ ብቻ በቂ ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን “ዛሬም ብሆን ክርስቶስ በአላዛርና በሌሎች ድኾች ተመስሎ መንፈሳዊ ለውጥ እንድናደርግ ሁላችንም በመለምን ላይ ስለምገኝ ከሀብት ጋር ያለንን ቁርኝነት አስወግደን እየቀረበልን ያለውን የመንጊፈሳዊ ለውጥ ጥሪ ተቀብለን በእግዚአብሔር ምህረት እድንታቀፍ የምያሳስበን ወቅት ጭምር መሆኑን ገልፀዋል።

በመጨርሻም “ልድሆች በራቸውን የምዘጉ ሁሉ በሕይወታቸው በፍፁም ደስታኛ ልሆኑ አይችሉም ብለው አሁን ባለንበት በ20ኛው ክፍለ ዘመን ዓለማችን በአብዛኛው በተሳሳተና ሀብት እንደ እግዚአብሔር እንዲመልክ ተደርጎ የተወጠነ እርዮተዓልም እየተስፋፋ በመምጣቱ ትኩረት ለሰው ልጅ ተንፍጎ በምትኩም ለሳይንስና ለተክኖሎጂ ከፍተኛ ተኩረት በመስጠት በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረ ሰው እየተገለለ በምትኩም ጥቂቶችን ብቻ ተጠቃሚ የያደርግ ስረዓት እየተንሰርፋ እንደምገኝ አውስተው ይህንን ተግባር እየፈጸሙ የምገኙ ሰውችንም ልብ ክርስቶስ በድኾች ተመስሎ እያንኩኳ ስለምገኝ የምያልፈውን ሀብትና ዝናንን ትተን የማያልፈውን የእግዚአብሔርን ፀጋ እንድለብሱ ጥሪ የምደረግበት የህማማት ሳምንት እንድሆን ያስፈልጋል በለው ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

                                                        








All the contents on this site are copyrighted ©.