2016-01-29 16:25:00

ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን


እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን ታስቦ የሚውለው ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ እንደ ማሪያም በመሐሪው ኢየሱስ መታመን፣ እርሱ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” በሚል ርእስ ሥር መልእክት ማስተላለፋቸው የህሙማንና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዝይግሙንት ዚሞውስኪ በዋና ጸሓፊዎቻቸው በብፁዕ አቡነ ዣን ማሪ ማተ ሙሲቪ ሙፐንዳዋቱና በአባ አጉስቶ ቸንዲ እንዲሁም በቅድስት መሬት ካቶሊካውያን ጉባኤ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ በአባ ፒየትሮ ፈለት ተሸኝተው እ.ኤ.አ. ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ አስታውቀዋል።

ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን በየዓመቱ የሚከበር ሲሆን በየሦስቱ ዓመት ደግሞ በቅድስት መሬት ናዝሬት ከተማ ለየት ባለ መንፈሳዊና ባህላዊ መርሃ ግብር አማካኝነት ደምቆ የሚከበር መሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት በማስታወስ፦ በዚህ እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምሕረት ዓመት በዚያች ኢየሱስ የፈውስ ተአምራት በፈጸመባት በተለይ ደግሞ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ቀዳሚ ተአመር በፈጸመባት በናዝሬት የጋሊለያ ከተማ በደመቀ ሁኔታ ማክበር ለሕመምተኞችና በስቃይ ላይ ለሚገኙት ቅድስት ማርያም ቅርብ መሆንዋ የሚመሰክር ነው። አደገኛ በሽታ የሰው ልጅ ህልውና ለቀውስ የሚያጋልጥ አበይትና ጥልቅ የህልውና ጥያቄዎችን የሚደቅን ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት ለፈተና ሲጋለጥ እምነት ያለው አዎንታዊ እምቅ ኃይል ይገለጥልናል በማለት ያሰምሩበት ሃሳብ ብፁዕ አቡነ ዚሞውስኪ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማተጋባት፦ ለሚሰቃየው መልካም ማድረግና ስቃይ ተስፋ ለመቁረጥ ሳይሆን በተስፋ ለተካነ መልካም ነገር ተለውጦ የህመምተኛው ስቃይ ስለ ሌሎችና ስለ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጌታ የሚያርግ መሥዋዕት ሆኖ በአሜን ለማቅረብ እንዲችሉ ሊደገፉ ይገባቸዋል። ብዙውን ጊዜ ህመምተኛው ከስቃዩና ካጋጠመው ሕመም ለማላቀቅና ለመፈውስ ሳንችል ስንቀር ተስፋ እንቆርጥ ይሆናል፣ ይኽንን ዓይነቱ ተስፋ የመቁረጡ አዝማሚያ አግለን ወደ ሕመምተኛው መሄድና ቀርቦ ለመደገፍ ተጠርተናል። ታማሚው የሌላው ሰው ሰብአዊ ቅርበትና መሐሪው ልብ እጅግ ይፈልጋል፣ ስለዚህ ኢየሱስ እንዳደረገው ለማድረግ ሳንችል ብንቀርም በእርሱ ታምነን ለህሙማን ቅርብ እንሁን እንዳሉ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።

የሰው ልጅ ጤንነት በመንከባከቡ ኃላፊነትና ጥሪ የተሰማሩ የሕክምና ባለ ሙያዎች የሚሰጡት ድንቅ አገልግሎትና አስተዋጽኦ ዓቢይ ግምት በመስጠት በሙያቸው እንዲበረቱና ተገቢ ሕንጸት ጭምር በማገኘት በሚሰጡት አገልግሎት ወቅታዊው የሰው ልጅ ስቃይ ለመጋፈጥ የሚችል እንዲሆን በሰብአዊና በስነ ሙያ በቀጣይነት እንዲታነጹ አደራ በማለት፣ የሕክምና አገልግሎት በቅድሚያ ሞያ ከመሆኑ በፊት ጥሪ ነው። ስለዚህ ጥሪ መሆኑ ግንዛቤው ተሰጥቶት የሚሰጠው አገልግሎት የተዋጣለት ይሆናል፣ የአንድ ስልጡን አገርና ሕብረተሰብ መመዘኛውም ለህሙማን የሚሰጠው ድጋፍ ነው እንዳሉ የገለጡት ልኡክት ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የተሳተፉት አባ ቸንዲ ይላሉ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከየካቲት 7 ቀን እስከ የካቲት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. ለህሙማን የሙሉ ሐጢአት ስርየት ይሁን እንዳሉ ሲገልጡ አባ ፈለት በበኩላቸውም በህሙማን ቀን ምክንያት በቅድስት መሬት ናዝሬት በተልሔምና ራማላሕ ከተሞች የተለያዩ መንፈሳዊና ባህላዊ መርሃ ግብሮች እንደሚከናወኑ ገልጠው በሕሙማን ቀን ምክንያት ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ህሙማን መንፈሳዊ ነጋድያን ወደ ቅድስት መሬተ እንደሚነግዱና እነዚህ ነጋዲያን ለማስተናገድ ቅድመ ዝግጅቱ በሚገባ እየተከናወነ ነው እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.