2016-01-29 16:27:00

ብፁዕ አቡነ ዙፒ፦ ቤተ ክርስቲያንና ቲዮሎጊያ በቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ


እ.ኤ.አ. ጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የመካከለኛው ክፍለ ዘመንና የምዕራቡ ዓለም በክርስቲያናዊ አሳቤ ታሪክ ላይ አቢይ አዎንታዊ ተጽእኖ ያሳደረው የቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ ዓመታዊ በዓል አክብራ መዋልዋ ሲገለጥ የቦሎኛ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ማተዮ ዙፒ በሳቸው በሚመራዊ ሰበካ ሥር በሚተዳደረው የኤሚሊያ ሮማኛ የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጭምር ጥልቅ ቲዮሎጊያ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ስለዚህ በጸሎት ከጌታ ጋር በሚኖር ጥልቅ ግኑኝነትና በቲዮሎጊያዊ ጥናት የተሸኘ አገልግሎት መሆን አለበት እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሉካ ተንቶሪ ገለጡ።

ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቲዮሎጊያ ያሻዋል ቲዮሎጊያም በተራው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ይሻል፣ ስለዚህ ሁለቱ የአገልግሎት ዘርፎች በመደጋገፍ የሚከወኑ ናቸው፣ እርስ በእርሳቸው አይነጣጠሉም ያሉት ብፁዕ አቡነ ዙፒ እንደ አብነት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ጠቅሰው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አለ ቲዮሎጊያ ባዶ ተግባር ሆኖ ነው የሚቀረው፣ ይዞታ የሌለው ባዶ ተግባር ይሆናል፣ በተመሳሳይ መልኩም ቲዮሎጊያ አለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ባዶ እሳቤ ሆኖ ይቀራል፣ ቲዮሎጊያ ከአስፍሆተ ወንጌል ጋር የሚነጻጸር አስፍሆተ ህልዩአዊና ታሪካዊ አስተንትኖ መሆን ይገባዋል። ጥንቃቄ የተሞላው ጥልቅ ነገረ መለኮታዊ ንባብ ታሪክ የመተንተን ብቃት አለው እንዳሉ ተንቶሪ አስታወቁ።

ቅዱስ ቶማስ ዘአኵይኖ በእምነትና በእሳቤ ሰው ልጅ የሚያቀርበው ተጋርጦ በጥልቀት ያስተውል ነበር፣ ስለዚህ ዛሬ ሰብአዊ የሆነ ነገር ሁሉ ሊያስፈራን እንደማይገባው በቲዮሎጊያዊ ጥልቅ ጥናቱ አማካኝነት ያሳስበናል፣ በቸልተኝነት ሊታይ የሚገባው ምንም ነገር የለም። ምክንያቱም ምንም ነገር ሲባል ባዶነት የሚያመለክት በመሆኑም መፍነሳዊና አእምሮአዊ አስተንትኖ አይጠይቅም ያሉት ብፁዕ አቡነ ዙፒ አያይዘው፦ ቲዮሎጊያዊ ስነ ምርምር ብቻ ሳይሆን ተግባራዊነትንም ይጠይቃል፣ በተለይ በዚህ እየተኖረ ባለው የምሕረት ዓመት ሊቀርበንና እኛን ለመፈለግ ያማይሰለቸው ምሕረት መከታችን ነው። ቅዱስ ዮሓንስ 23ኛ እንደ ሚሉትም ምኅረት የአእምሮ መከላከያ ነው። ቲዮሎጊያ በእርግጥ ጥልቅ ጥናት ያስፈልገዋል፣ ሆኖም ጥልቅ ጥናት ያስፈልገዋል በሚለው ሐሳብ ብቻ ታጥሮ ባስመሳይነት ሊበከል አይገባውም እንዲህ በመሆኑም በቃልና በተግባር የተሸኘ መሆን አለበት እንዳሉ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.