2016-01-27 16:23:00

ብፁዕ ካርዲፍናል ባኛስኮ፦ ብፁዓን ጳጳሳት ቤተሰብ በመከላከል ተግባር ውህደት አላቸው


የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር የጆኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ በአሁኑ ወቅት የኢጣሊያ መንግሥት ቤተሰብ በሚመለከት ርእስ ሥር ሊያጸድቀው ያቀረበው የሕግ ንድፍ ዙሪያ እ.ኤ.አ. ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የብፁዓን ጳጳሳት ቋሚ ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ አስታውሰው ቤተሰብ የቤተ ክርስቲያን የማኅበርሰብና የኅብረተሰብ ማእከል ነው። ከዚሁ ጋር በማያያዝም ብፁዓን ጳጳሳት ቤተሰብ በመከላከሉ ተግባር ሁባሬ እንዳላቸው በማረጋገጥ ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ለከፋ ችግር የተጋለጠው ቤተሰብብ በሥራ አጥነት  የተጠቃው ቅድሚያ ተሰጥቶት መንግሥት የሕዝብ ችግር መፍትሔ በማፈላለጉ ሂደት እንዲተጋና በኤውሮጳ የሚታየው የስደተኞች ጸአት ኤውሮጳዊ መልስ ያሻዋል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሪኤላ ቸራዞ አስታውቀዋል።

ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ በብፁዓን ጳጳሳት ዘንድ ምንም አይነት መክፋፈል የለም

ምኞታችን መከባበር የሁሉን ሰብአዊ መብትና ክብር ማክበርና መንከባከብ የሕይወት አግባብ የሚያደርግ መንግስትና የቤተሰብ ልክነት ያለው አገር ግንባታ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ፍትህ የተካነው የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ሰው የሌላው ሰው ሰብአዊ መብትና ጥያቄ ሊሆን አይችልም፣ የሚወለደው ልጅ ስለ ገዛ እራሱ መፈቀር ይኖርበታል። የሚወለደው ሕፃን የገዛ እራሱ ሰብአዊ መብትና ክብር ያለው ዋስትናና እርጋታ ያሻዋል። ስለዚህ አባትና እናት ለአንድ ልጅ ምሉእ እድገት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፣ መንግሥት በአባላት ብዛት አቢይ ለሆነው ቤተሰብ ልዩ ድጋፍ የማቅረብና እንዲሁም የወሊድ ቁጥር የሚያበረታታ የቤተሰብ ፖለቲካ ሊኖረው ይገባል እንዳሉ ቸራዞ ያመለክታሉ።

የኤኮኖሚ ቀውስ መሻሻል በተጨባጭ የሚታይ አይደለም

ብፁዕነታቸው የኢጣሊያ ወቅታዊው የኤኮኖሚ ጉዳይ ጠቅሰው ኤኮኖሚ እየተሻሻለ ነው እንደገት እየተረጋገጠ ነው የሚባለው ዜና በእውነቱ በተጨባጭ የሚያረጋግጠው ጉዳይ መታየት ይኖርበታል፣ ይኽ ደግሞ የሥራ እድል በመፍጠር በሥራ አጥነት የተጠቃው የኅብረተሰብ ክፍል መደገፍ በሚል የውሳኔ ትግባሬ ፖለቲካ አማካኝነት የኤኮኖሚው የመሻሻል ወጤት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ካልሆነ እድገት አለ ብሎ መናገሩ ፖሊቲካዊ ቅስቀሳ ነው የሚሆነው።

የስደተኛው ጸአት፦ ኤውሮጳዊ መፍትሔ

በአሁኑ ሰዓት በኤውሮጳ እየታየ ያለው የስደተኛው ጸአት ጉዳይ ስደተኛው ለሚገባበት አገር መተው ሳይሆን ኤውሮጳዊ መፍትሔ ያሻዋል ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ባኛስኮ በማስከተል፣ እግጅ የሚያሳዝነው በተለያየ ምክንያት ተገዶ የሚሰደደው ዜጋ የሚያጋጥመው የሞት አደጋ ለምንኖርበት ዓለም የሕሊና ጥያቄ ነው። የምንኖርበት ዓለም ከግድ የለሽነት ባህል ለማላቀቅ ሁሉም እንደየ ኃላፊነት የተቻለው ማድረግ ሳይሆን ለዚሁ ጉዳይ ካለ መታከት ማገልገል ይኖርበታል ካሉ በኋላ እየተኖረ ያለው የምሕረት ዓመት በማስታወስ ይኽ ቅዱስ ዓመት ሰውንና ነገሮችን በእግዚአብሔር ዓይን እንመለከት ዘንድ የሚያነቃቃን የጌታ ምሕረት እንደሚያስተናግደን ሁሉ እኛም ቅዱስ በር በመሆን ሌላውን የሚያስተናግዱ ሆነን እንገኝ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.