2016-01-25 16:14:00

ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ፦ ጋዜጠኞች ምኅረት የት እንደሚያስፈልግ አሳውቁ


ሮማ በሚገኘው ቅድስተ ማሪያም ዘ ሞንተሳንቶስ ባዚሊካ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ  የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበርና ቅዱስ የምኅረት ዓመት አስተባባሪ ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችና ጋዜጠኞች ደራሲያን ጠባቂ ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘሳለስ እ.ኤ.አ. ጥር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በዓል ምክንያት የምኅረት ዓመት ሥር  ከጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ደራሲያን ጋር የተገናኙ ሲሆን ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች እ.ኤ.አ. የካቲት 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የባህል ጉዳይ ከሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ፣ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሰባኬ ቤተ ጳጳስ ክቡር አባ ራኒየሮ ካንታላሜሳ፣ ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቦዜ ገዳም አበ እምኔት አባ ኤንዞ ቢያንኪ፣ እ.ኤ.አ. ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ኅየንተ ብፁዕ አቡነ ዳሪዮ ኤዶአርዶ ቪጋኖ ጋር እንደሚገናኙ ያሳወቁ ሲሆን ብፁዕነታቸው ከጋዜጠኞች ጋር “እውነት ባንድ ሰው ላይ እማኔ ማኖር፣ እውነት ታማኝነት ማለት ነው” በሚል ርእስ ሥር አስተምህሮ መስጠታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ኤውጀኒዮ ሙራሊ አስታውቀዋል።

የመገናኛ ብዙኃን ብዙዉን ጊዜ ቀዳሚ ገጽ የሚሰጡት ዋና ዜና አድርገው የሚያቀርቡት አመጽ ግጭት ጦርነት ቅትለት የመሳሰሉት ዜናዎች ናቸው። አሉታዊ ነገር ሁሉ ቅድሚያ ይሰጠዋል፣ ሆኖም የሚከሰቱት የሚፈጸሙት መልካም ነገሮች ሁሉ ይዘነጋሉ፣ ሰው አለ ደግነትና አለ ፍቅር መኖር አይችልም፣ በመሆኑም የመገናኛ ብዙኃን ይኸንን በማስተዋል ሁሉን ነገር አገናዝበው ተጨባጩ ሁነት በትክክል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ይኽ ደግሞ የምኅረት ተግባር ጋር ማጠቃለል ይቻላል፣ ሰውን በአሉታዊ ዜና ብቻ ከማስጨነቅ አወንታዊ ዜናዎች በማቅረብ ተስፋው በማነቃቃት መደገፍ ይኖርባቸዋል።

በዓለም የመገናኛ ብዙኃን የሚከተለው ያሠራር ሥልት መቀየር ይኖርበታል፣ ስለዚህ የአስተሳሰብ የባህልና ለሰው ልጅ መሠረታዊ የሆነውን ጉዳይ ለማቅረብ የሚያግዝ ለውጥ ያስፈልጋል፣ ይኽ ደግሞ የመገናኛ ብዙኃን ያለባቸው ዓቢይ ኃላፊነት ያመለክታል። ከማናጋት ማረጋጋት፣ ከጦርነት ሰላም የሚለው በተለያዩ የዓለማችን ክልል የሚከናወኑት ጥረቶች ላይ ማተኰር ይኖርብናል፣ እንዲህ ባለ መልኩም በሰው ልጅ መካከል መቀራረብ መግባባት እንዲኖር መደገፍ ያስፈልጋል እንዳሉ ሙራሊ ገለጡ።

አየተኖረ ያለው ቅዱስ ዓመት በሮማ በሚገኙት አራቱ አበይት ባዚሊካ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ በዓለም በሚገኙት ካቴድራሎች ቁምስናዎችና አቢያተ ክርስቲያን ቅዱስ በር ተከፍተዋል። የመገናኛ ብዙኃን ይኸንን ተጨባጭ ሁነት በትክክል በዚያ ጦርነትና ግጭት ባለበት ክልል ቅዱስ በር ለመክፈት የተከናወኑት የሊጡርጊያ ሥነ ሥርዓቶች የሚያወሱና የምኅረትና የሰላም መሣሪያ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ሙራሊ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.