2016-01-23 08:42:00

ክርስትያኖች የሆንን ሁላችን ለአንድነት በምደረግ ውይይትና እንቅስቃሴ በራሳችንን መክፈት ግድ ይለናል


እንደሚታወቀው የያዝነው ሳምንት ለክርስታይኖች ሕብረት ፀሎት የምናደርግበት ወቅት በመሆኑ ለዝህ የፀሎት ሳምንት እንደ መሪ ቃል ሆኖ የተመረጠው የእግዚአብሔር ቃል ደግሞ ከመጀመሪያ የሓዋሪያው ጴጥሮስ መልዕክት ከምዕራፍ 2፣9 የተወሰድው “እናንተ ግን ከጨለም ወደ አስደናቂ ብርሃን የተጠራችሁ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉስሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ለእርሱ የመረጣችሁ ሕዝብ ናችው” የምለው መሆኑ ይታወቃል።

በዝህ መሪ ቃል ላይ ተመስርቶ ከተለያዩ ሀይማኖቶች ለተውጣጡ የክርስትያን ሕበረት እንቅስቃሴ ተወካዮች “በቤተ ክርስትያን ሕብረትን ማምጣት ይቻላል ወይ?” ብላ ጋዜጠኛችን አንቶነላ ፓሌርሞ ላቀረበችው ጥያቄ በቅድምያ ሄንዞ ቢያንክ የተባለ ተሳታፊ እንደመለሰው “ክርስትያኖች በመሰረቱ መለያየት አልነበረባቸውም” በማለት ጀምሮ “ ነግር ግን ያለመታደል ሆኖ ልዩነቱ ልከሰት የቻለው በተክርስትያን ታሪክ ውስጥ በተከሰቱ አወዛጋቢ ገጠመኞች መሆኑን አውስቶ እኛ አሁን ባለንበት ወቅት የክርስትያን ሕብረትን መፍጠር የሰው ልጅ ፍላጎትን ሟሟላት ብቻ ሳይሆን፣ ክርስቶስም የምፈልጋት ቤተ ክርስትያን አንድነት ያላትን ቤተ ክርስትያን በመሆኑ ሁላችንም የሕብረቱን እንቅስቃሴ እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባናል ብልዋል።

በዝህ በክርስቶስ አሳብ ላይ ተመስርተን ክርስትያኖች የሆንን ሁላችን ለአንድነት በምደረግ ውይይትና እንቅስቃሴ በራችንን መክፈት ግድ ይለናል ካሉ ቡኋላ በሩን ለክርስትያን ሕብረት ውይይት የማይከፍት ቤተ ክርስትያን ካለ፣ እርሱ እራሱን እንደ ክርስትያን ልቆጥር አይገባም በማለት አስተያይቱን አጠናቋል።

አባ ትራያን ቫልድማን በጣልያን የሮማንያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን አስተዳዳሪ በበኩላቸው ስለ መሪው ቃል አስፈላጊነት ስገልፁ “ክርስትያኖች ሁሉ ሕበረት ልንፈጥር ይገባል የምንለው ክርስቶስ የቤተ ክርስትያን እራስ በመሆኑና በዝህም ላይ ተመስርተን በየጊዜው በፀሎተ ሓይማኖት “ቤተ ክርስትያን አንድ መሆኗንና ሁልም ክርስታያኖች በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን ስለምናውጅ ምንም እንኳን በተለያየ መልካ ምድርና ባህል ብንኖርም በመግባባት እና ሕብረትን በምፈጥር መልኩ ተቀራርበን ስንኖር ላሰብነው እና እየለፋንበት ለምንገኘው የክርስትያኖች ሕብረት መሰረት መጣል እንችላለን ብለዋል።

በመጨረሻም “ቤተ ክርስትያን ተለያይታ መኖር ትችላለች ወይ?” ተብለው ከጋዜጠኛ ለቀረበላቸው ጥያቄ የባቲስት ቤተ ክርስትያን ተወካይ የሆኑ ሉካ ኔግሮ ስመልሱ “ ቤተ ክርስትያን በፍፁም ተለያይታ እስከ መጨረሻ መኖር አትችልም ካሉ ቡኋል በታሪክ የተፈፀሙ የተለያዩ ችግሮችን በማጉላት ልዩነታችንን ማስፋት ሳይሆን የምጠበቅብን በየጊዜው የምያቀራርቡንን ነግሮች በመሻት ልክ አሁን እንደምናደርገው በአመት አንዴ ብቻ ለአንድ ሳምንት የምቆይ ቀን መድበን ለክርስትያኖች ሕብረት መፀለይ ብቻ ሳይሆን የምጠበቅብን በእየዕለት ተግባራችንም ሁሉ ለዝህ ሕብረት መምጣት የበኩላችንን ጥረት ማድረግና መፀለይ ይጠበቅበናል በማለት ንግግራቸውን አጠናቋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.