2016-01-23 08:14:00

ቅናት እና ምቀኝነት እንደ አረም በውስጣችን የምያድጉ ክፉ የሓጥያት መንሰሄዎች ናቸው


በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 21.2016 በቅድስት ማርታ የፀሎት ቤት ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮስ ባደርጉት እለታዊ ስርአተ ቅዳሴ ላይ እንዳወሱት የእለቱ የስርዓተ ቅዳሴ የቀን መቁጠርያ የምያሳየውና እለቱ የምከበረው ድንግል እና ሰማዕት የሆነችውን ቅድስት አኜስን በማሰብ ነው ካሉ ቡኋላ በቃለ ወንጌል አስተንትኖዋቸውም ላይ ቅናት እና ምቀኝነት በክርስትያን ማህበረሰብ እና በአጠቃልይ በሰው ልጆች ሕይወት ውስጥ የምንፀባረቁ ክፉ ባህሪያት መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ደግሞ በየቀኑ በምላሳችን ብዙ ሰዎችን እየገደልን ስለምንውል ከንዝህ ትልቅ ሓጥያት እንድንሰራ ከሚገፋፉን ስሜቶች እግዚአብሔር እንድጠብቀን በቅድስት አኜስ አማልጅነት ጸሎታችንን ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይጠበቅበናል ብለዋል ስል ሰርጆ ቼንቶፋንቲ ዘግቡዋል።

ቅናት እና ምቀኝነት እንደ አረም በውስጣችን የምያድጉ ክፉ የሓጥያት መንሰሄዎች ናቸው ያሉት ቅዱስ አባታችን በመጀመሪያው መጻሓፈ ሳሙኤል 18.6-9፣19.1-7 እንደተጠቀሰው የእስራኤል ንጉስ የነበረው ንጉስ ሳኦል፣ ዳዊት ማንኛውንም አይነት ተለዕኮ በሚገባ የሚፈፅም መሆኑን በተረዳ ጊዜ የጦር ሰርዊቱ አዛዥ እንድሆን እንደሾመው እና ዳዊትም በብዙ ሺ የምቆጠር የፍለስጤማዊያንን ጦር በመደምሰሱ ሕዝቡ “ሳኦል ሺ ገደለ ዳዊት አስር ሺ ገደለ” ብለው በድስታ በዘመሩበት ወቅት በቅናት በዳዊት ላይ እንደተነሳ የሚያወሳ መሆኑን ከገለፁ ቡኋላ  ሳኦል ሁል ጊዜ ዳዊት ይከዳኛል በምል ሓሳብ ላይ ተመስርቶ በጥርጣሬ ይመለከተውና ልያስገድለውም ያስብ እንደነበረ አስታውሰው ነገር ግን ልጁን ዮናታንን ካማከረ ቡኋል ይህንን ሓስቡን ለጊዜው እንደቀየርና ብዙም ሳይቆይ የቅናትና የጥርጣሬ ስሜቱ ተመልሶ እንደመጣበት በዳዊት ላይ ያሰበውን ክፉ ነገር ለመፈፀም በድጋሜ እንደተነሳሳ የዛሬ የመጀመሪያ ምናባብ ያስረዳል በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን ጀምረዋል።

በመቀጠልም ቅናት አሉ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮስ በሕይወታችን እየተመላለሰ የምቀኝነትን ስሜት የሚፈጥር “አደገኛ በሽታ ነው” ካሉ ብኋላ፣ ከሁሉም የከፋው ነገር ምቀኝነት መሆኑን አስምረው፣ ምቀኝነት ደግሞ ክፉ ነገሮችን እንድንፈፅም ስለ ምያነሳሳን ትልቅ እና አደገኛ ሓጥያት ነው በለዋል። ቅናት እና ምቀኝነት በልባችን ውስጥ እንደ አረም በማደግ መልካም ፍሬን እንድያፈራ በእግዚአብሔር ቃል በልባችን ውስጥ የተተከለውን እፅዋት እንዳያድግ ሰለምከለክለውና ተፅኖ ስለሚፈጥርበት የልባችንን ሰላም በመንሳት የታመመና የተሸበረ ልብ እንዲኖረን ያደርጋል ብለዋል።

በተጨማሪም ደግሞ በቅናትና በምቀኝነት የተለከፈ ልብ ሁል ጊዜ የሚያስበው ክፉ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም ብቻ በመሆኑ መፃሓፍ ቅዱሳችን እንደሚለው” ሞት ወደ አለም የገባው በስይጣን ቅናት ነው” እንደሚለው ቅናት የሁሉም ክፉ ነገሮች መሰረት በመሆኑ ከዝህ ከፉ ስሜት ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል።

አሁን የምንኖርበት ዘመን በቅናት እና በምቀኝነት የተለከፈ መሆኑን ያስታወሱት ቅዱስ አባትችን  ቅናተኛ ልብ ያለው ሰው ሌላው ከእርሱ የተሻለ ነገር ባገኘ ቁጥር በቅናት የምቃጠልና የተሸበረ ልብ ስለሚኖረው ምንም ጊዜ ብሆን የተረጋጋ ሕይወት ልኖር አይችልም ብለዋል።

በመጨረሻም የካህናት አለቆች በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሞት ፍርድ ያስፈረዱበት በቅናት መንፈስ ተነሳስተው መሆኑ ይታወቃል ያሉት ቅዱስ አባታችን የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል እናደምያስተምረን በእኛ በሁላችን ልብ ውስጥ የቅናት ስሜት ካለ፣ ይህ የቅናት ስሜት በሌሎች ላይ ክፉ ነገርን እንድንፈጽም ስለ ምያበርታታን ከሁሉም በላይ ደግሞ ቅናት የሁሉም ሓጥያት ምንጭ መሆኑን በመረዳት ይህንን ክፉ ሓትያት ለማስወገድ እግዚአብሔር ፀጋውን እንዲሰጠን ልባችንን ክፉ ነገር እንድናደርግ ለምገፋፋን ቅናትና ምቀኝነት ዘግተን በምትኩ ደግሞ እግዚአብሔር በፀጋ እንድሞላው መጸልይ እና ላባችንን ለርሱ ብቻ መክፈት ይጠበውብናል በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቀዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.