2016-01-20 16:26:00

የፎኮላሬ እንቅስቃሴ “በወንጌል ላይ የተመሰረት ሕይወት ልንኖር ያሰፈልጋል”


በአለም የሚገኙ ክርስትያኖች ሁሉ ክርስቲያናዊ እሴቶችን በተቀናጄ መልኩ ለሰው ልጆች ማስተላለፍ እንዲችሉ በቀዳሚነት የምያስፈልጋቸው ህብረት መፍጠር በመሆኑ ይህንንም አንድነት ለማምጣት የተልያዩ ተቋማት ተደራጅተው እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል። ይህንንም አሳብ መሰርት በማድርግ የፎኮላሬ እንቅስቃሴ በክያራ ሉብኪ ተመስርቶ ባለፉት አሥርተ አመታት በክርስቲያኖች መካከል ህብረትን ለመፍጠር እየተንቀሳቀሰ እንድሚገኝና መሰረታዊ የሆኑ ልዩነቶች እየተፈቱ መምጣት መጀመራቸውን የመጀመሪያዋ የአንግሊካን ፎኮላሬ እንቅስቃሴ መስራች ከሌስለይ ሄሊሰን ጋር ዘጋቢያችን ሮዛሪዮ ቱሮኖሎነ ባተደረግው ቃለ ምልልስ መረዳት ተችሏል።

ሌስለይ ሄሊሰን የፎኮላሬ እንቅስቃሴ በመጀምሪያ እናዳውቅ ያደረገኝ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በ1966 የተዋወኩት በአንድ ፍራንችስካዊ ወንድም አማካይነት ብለው በጣም የነካኝ እና ይህንን እንቅስቃሴ በአንግሊካን ቤተ ክርስትያን እንድመሰርት የገፋፋኝ ደግሞ የዚህ እንቅስቃሴ አባላት “በወንጌል ላይ የተመሰረት ሕይወት ልንኖር ያሰፈልጋል” የሚለው መርህ ቃል መሆኑን በመግለፅ መሪ ቃሉ በራሱ ለምስረታው ከፍተኛ አስተዋጾ እንዳደርገም ገልፀዋል። ምክንያቱንም ስትገልፅ የእግዚአብሔር ቃል ለሁላችን የተሰጠ መርህ በመሆኑና ሁሉም ክርስትያኖች የቤተ ክርስቶያናቸው አስተምሮ መሰርት ያደረገው በዚሁ የወንጌል ቃል ላይ ተመስሪቶ በመሆኑ እኔ እንደምረዳው የእግዚአብሔር ቃል ሁላችንም አንድ እንድንሆንና ህብረት እንዲኖረን ያስችለናል በለዋል።

በዚህ በያዝነው ሳምንት ለክርስትያን ህብረት በሚደረገው ፀሎት ላይ መርህ ቃል እንዲሆን የተመረጠው “ የተጠራነው የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ለመመስከር ነው” የሚለው ስሆን እርሶ በዚህ መሪ ቃል ልይ ምን አስተያየት አሎት ተብሎ ከጋዜጠኛ ለከረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “ ይህ መሪ ቃል የተወሰደው ከአዋሪያው ጴጥሮስ መልዕክት ሲሆን አላማውም በጊዜው ለነበሩ ክርስትያኖች እግዚአብሔር ያሳያቸውን ድንቅ ፍቅርና እንክብካቤ ለመግለፅ ሲሆን በማከተልም “የተመረጥ ሕዝብ፤ ቅድስት ሀገር፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ” የሚሉት ቃላት የሚያሳዩን ደግሞ እኛ ክርቲያኖች ሁላችን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን በመሆኑ ምንም እንኳን ብዙ መሰረታዊ የባህልና የአመለካከት ልዩነቶች ቢኖሩብንም እንዚህን ልዩነቶቻችንን በማክበርና የልዩነት ውበት ነው” በሚለው መርህ ላይ ተመስርተን በመከባበር ልንኖር ያስፈልጋል በለዋል።

በማከልም ለኔ አስፈላጊ እና ዋናው ነገር ህብረት ማለት በሁሉም ነገር መመሳሰል ማለት እናልሆነ ማሳወቅ እፈልጋለው ካሉ ቡኋላ ልታወቅ የሚገባው ጉዳይ ደግሞ ህብረት እየፈጠርን በምንመጣበት ወቅት እርስ በርሳችን እየተዋወቅን፣ እየተግባባንና የተቀራረብ ስንመጣ እግዚአብሔር በሕይወታችን ያደረገልንን ድንቅ ሥራ እንዱ ለአንዱ የመሰከረ በእግዚአብሔር ፍቅር ታቅፈን እንድንኖር የምመክረንና ሌሎችም እኛ በምናሳየው ፍቅር ተማርከው ህብረታችንን እንድቀላቀሉ የሚያበርታታን ቅዱስ ቃል ነው ብለዋል።

እውነተኛና ከልብ የመነጨ ህብራት ልመሰረት የምችለው ይቅር መባባል ስንችል ብቻ ነው። እኛ አሁን ያለንበት አመት ደግሞ በር.ሊ.ጳጳስ የምህረት አመት ተብሎ ተሰይሙዋል። ይህ የምህረት አመት ለተጀምረው የክርስትያኖች ህበረት ንቅናቄ የምያበርክተው አስተዋፆ ያለ ይመስሎታል ወይ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ “እኛ በጀመርነው የፎኮላሬ ንቅናቄ ባገኘነው ልምድ መሰረት ህብረት ከእግዚአብሔር የምሰጥ ስጦታ መሆኑን ተረደትናል” ካሉ ቡኋላ “ነገር ግን ትክክለኛ ህብረት ልመጣ የሚችለው ፍቅር፣ ምሕረት፣ መተሳሰብ በለበት ቦታ በመሆኑ ይህ የምህረት አመት የምያበረክተው ትልቅ አስተዋፆ አለው ብለው በተለይም ደግሞ በኢየሱስ ስም በምንሰብሰብበት ጊዜ እርሱ በመሀላችን ስለምኖር የእርሱ ከእኛ ጋር መኖር ደግሞ ህበረትንና ምህረትን ስለምያጠናክርና መተማመንን በመፍጠር የበለጠ እንድንቀራረብ ስለምያደርግ የምህረት አመት ተብሎ መታወጁ በጣም ተገቢ እና ጠቃሚ ነው በለዋል።

በመቸረሻም ቅድስ ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮስ በቅርቡ ባሳተሙት “ላውዳቶ ሲ” ወይም በአማረኛ በግርድፉ ሲተረጎም “ይባርክ” በሚለው ሰንድ ላይ ክርስትያኖች በሙሉ በጋራ ለአለማችን ደህንነት እና ለአከባቢ ጥበቃ በጋር እንድሰሩ ማስገንዘባቸው ይታወቃል። በእርሶ አመለካከት ይህ የቅዱስ አባትችን ጥሪ ለተጀመረው ይክርስትያን ህብረት ምን አስተውፆ ልያበርክት ይችላል ወይ ? ተብሎ ለቀረበላቸ ጥያቄ ስመልሱ “ በትክክል ከፍተኛ የሆነ አስተውፆ ያደርጋል ብየ ሓስባልው ብለው በቅርቡ በእንግሊዝ ሀገር የሚገኙ ከትለያዩ አብያተ ክርስትያናት የተውጣጡ ወጣቶች በጎ ፍቃድ ካላቸው ሙስሊም ወጣቶች ጋር በምሆን ለአከባቢያቸው ጥበቃ ለማድረግ የዛፍ ተከላ ሥራ ያከናወኑ ስሆን ይህ የምያሳየው ደግሞ ክርስትያኖች ብቻ ስይሆኑ ሁሉም የአለም ማህበረሰብ ለአከባቢው ጥበቃ እንድያደርግ ጥሪ የምያቀርብ መፃፍ በምሆኑ ለክርስትያን ህብረት ልዩ ጥንካሬን የፈጠረ ሰንድ መሆኑን በመግለፅ ሓሳባቸውን ደምድመዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.