2016-01-20 16:39:00

አባ በተጋ፦ በተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ለውህደት ታልሞ የሚደረገው የጋራ ውይይት ወንጌላዊ ትውስብነት እንጂ ሥርዓተ ማክበር ማለት አይደለም


በየዓመት የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ስለ ክርስቲያኖች አንድነት ታልሞ በጋራ የሚያካሂዱት የጸሎት ሳምንት እ.ኤ.አ. ጥር 18 ቀን 2016 ዓ.ም. መጀመሩ ሲገለጥ፣ ይኽ የጸሎት ሳምንት በተለያዩ መንፈሳዊና ባህላዊ መርሃ ግብሮች አማካኝነት የሚከናወን ከመሆኑም ባሻገር ዘንድሮ ለየት የሚያደርገው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባወጁት ቅዱስ የምኅረት ዓመት ጋር የተሳካ መሆኑ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የጋራ ውይይት የሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር አባ ክሪስቲያኖ በተጋ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፦ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የጋራው ውይይት በምኅረት ዓመት ርእስ ሥር ማጠቃለሉ አቢይ ተጨባጭ ቲዮሎጊያዊ ትርጉም እንዳለው ያመለክታል፣ ስለዚህ ምኅረት የእግዚአብሔር ማንነት ወይንም መለያ ከሆኑት ባህርያት ውስጥ አንዱ ነው፣ ይኸንን ምህረት እንደ ክርስቲያን መጠን ክርስቲያን የሆነው ሁሉ ካልኖረው ከእግዚአብሔር ከገዛ እራሱና ከባለንጀራው ጋር መገናኘት አይችልም፣ በገዛ እራሱ የተዘጋ ይሆናል፣ እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ልጅ መሃሪ ነው፣ እግዚአብሔር ምህረቱ አለ ምንም አድልዎ ለሁሉም ሰው ልጅ የሚጸግው ከሆነ እኛም በተራችን መሃሪያን ሆነን መገኘት ይኖርብናል፣ በሰማይ እንዳለው አባታችሁ መሃሪያን ሁኑ ነውና ጥሪያችን።

የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የጋራ ጸሎት ሳምንት ምክንያት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት በዚህ አመጽና በደም መፋሰስ በተሞላውና እንዲሁም በቅጥ የለሽ ዓለማዊነት ባህል በተጠቃው ዓለም በቃልና በሕይወት የተቀናጀ ምስክርነት እጅግ አስፈላጊ መሆኑ አስምረውበታል፣ ማንኛውም ክርስቲያን ለክርስትና እምነቱ ታማኝ ከሆነ በቅዱስ አባታችን የቀረበው ጥሪ የሚኖር ይሆናል። ክርስትና በቃልና በሕይወት መመስከር አማራጭ ሳይሆን ክርስትናው ለገዛ እራሱ ነው። ካቶሊክ አንግሊካዊ ወይንም ኦርቶዶክስ መሆን ውደራ ሳይሆን ያለን ልዩነት ጭምር የእግዚአብሔር ምህረት እንደሚያስፈልገን አውቀን፣ አንዱ ለሌላው አስፈላጊ መሆኑ ለቡ የሚል ነው።

ስለ ክርስቲያኖች አንድነት በየዓመቱ እ.ኤ.አ. ከጥር 18 ቀን እስከ ጥር 25 ቀን የጋራ የጸሎት ሳምንት ይከናወናል፣ የመገናኛ ብዙሃን በዚህ ሳምንት ብቻ ካልሆነ በስተቀረ ከዚህ ውጭ በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው ውይይት ለቀራረብ የሚፈጸመው የጋራ ዓውደ ጉባኤና ዓውደ ጥናት በተመለከቱ ወይንም ስለ አንድነት ታልሞ በጋራ የሚያካሄዱት ቲዮሎጊያዊ ስነ ቤተ ክርስቲያናዊ ውይይት አይናገሩም፣ ቅዱስ አባታችን ር.ል.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተጠሩበት ዕለት ጀምረው ስለ ተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን አንድነት ታልሞ የሚደረገው የጋራው ውይይትና ጸሎት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቅድሚያ የሰጡት ርእስና ተግባር ነው። ሁሉም ክርስቲያን እርሱ በእርሱ በመደጋገፍ በመተባበር በቤተ ክርስቲያኖች በቁምስናዎች በውሉደ ክህነት በማኅበረ ክርስትያን ደረጃ የጋራው ግኑኝነት መኖር ይገባል፣ የጋራው ግኑኝነትና የክርስቲያኖች አንድነት ያለው አስፈላጊነት በየዓመት እ.ኤ.አ. በዚህ ጥሪ ወር ብቻ የሚታወስ ሳይሆን ዓመቱን ሙሉ የሚኖር ተግባር መሆን አለበት ምክንያቱ  የክርስቲያን አንድነት ወንጌላዊ ጥሪ እንጂ ሕግና ስርዓት መኖር ማለት አይደለም ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.