2016-01-19 10:51:00

ቅ.አባታችን ፍራንቸስኮስ፦ አረጋዊያን ትኩረት ሊቼራቸው ይገባል


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ ባለፈው አርብ እለት ከሰዓት ቡኋል ድንገተኛና ያልታቀደ ጉብኝት በማድረግ ከሰላሳ ሦስት በላይ ሀረጋዊያን የሚጦሩበትን መኖሪያ ቤት መጎብኘታቸው ተገለፀ። ቅዱስ አባታችን ይህንን ያልታቀደ ጉብኝት ያደርጉበት ምክንያትን ምክንያት ሲገልፁ እርሳቸው እንደ አንድ ክርስቲያን በዚህ በያዝነው የምህረት አመት የእግዚአብሔርን ምህረት እና ሰላም የተቸገሩትንንና የታመሙትን በመጎብኘት የግል መንፈሳዊ ገደታቸዉን ለምፈፀም በመፈልጋቸውና መሆኑን ገልፀው አሁን ባለንበት ዘመን ትኩረት እየተነፈጋቸው የመጡትን አረጋዊያን ትኩረት ሊቼራቸው እንደሚገባ ለማሳሰብ ጭምር መሆኑን ጂአዳ አኩሊኖ ዘግባለች።

ቀደም ብሎም ቅዱስ አባትችን በዚህ በያዝነው የምህረት አመት በወር አንድ ጊዜ አረጋዊያንንና የታመሙትን ለምጎብኘት እቅድ ያወጡ መሆናቸው የሚታወስ ስሆን በተልይም ደግሞ በተለያዩ ከባድ በሆኑ የህመም ዓይነቶች የሚሰቃዩትን አረጋዊያን እና በመኪና አደጋ ምክንያት ዘላቅ የሆነ የአካል ጉዳት የገጠማቸዉን ወጣቶች በቀጣይነት እንደ ሚጎበኙም ተወስቷል።

 

አርብ እለት በአረጋዊያን ማረፊያ ያደርጉት ጉብኝት እንደወትሮ ግርግር የበዛባት ሳይሆን ቀለል ያለ እንደነበር ተወስቶ ለያንዳንዱም በሽተኛ ጊዜ ሰጥተው ፎቶግራፍ በመነሳት አጋርነታቸውን እና ሁል ጊዜም በፀሎት አብረዋቸው ከእነርሱ ጋር እንደሚሆኑ በመግለጽ በትህትናቸው ለአረጋዊያን ያላቸውን አጋርነት እና ፍቅር ያስዩበት ወቅት እንደነበረም ተጠቅሷል።

በጉብኝቱ ወቅትም ቅዱስ አባታችን ብዙ ከመናገር ይልቅ ብዙ ያዳመጡ መሆናቸው የተገለፀ ስሆን በተደጋጋሚም ለእርሳቸው አርጋዊያን እድፀልዩ የጠየቁ ስሆን እርሳቸውም በፀሎት ከእነርሱ ጋር ሁሌም እንደሚሆኑ በመግለጸ በፈገግታ በታጀበው ሰላምታቸው በበሽታ የሚሰቃዩ አረጋዊያን ለትንሽ ጊዜም ቢሆን ስቃያቸውን እንዲረሱ አስቸልውም እንደነበር ተወስቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የነበሩ አንድ አንድ ሰዎች በሰጡት አስተያየት ቅዱስ አባታችን ያደርጉት ያልተጠበቀ ጉብኝት ለቤተ ክርስትያን አገልጋዮች እና ለምዕመናን በዚህ በያዝነው የምህረት አመት በመንፈስ እና በአካል የተቀናጀ በንፈሳዊ ዝግጅት ማድረግ እንድሚጠበቅባቸው ያስተማረ እና አስፈላግነቱን በጉልህ የሚያሳይ መሆኑን አውስተው እኛም እርሳቸው ያሳዮንን መልካም ምሳሌና አርአያ ተከትለን የመንፈስ ዝግጅት ማድረግ ቢቻ ሳይሆን በትግባርም የታመሙትንና የተቸገሩትን በመጎብኘት ጭምር ይህንን ቅዱስ የምሀረት አመት እንድንዘክር ያስተማረ ጉብኝት ነበር በማለት አስተያየታቸውን ገልፀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.