2016-01-18 16:08:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ግኑኝነቶችና የአዲስ ሐዋርያዊ ልኡካን ሢመት


እ.ኤ.አ. ጥር 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀትር በፊት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ማርክ ኦወለትን በመቀጠልም በሊቀ ጳጳሳት የሞንተ ነግሮና ሊቶራለ ሜጥሮፖሊታ ብፁዕ አቡነ አምፊሎሂየ የተመሩትን የኖቪ ሳድሪና ባካ ጳጳሳስ ብፁዕ አቡነ ኢረንየ በቅድስት መንበር የሰርቢያ ልኡከ መንግሥት ፕሮፈሰር ዳርኮ ታናስኮቪችን ተቀብለው እንዳበቁም የቅድስት መንበር የኤኮኖሚ ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ ፐል በሩዋንዳ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሉቻኖ ሩሶና እንዲሁም በሱዳንና ኤርትራ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ቡበርቱስ ማተውስ ማሪያ ቫን መገንን ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን በሞናኮ ቦስኒያና ኤርዞጎቪና የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሆነው እንዲያገለግሉ ሊቀ ጳጳሳትን ብፁዕ አቡነ ልዊጂ ፐዙቶ መሾማቸው የገለጠው  የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ በቻይና የማካኡ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ኾሰ ላኢ ሁንግ ሰንግ በእድሜ መግፋት ምክንያት ያቀረቡት የሊኅቅነት ጥያቄ ቅዱስ አባታችን በማጽደቅ በምትካቸው የሆንግ ኮንግ ሰበካ ረዳት ጳጳሳ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙትን የማካኡ ሰበካ ጳጳስ እንዲሁን ብፁዕ አቡነ ስተፈን ሊ ቡን ሳንግ መሾማቸው ሲያመለክት የማካኡ ሰበካ ሕዝብ ብዛት 636,200 ሲሆን ከዚህ ውስጥም 30 ሺሕ 124 የካቶሊክ እምነት ተከታይ ሲሆን በጠቅላላ 9 ቁምስናዎች ያሉትና 16 የሰበካ ካህናት 49 የመንፈሳዊ ማህበር አባላትና 194 የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ደናግል እንደሚገኙም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.