2016-01-16 10:23:00

ለአፍሪቃ ቤተ ክርስቲያን ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ድጋፍ


የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በአፍሪቃ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተለይ ደግሞ በምእመናን ቁጥር ብዛት በማደግ ላይ ለሚገኙት ሰበካዎች፣ የወጥኑት የግብረ ሐዋርያዊ እቅድ ማስፈጸሚያ ለወንጌላዊ ተልእኮ ለትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪዎች ሕንጸት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ድጋፍ የተስተካከለና የተገባ ትምህርት ቤት እንዲኖራቸው በሚል አላማ የአንድ ሚሊዮን ዶላር እርዳታ መስጠቱ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. ከ 1980 ዓ.ም. ወዲህ ብቻ  የአፍሪቃ ካቶሊክ ምእመን ብዛት በሦስት እጥፍ ከፍ ያለ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከ 200 ሚሊዮን በላይ ምእመናን እንዳሉ ነው የሚነገረው። የዋሽንግተን ልኂቅ ሊቀፍ ጳጳሳት የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ይኸንን በምእመናን ብዛት ከፍ ለሚሉት ድኾች አገሮች መርጃ የሚከታተለው ማኅበር ተጠሪ ብፁዕ ካርዲናል ተዎዶረ መክካሪክ የሰጡት መግለጫ የጠቀሰ ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፦ የእርዳታው ተጠቃሚ ሰበካዎች ከሆኑት ውስጥ በኢትዮጵያ በኡጋንዳ የሚገኙትን ጠቅሰው ሌሎች ሰበካዎች ጭምር የሚመለከት እርዳታ ነው ብለው በአፍሪቃ የሚታየው የካቶሊክ ምእመን ብዛት መጨመር ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጸጋ ነው እንዳሉም ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.