2016-01-14 09:38:00

የእግዚአብሔር መህሪ ነው፦


በቅዱስ ር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቸስኮስ ቃለ ምልልስ ላይ ተመስርቶ “የእግዚአብሔር መህሪ ነው”  በተሰኘው አርስት ለንባብ የበቃው መፀሓፍ የቫቲካን አስተዳድሪ ካርዲናል ጲየትሮ ጳርሎኒ እና የቫቲካን ሕዝብ ግንኙነት አላፊ አባ ፈረዲሪኮ ሎምባርዲ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በትላንትናው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በጥር 12.2016 ተመርቆ ለንባብ በቅቷል ሲል አልክሳንድሮ ጂዞቲ ዘግቧል።

መፃሓፉ በአብዛኛው ትኩረቱን ያደረገው በእግዚአብሔር የምህረት ሚስጢር ላይና ይህ ታልቅ የምህረት ሚስጢር በር.ሊ. ጳጳስ ፍራንቼስኮስ የቤተ ክርስያን የአመራር ሂደት ውስት የሚያበረክተውን አስተውፆ በማዉሳት ይጀምርና የእግዚአብሔር እልውና በሙላት ሊገለፅ የሚችለው በምህረት አድራጊነቱ መሆኑን በዝርዝር በማስረዳት በተለየም ደግሞ ከያዝነው የሚሀረት አመት አስተምሮ እና አሳብ ጋር እንዲዛመድ ተደርጎ የእግዚአብሔርን ምህረት በመንፈሳዊነት እንድንለማመድ በ86 ቋንቋዎች የተተረጎመ መጻሃፍ መሆኑ ተገልጿል።

በምረቃው ስነ ስረዓት ላይ ተግኝተው የነበሩ ካርዲናል ጴትሮ ጳርሎኒ በበኩላቸው እንደገለጹት እግዚአብሔር እንዲገለፅለት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በእግዚአብሔር ምህረት እንዲታቀፍ የሚያበረታታ መፅሓፍ መሆኖኑን አመልክተው የመፃሓፉ ጠቅላላ ይዘት ደግሞ የሚያሳየው ያለ እግዚአብሔር ታልቅ ምህረት ያለንባት ዓለም ልትኖር እንደማትችል ያስገነዘበና ሰዎች እግዚአብሔር በነፃ ወደ ሚለግሳቸዉ ታላቅ ምህረትና ፍቅር የሚጋብዝ በመሆኑ ጠቃሚነቱ በተለይም ደግሞ በዚህ በያዝነው የምህረት አመት በጣም ከፍተኛ ነው በለዋል።

በመቀጠልም ተምርቆ ለንባብ የበቃው ይህ አዲሱ መፃሓፍ በጊዚያችን ለሚታዩት ውስብስብ የዓለማች ጥያቄዎችና ችግሮች ቀጥተኛ የሆነ ማልስ ባይሰጥም ሰዎች ተስፋ ባለመቁረጥ ዘላለማዊ ፍቅር ወዳለው እግዚአብሔር ያለ ፍረሃ እንዲቀርቡ የምያስረዳና በተለይም የእግዚአብሔር ሓሳብ ከሰዎች ሓሳብ በእጅጉ የተለየ መሆኑን በማውሳት ላይ ትኩረቱን አድርጓል ሰዎች ያለ አንዳች ፍርሃት ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ ያበረታታል ብሉዋል።

ምህረት ማለት የአንድ ሰው የግል መንፈሳዊ ለውጥ ቢቻ አለምሆኑን ይሚያስረዳው አዲሱ መፃፈ ነገር ግን በተጨማሪም ምህረት ማለት በሰዎች እና በሀግሮች መካከል የሚገኝውን የጥል ግድግዳ በማስወገድ ባለንበት በግዴለሽነት የተሞላ፣ የሓትያትን እንደ ነውር መቆጠር እየተወ በመጣ ዓለማችን ሊያበርክት የሚችለው አስተዋጾ እጅግ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

የር.ሊ.ጳጳስ ዋንኛው መለዕክትም የቅርታን ማድረግና ይቅር መባል የሚያመጥውን መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ለውጥን ማዕከል ያደርገ በመሆኑ በያዝነው የምህረት ዓመት በተከፈቱት የምህረት በሮች በመጋባት እራሳችንን በእግዚአብሔር ፍቅር ለመታቀፍ ዝግጁ በማድርግ ለግል መንፈሳዊ ለውጥ ቢቻ ሳይሆን ለያንዳንዱ ሰው፣ ሕዝብ፣ ማህበረሳብ እና ሀገር መንፈሳዊ በርከት በማምጣት አዲስ በሆነ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ ግንኙነትን በመፍጠር ከራስችን በመነሳት የዓለም ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፍቅር በመታቀፍ በስላም እና በጤና እየኖረ ፈጣሪዉን እንዲያምሰግን የሚያነሳሳ ጭምር ነው ተብሏል።

በስተመጨሻም በመፃፉ ምርቃት ላይ የተገኘው የጣሊያን ታዋቅ የፊልም ደራሲ እና ተዋንያን ሮበሮቶ ቤኒኚ እንደገለፀው ይህ አዲሱ መፃፍ ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኩስ በፈጠሯቸው ቃልት ልባችንን በመንካት ሁላችንም በጣም የሚያቀራርበን፣ የሚያቅፈን፣ ይቅር የሚያባብለን ልዩ መፃፍ ነው ሲል መፃፉን አወድስዋል።

በመቀጠልም ምሀረት ማለት ዝም ብሎ ተቀማጭ የሆነ ነገር ሳይሆን ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባና ነባራዊ ሆኖ ሁልጊዜ ያለማቋረጥ ከእኛ ጋር የሚጓዝ ልብን ቢቻ ሳይሆን ሁለንታናችንን ያለማቋረጥ የሚያንቀሳቅስ ለአንድ ሰኮንድ እንኳን ሳንዘገይ ችግርን እና ድህነትን እድንጋፈጥና መፍትሄ እንድናበጅ የሚያነሳሳ መፀሓፍ ነው ብልዋል።

በማስከተልም ሮበሮቶ ቤኒኚ እንዳሰመርው የዚህ አዲሱ መፃፍ በይዘቱ መንፈሳዊና መልኮታዊ ቢመስልም፣ በማህበራዊና ፖለቲካዊ መስክ የሚያበረክተው አስተዋጾ እጅግ በጣም ከፍ ያለ በመሆኑ ጠቃሚነቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያማከል በምሆኑ ጠቃሚነቱ አያጠያይቅም ብሏል።

ይህ መፃፍ በተለይም የተናቁትን እና የተረሱትን ወገኖቻችንን እንድናስብና እንድንዘክር መንገድ ይከፍትልናል ካለ ቡኋላ ር.ሊ.ጳጳስ ፍራንችስኮስ ጳጳስ ሆነው ሲመረጡ የጀመሪያ ጉብኝታቸውን የጀመሩት በላፓዱሳ የሚገኙትን ባአስቸጋሪ ሁኔታ ወደ አውሮፓ ለምግባት ሲሉ ሕይወታቸውን ያጡትን ስደተኞች ለመዘከርና አጋርነታቸውን በፀሎት በመግለፅ በትግባር እናዳሳዩንና በመቀጠልም ታላቁን የኢዩበሊዩ የምህረት በር በጦርነት እና በስደት በታመሰችው በመካከለኛ የአፍሪካ ሪፖብልክ ባጒዊ በመክፈት አጋርነታቸውን እጅግ ለተጎሳቆሉ ወገኖች በትግባር የምህረት አድራጊነትን አስፈላጊነት በማሳየታቸው ልብን በሚነካ ሁኔታ የእርሳቸውን አርዓያ እንድንከተል አስተምረውናል ይህም አዲሱ መፃፋቸው ምህረት አድራጊዎች እንድንሆን ያበረታታናል በማለት ንግግሩን አጠናቋል።

በመጨረሻም ፍራንቸስኮ የተባለ አንድ ተሳታፊ በማጠቃለይ ንግግሩ እንደለፀው በዓልመ ዉስጥ ለሚሰሩት ጥፋቶች ሁሉ ይቅርታ ብናደርግ የፍትህ አካላት አስፈላጊነት ታድያ ምኑ ላይ ነው? ብሎ በጥያቄ ጀምሮ ከቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮስ መፃፍ በመጥቀስ ይቅርታ ከፍትህ በጣም የተሻለና ፍተህ ደግሞ በትንሹ የይቅርት መገለጫ በመሆኑ አስገንዝቦ ይቅርታ በፍፁም ምህረትን ሊያጠፋና ሊቃወም አይችልም ብሏል። በማከልም በፍትህ ቢቻ የሚያምን ዓለም በጣም የቀዘቀዘ ዓለም ይሆናል ብሎ፣ የሰው ልጅን የሚያስፈልገው ፍትህ ቢቻ ሳይሆን ይቅርታ ዋንኛው እና መሰረታዊ የማህበረሰብ እሴት ሊሆን ይገባል ሲል ንግግሩን አጠናቁቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.