2016-01-13 16:44:00

ኢንዶነዢያ፦ የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራ ለሰላማዊ ማኅብራዊ ኑሮ


አክራሪነትና አሸባሪነት በጋራ በመዋጋት መድብላዊነት ማነቃቃት ማኅበራዊ ሃይማኖታዊ ባህላዊ ኅብረአዊነት መንከባከብ ለኢንዶነዢያ ሰላማዊ ኅብረተሰብና አገር ግንባታ መሠረት ይሁን የሚል ቅዉም ሃሳብ የሚያስተጋባ በአገሪቱ የሚገኙት ከሁሉም ሃይማኖቶች የተወጣጡ አካላትና ምእመናን ያሳስተፈ መከባበር መቀባበል እንዲሰፍን ያለመ ሰላማዊ የእግር ጉዞ በጃካርታ እ.ኤ.አ. ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ሊካሄድ በእቅድ መያዙ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት ገለጠ።

ይኽ በኢንዶነዢያ የሚገኙት 13 የተለያዩ የምስልምና ሃይማኖት ድርጅቶች ከአገሪቱ የብፁዓን ጳጳስት ምክር ቤት፣ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን ለመላ ኢንዶነዢያ የኮንፉቾ ሃይማኖት ምክር ቤት  ጋር በመተባበር ያዘጋጁት መሆኑ የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፦

የብፁዓን ጳጳሳት ተሳትፎ

ብዙኅነት የአገር ኃይል መሆኑ ሊመሰክር በተዘጋጀው በዚህ የሁሉም በኢንዶነዢያ የሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖቶች በጋራ ባዘጋጁት ሰላማዊ የእግር ጉዞ በኢንዶነዢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት ምእመናን ውሉደ ክህነት ገዳማውያን እንደሚሳተፉ የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የዓለማውያን ጉዳይ ለሚንከባከበው ድርገት ሊቀ መንበር አባ ጉይዶ ሱፐራቶ የሰጡት መግለጫ ጠቅሶ ያመልከታል።

በኢንዶነዢያ ማንኛውም ዓይነት ገዛ እራሱ  እስላማዊ አገር ብሎ የሰየመው አሸባሪው ኃይል የሚያረማምደው የሽበራ ተግባርና ሽብርተኛው አመለካከት እንዳይጋባ በጋራ አክራሪነትና አሸባሪነት በመቃወም የሰላም ሕንጸት አስፈላጊ መሆኑ የጋራው ሰላማዊ ሰልፍ ካዘጋጁት ውስጥ አንዱ የናህድላቱል ኡለማ ሊቀ መንበር ማርይሱዲ ስዩሁድ ገልጠው ሁሉ አገሮች በወንድማማችነት መንፈስ ማስተባበር ማቀራረብ ዓላማችን ነው እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የምስልምናው ሃይማኖት የሰላም ሃይማኖት አይደለም የሚሉትን በሰላማዊ መንገድ ለማረምና ሃይማኖት የሰላምመሳሪያ መሆኑ እንዲስተዋል ለመደገፍና በሺዓውያንና ሱኒቶች መካከል ተቀስቅሶ ያለው ግጭት በማስወገድ ሁሉም ሃይማኖት በሰላም በጋራ ለመኖር የተጠሩ መሆናቸው በመመስከር  የዚያ እስላማዊ አገር ፖለቲካዊ ህልም እናክሽፍ ከኢንዶነዢያ ወደ ሶሪያ ሄደው ያንን አሸባሪ እስላማዊ አገር ሥር አገልግለው ወደ ኢንዶነዢያ የተመለሱ እንዳሉ ሁሉም ያውቀዋል ሆኖም መንግሥት አነዚህ ሰዎች ለይቶ እንዲከታተላቸው ያስፈልጋል እንዳሉ  ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልጎት አመለከተ።

ያንን እስላማዊ አገር የሽበራው ኃይል የሚያረማምደውን የጸረ ሰላም ዓላማውን ለመደገፍ ከኢንዶነዢያ 800 ሰዎች ወደ ሶሪያ መሄዳቸውና ከእነዚህም ውስጥ 150 ወደ ኢንዶነዢያ የተመለሱ መሆናቸው ኤሺያን ኔውስ የተለያዩ ምንጮች ጠቅሶ ሲያምለክት፣ አክሎ የአገሪቱ የዜና ምንጮች አስደግፎ 800 የኢንዶነዢያ ዜጎች ወደ ሶሪያ መሄዳቸውና ከእነርሱም ውስጥ 240 ማንነታቸው ሲታወቅ ሌሎች 52 ደግሞ በሶሪያ በመካሄድ ላይ ባለው ውግያ መገደላቸው ያመለክታል።         








All the contents on this site are copyrighted ©.