2016-01-12 10:15:00

የይቅርታ አድራጊነትን አስፈላጊነት በመማር...ሰላምን እና ይቅርታን እንዲያመጡ ማስተማር


እንደሚታወሰው እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በታህሳስ 8.2015 ብቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳጳስ ፍርንቼስኮስ ተባርኮ የተከፈተው ኢዩቤሊዩ ቅዱሱ የምህረት አመት በር በይፋ ከተከፈት ቡኋል 1 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሚልዮን በላይ በሚሆን ነጋድያን መጎብኘቱ ተገለፁ የሚያሳየው ምዕመናን በታልቅ ደስታና ስሜት እምነታቸውን እያጠነከሩ መምጣታቸውን ነውና በዚህም በያዝነው ወርም በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲልካ የሚገኘውን ቅዱሱን የምህረት በር ለምጎብኘት ቢዙ ምዕመማን ቅድመ ዝግጅት ያደርጉ ሲሆን በተለይም ደግሞ በየካቲት ወር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲልካ የሚመጣውን የቅዱስ ፕዮን አጽም ምክንያት በማድረግ ቁጥራቸው ከፍ ያለ ምዕመናን ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል ብለዋል አቡነ ሪኖ ፊዝኬላን ስትል ማሪና ቶማሮ እንደ ዘገበችው።

በመላው ዓልም በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በተከፈተው የምህረት በር ያለፉት የምዕመናን ቁጥር ከመቶ ምሊዮኖች ይበልጣል ተብሎ ቢገመትም ዋናውና አስፈላጊው ነገር ምዕመናን በነዚህ በተከፈቱት የምህረት በሮች ማለፋቸው ቢቻ ሳይሆን፣ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ጉዳይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ ጳጳስ ፍራንቼስኮስ በታህሳስ ወር የምህረትን በር መርቀው የከፈቱበት ዋነኛው ምክንያት ግን በዚህ የቅዱስ በር በማለፍ የእግዚአብሔርን ምህረት ማግኘት እና እኛም ያገኘነውን ምህረት ለእህት እና ወንድሞቻችን ምህረትን በማድርግና የበደሉንን ይቅር በማለት በሕይወታችን የእግዚአብሔርን ምህረት መለማመድ ዋናውና መሰረታዊ ዓላማ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።

በተለይም ደግሞ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ከየካቲት 3-11 የቅዱስ ፒዮ አጽም ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ባስሊካ በሚመጣበት ወቅት የምዕመናን ቁጥር በእጅጉ ከፍ እንደሚል ይጠበቃል ካሉ ቡኋላ ለኛ ዋንኝዋ ጠቃሚ ነገር የምዕናን ብዛት ሳይሆን በኛ በኩል ትኩረት የሚቸረው ነገር ከልብ የመነጨ መንፈሳዊ ተሳትፎ ነው ብለዋል።

 በመሆኑም ዋንኛውም የዚህ የምህረት ኢዩበሊዩ ዓመት ዓላማ ሊሆን የሚገባው የእግዚአብሔርን እምህረት በየጊዜው በክርስትያኖች ሕይወት ውስጥ በማኖር እንርሱም የይቅርታ አድራጊነትን አስፈላጊነት በመማር በዓለማችን ውስጥ የሰላም መሳሪያ ሆነው ሰላምን እና ይቅርታን እንዲያመጡ ማስተማርና የተጋባር ለውጥ ማስገኘት ነው ዋንኛው ግባችን ብለወ ንግግራቸውን አጠቃለዋል።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.