2016-01-12 09:15:00

እግዚአብሔር እንዲሰጠው ለእግዚአብሔር መልሶ ያበደርው ማን ነው?


ክቡራት እና ክቡራን የተውደዳችው የእግዚአብሔር ወዳጆች እና በጎ ፍቅድ ያላችሁ አድማጮች በሙሉ፤

ከሳምንት እስከ ሳምንት ጠብቆን ከቀን ወደ ቀን አሻግሮን እንደ መልካም ሥራችን ቢቻ ሳይሆን በታላቅ ምህረቱ ጎብኝቶን እዚህ ያደረሰን እግዚአብሔር አምላካችን የተመሰገነ ይሁን።

“ሓሳቤ እንደ ሓሳባችው መንገዴ እንደመንገዳችሁ አይደለም፣ ልክ ሰማይ ከምደር ከፍ እንደሚል ሓሳቤም ከሓሳባችሁ መንገዴም ከመንገዳችሁ እንዲሁ ከፍ ይላል” ብሏል እግዚአብሔር በት. ኢሳይያስ 55፡ 8። የእግዚአብሔር ሓሳብ ሁል ጊዜም ቅዱስ ነው፣ በደግነትና በፍቅር የተሞላው፣ የማያዳላ፣ ይቅር ባይ እንደበደላችን የማይከፍለን አምላክ ነው።

እኛ ሰዎች ግን በአንፃሩ በደል ቆጣሪዎች፣ ለይቅርታ የዘገየን፣ ጥልና ክርክር የበዛብን፣ በአንዱ እግዚአብሔር ሥም ተከራክረን ጦርነትን የምናውጅ፣ እርስ በእርሳችን ለመዋደድ የምንቸገር፣ በአብዛኛው ደግሞ ከእርሱ ፍቅድ የራቅን በመሆናችን ሓሳባችን ከእግዚአብሔር ሓሳብ ልክ የሰማይና የምድርን ያህል ለመራራቁ ማስረጃ ነው።

በዛሬ ዕለት ማለትም በጥር 1.2008 እንደ በኢትዮጵያ የስራዐተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር  የመጀመሪያው  የእግዚአብሔር ቃል የተወሰድው ከሓዋሪያው ጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮሜ ሰዎች በምዕራፍ 11.25-36 በፃፈው የእግዚአቤር ቃል ይጀምራል። በ11፣33 ላይ እንድህም ይላል…“እግዚአብሔር የጥበቡ እና የእውቀቱ ባለጠግነት እንዴት ጥልቅ ነው! ፍረዱ አይመረመርም ለመንገዱም ፈልግ የለውም! የጌታን ልብ ያወቀ ማን ነው? አማካሪውስ የነበረ ማን ነው? እግዚአብሔር እንዲሰጠው ለእግዚአብሔር መልሶ ያበደርው ማን ነው? ሁሉም ከእርሱ፣ በእርሱ፣ ለእርሱ ነውና ለዘላልም ለእርሱ ክብር ይሁን አሜን።” አሁን ያነበብነው የእግዚአብሔር ቃል የምያሳየን እግዚአብሔር መሀሪና ምንም ተወዳዳሪ የሌለው አምላክ መሆኑን ሲሆን ሁሉንም የሰው ልጆች የለምንም ልዩነት ለማዳን (በዘር፣ በቀለም፣ በሓይማኖት ወዘተ…ሳይከፋፍል ለማዳን) ያለውን ታላቅ እቅድ፣ ጥልቅ በሆነው ጥበቡና ዕውቀቱ እንዲፈጸም ላደረገው ለእግዚአብሔር የቀረበው ምስጋናን ያካተተ ነው።

እግዚአብሔር እውቀቱ የጠለቀ የሰውን ልብ እንኳ መርምሮ የሚያውቅ አማልክ በምሆኑ ከእርሱ የሚሰወር ነገር በፍፁም ሊኖር አይችልም።

---በአብዛኛው ከሰዎች ተደብቀን ብዙ ስህተቶችን ልንፈፅም እንችል ይሆናል ነገር ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ መደበቅ አንችልም።

----የጌታን ለብ ያወቀ ማን ነው? የጌታን ልብ በተወሰን መልኩ ልናውቅ እንችል ይሆናል….አፍቃሪነቱን፣ መሓሪነቱን፣ ደግነቱን፣ ሓሳቢነቱን፣ አይዞ ባይነቱን፣ አዛኝነቱን...ወዘተ ተርፈ…ነገር ግን እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ሁሉንም እቅድ ልናውቅ ግን አንችልም እግዚአብሔር ታልቅ አምላክ በመሆኑ።

---እግዚአብሔር መልሶ እንዲሰጠው ለእግዚአብሔር መልሶ ያበደርው ማን ነው? ግፋ ቢል ከእግዚአብሔር ለተቀበልነው ስጦታ እግዚአብሔርን እናመሰግነው ይሆናል….ቅዱስ ነህ ልንለው እንችላለን ነገር ግን በእግዚአብሔር ቅድስና ላይ ጠብታ ቅድስና መጨመር አንችልም…ክብሩ ይስፋ ልንል እንችላለን ግን የእግዚአብሔርን ክብር እኛ ልናሰፋ አንችልም ምክንያቱም እግዚአብሔር ሙሉ ነዉና ወዳጆቼ…ስለዚህ እግዚአብሔር በደግነቱ ከነ ኮተታችን የምህረት አባት በመሆኑ የወደናል ይንከባከበናል እንጂ እኛ መልካም እና ሁል ጊዜ የእርሱን ፍቅድ ፈፃሚዎች ሰለሆንን አይደለም።

ከታልቅ ምህረቱ የተነሳም እኛን እንዲያድነን፣ እንዲያስታርቀን፣ ሰላምን እና ደስታን እንዲሰጠን አንድኛ ልጁን ሥጋ ለብሶ ወደዚህ ምድር እንዲመጣ እና በበረት እንዲወለድ የፈቀደው ደግና መሓሪ አምላክ ስለሆነና እኛን ለማዳን ከፍተኛ ፍላጎት እናዳለው ስለሚያሳይ ነው። እኛም እርሱ ባስተማረን መሰርት እርስ በእርሳችን ይቅር ልንባባል ያስፈልጋል።

ቅዱስ ዩሓንስ በአንደኛው መልዕክቱ በምዕራፍ 4፣1 ጀምሮ “ወዳጆቼ ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ዘንድ መሆናቸዉን መርምራችሁ እወቁ” ይለናል። ሓዋሪያው ዩሓንስ ይህንን ያሳሰበበት ምክንያት ምንድነዉ? ስንል…እርሱ በነበረበት ዘመንና አሁን ባለንበት በኛም ዘመን ስለ ኢየሱስ የተለያዩ የተዛቡ አስተምሮዎች በመኖራቸው ለምሳሌም ኢየሱስ በውሃ በዮርዳኖስ ወንዝ በሚጠመቅበት ጊዜ መለኮትነቱ በእርግብ አምሳል እርሱ ውስጥ ገባ ከዚያም ደግሞ በመስቀል ልይ በነበረበት ጊዜ ተለይቶት ሄደ የሚል የኖስትሳዊያን የሓሰት አስተምሮ ስለነበረ በዚህ አስተምሮ ክርስቲያኖች እንዳይታለሉ በማሰብ ነበረ ይህንን የምስገንዘብያ ደብዳቤ የፃፈው።

ስለዚህ እኛ የምንቀበለው እና የምናምነው ኢየሲስ መሆን ያለብት ቃል የነበረ ይህም ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ እንደነበረ፣ ቃሉም እግዚአብሔር እንደነበረ እና ይህም ቃል በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከእናትችን ከቅድስት ማሪያም ሥጋን ነስቶ ሰው የሆነ እኛን ለማዳን በምስቀል ልይ የተስቀለና ዓልምን በሙሉ በደሙ የዋጄ፣ የሓጥያታችንን ካሳ ሁሉ በደሙ የከፈልውን ኢየሱስን ነው የምናምነውና የምንቀበለው።

ስለዚ እኛን ከሌሎቹ ሊለየን የሚገባው ይህንን አዳኝ የሆነውን ኢየሱስን በማወቅ ቢቻ ሊሆን አይገባም። ምክንያቱ ኢየሱስን ማወቅ ብቻ ይበቃል የምንል ከሆነ እርኩሳን መንፍስትም ያውቁታል ለምሳሌም በማርቆስ ወንጌል 1፣24 ኢየሱስ ምኩራብ ለማስተማር በገባበት ጊዜ አንድ እርኩስ መንፈስ ያደረብት ሰው “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ ከኛ ምን ትሻልህ? ልታጠፋን መጣህን? እኔ ማን እንደሆንክ አውቃለሁ፣ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ” ብሎ ስለ ኢየሱስ ማንነት መመስከሩ የሚያሳየው ኢይሱስን ማወቅ ቢቻ ሊያድነን እንደ ማይችል ነገር ግን እርሱ የሚለንን ትዕእዛዝ በመፈፀም በእለት ተእለት ኑሩዋችን እርሱን ስንመስክር እና ተጋባራዊ ስናደርግ ቢቻ ምሆኑን ስንረዳ ትክክለኛውን መንፈስ እና አስተምሮ ይዘናል ማለት እንችላለን።

በዛሬው የቅዱስ ወንጌል ቃል የተወስደው ከማቴዎስ ወንጌል ከምህራፍ 2፣1-12 የሚገኝው ሲሆን የሚያወሳውም ከምሥራቅ ኮከብ እየመራቸው ሕፃኑን ኢየሱስ ለማግኝት የመጡ ጠቢባንን (ሰባሰገል) ታሪክ ያወሳል።

እነዚህ ጠቢባን በጊዜው የኮከብ ቆጠራ ትምህርትን በደንብ ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ በማህበረስቡ ውስጥ ተሰሚነት የነበራቸው ሰዎች ነበሩ። “የተወለደው የአይሁድ ንጉስ ወዴት ነው፣ በምስርቅ ኮከብን አይተን ልንሰግደለት መተናል” አሉ እንዚህ ጠቢባን ለሄሮድስ። በኮከብ ልንመስላት የምንችለው ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ኮከቡ ጠቢባንን እንደመራና ወደ ሕፃኑ ኢየሱስ እናዳደረሳቸው ሁሉ ቤተ ክርስትያንም ምዕመናንን ወደ ኢየሱስ የመምራት ዓላማና አላፊነት ተሰጥቷታል። ዛሬም ኢየሱስ ወደ እርሱ ለሚጓዙ ሁሉ ለመገለጥ ዝግጁ ነው።ኢየሱስ በተወለደብት ሌሊት በቤተሊሄም ለነበሩ እረኞች መላዕክት እንደተገለፁና እረኞቹ ወደ በረት እንድሄድ በነገሯቸው መሰረት የመላዕክቶችን ቃል ሰምተው እንድሄዱና ሕፃኑን ኢየሱስን እንዳገኙት ሁሉ እኛም ቤተ ክርስትያናችን የምትነግረንን መልካም ዜና አዳምጠን ወደ ኢየሱስ ልንጓዝና በሕይወታችን ውስጥ ልናስገባው ይገባል።

እነዚህ ጠቢባን ምድራቸውን ጥለው በኮከቡ መሪነት ከሀገራቸው መውጣታቸው ሀገር ለምጎብኘት ወይም ለመዝናናት ሳይሆን የደከሙት ሕፃኑን ኢየሱስ ፍለጋ በመሆኑ እኛም የራሳችንን ፍላጎት ለማሳካት ቢቻ ሳይሆን፣ ኢየሱስን በሕይወታችን ለማስገባት እና የግል አዳኛችን ለማድረግ ጭምር ልንተጋና ኢየሱስን እንዳናገኝ የሚያግዱንን ነገሮች ሁሉ አውልቀን ጥለን እርሱን ቢቻ የግላችን አዳኝ ለማድርግ መትጋት ይጠበቅብናል።

ጠቢባኑ ኢየሱስን ለምፈለግ በምያደሩት ጥረት በመሃሉ ኮከቡን ጠፍቶባቸው ነበረ….ነገር ግን ለመዳን ታልቅ ጉጉት ስለነበራቸው ምንም ተስፋ ባለምቁረጥ ጉዞዋቸውን እንደቀጠሉ ሁሉ ...እኛም የነርሱን ፈልግ ተከትለን ኢየሱስን ለማግኝት በምናደርገው ጥረት የምገጥሙንን መሰናክሎች በትዕግስትና በታልቅ ጠበብ ማለፍ ይጠበቅብናል።

ጠቢባን ኮከቡን በድጋሜ ባዩት ጊዜ እጅግ በጣም እንደ ተደሰቱ ሁሉ እኛም ተስፋ ባለመቁረጥ ኢየሱስን ፈልገን ስናገኘው ደስታችን እጥፍ ድርብ ይሆናል ሕይወታችንም በስኬት ይሞላል።

…ሄርድስም “ሂዱና ሕፃኑን ፈልጉ እኔም ደግሞ ሄጄ እንድሰግድለት እንዳገኛችሁት ወደ እኔ ተመልሳችሁ የት እንዳለ ንገሩኝ” ብሎዋቸው ነበር ለጠቢባኑ …ሊሰግድለት ሳይሆን ሕፃኑን ኢየሱስን ለምግደል ፈልጎ እንጂ….ጥቢባኑ ግን ሕፃኑን ኢየሱስ ካገኙና ሰግደው ስጦታቸውን ካቀረቡለት ቡኋላ መንገዳቸውን ቀይረው ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ሁሉ እኛም ኢየሱስን በሕይወታችን ካገኘነው ቡኋል የቅድሞ የሕየወት መንገዳችንን በመቀየር እግዚአብሔር በሚፈልገው ጎዳና ላይ ቢቻ ልንመላለስ ያስፈልጋል።

ስለዚህ የተወደዳችሁ ወዳጆቼ ኢየሱስን ለማግኘት የሚደረገው ሙከራ አድካሚና አሰልቺ ቢመስልም ተስፋ ሳንቆርጥ ታላቅ መስዋትነት ከፍለን ስናገኘው ግን ድስታችን ከፍ ያለ በመሆኑ ዘወትር ተስፋ ባለምቁረጥ እርሱን በቤታችን፣ በሕይወታንች በኑራችን ሁሉ ብናስቀድም ከፍተኛ የሆነ የሕይወት እርካታ እናገኛለን።

የሰማነውን የእግዚአብሔር ቃል በተግባር በሕይውታችህን እንድንተገብረው እርዚአብሔር ሁላችንንም ይርዳን።

አሜን

 








All the contents on this site are copyrighted ©.