2016-01-08 15:29:00

በዓለ ልደት በባግዳድ


በባግዳድ የሚገኘው ማኅበረ ክርስቲያን በዓለ ልደት ሰላምና ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር በጋራ የውይይት መንፈስ ሥር እንዳከበረው በኢራቅ የከለዳዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልዊስ ራፋኤል ሳኮ ማሳወቃቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የተገባው የምህረት ዓመት እንዲሁም በዚሁ መንፈስ የተከበረው በዓለ ልደት በእውነቱ ማኅበረ ክርስቲያን በኢራቅ ሰላም እንዲሁም በተለያዩት በሁሉም ሃይማኖቶች ሰላማዊ የጋራ ኑሮ እንዲረጋገጥ የሚደገፍ ተጨባጭ ተግባር የጐላበት ነበር ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ አያይዘው፦ በበዓለ ልደት ምክንያት በጠቅላላ በኢራቅ በሚገኙት ሰላሳ የከለዳዊ ሥርዓት በሚከተሉት የካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን እንዲሁም በሌሎች 35 የከለዳዊ ሥርዓት በሚከተሉት ተናንሽ ቁምስናዎች በዓለ ልደት በደመቀ ሁኔታ መከበሩ ገልጠው፣ እ.ኤ.አ. የተገባው 2016 ዓ.ም. ምንም’ኳ በአገሪቱ ያለው ውጥረት እልባት ያላገኘ ቢመስልም ቅሉ የሰላም ዓመት እንዲሆን መመኘታቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በዓለ ልደት ላከበረው የኢራቅ ማኅበረ ክርስቲያን ከሙስሊም የአገሪቱ ዜጋ ከምስልምና ሃይማኖት የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች ጭምር የመልካም በዓል ምኞች መግለጫ መልእክት የደረሰው ሲሆን በዚህ ብቻ ሳይገታም ብዙ የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በበዓለ ልደት ሌሊት ባረገው መስዋዕተ ቅዳሴ በእንግድነት መሳተፋቸው ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ የሰጡት መግለጫ የጠቀሰው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ፦ ሕዝቡ የተጠማው ሰላም ነው በመሆኑም የፖሊቲካ አካላት ያስተላለፉት የመልካም በዓለ ልደት የመግለጫ መልእክትና እንዲሁም ያቀረቡት ገጸ ማኅበረ ክርስቲያን ምስጋና በማቅረብ የመልካም በዓል ልደት ምኞች መግለጫ መልእክት መሆን የሚገባው ሰላም ለተጠማው የኢራቅ ሕዝብ ወደ ሰላም የሚሸኝ ተግባር ነው ሲል ምላሽ ሰጥቶበታል።

ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ በበዓለ ልደት ምክንያት ባስተላለፉት ሐዋርያዊ መልእክት የኢራቅ ሕዝብ ላደጋ እያጋለጠ ያለው ተግባር ሁሉ በማውገዝ ከ 2014 ዓ.ም. ወዲህ ገዛ እራሱ እስላማዊ አገር በማለት የሰየመው የምስልምና ሃይማኖት አክራሪው ታጣቂ ኃይል ከሚቆጣጠረው ክልል ንብረቱንና ቤቱን ጥሎ የተሰደደው የተፈናቀለው ማኅበረ ክርስቲያን የሌሎች ሃይማኖት ተከታዮችን በማስታወስ የኢራቅ ሁኔታ ሁሉም የአገሪቱ ዜጋ በሰላም ለመኖር የሚችልበት የሁሉም ኢራቃዊ ዜጋ አገር ግንባታ በዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድጋፍ አማካኝነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም ስለ ኢራቅ ሰላም የሚደረገው ጥረት የቃል ሳይሆን ተግባራዊ  እንዲሆን አደራ ማለታቸው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በተከበረው በዓለ ልደትና በተገባው የምኅረት ዓመት ምክንያት የኢራቅ ማኅበረ ክርስቲያን አለ ምንም የሃይማኖት ልዩነት ስለ ሁሉም ድኻው የኢራቅ ክፍለ ማሕበረሰብ ድጋፍ እንዲውል ታልሞ የተለያየ እርዳታ በማሰባሰብና ድኻው የኢራቅ ዘጋ እንዳይረሳ የተለያዩ የድጋፍና የትብብር ዘመቻ ጭምር ማካሄዳቸው ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ ገልጠው፣ እምነት በቃልና በተገባር እንዲኖርና ሃይማኖት ለሰላም እንጂ ለግጭትና ለጦርነት ምክንያት ሊሆን አይችልም እንዳሉ ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግልት ያመለክታል።

በኪርኩክ የከልዳዊ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከተፈናቀሉት ቤተሰብ ለተወጣጡት 380 ተማሪዎች በተመያየ መስክ ድጋፍ እያቀረበ ሲሆን በኢራቅ በተለያየ መጠለያ ሰፈር በበዓለ ልደት ምክንያት ተፈናቃዩ ማኅበረ ክርስቲያን እንዲሁም የሌላው ሃይማኖት አባላት ያሳተፈ መስዋዕተ ቅዳሴ መቅረቡና በሁሉም መጠለያ ሰፈር በኢዮበልዮ የምኅረት ዓመት ምክንያት ቅዱስ በር መከፈቱም ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት የብፁዕ ካርዲናል ሳኮ ሐዋርያዊ መልእክት ጠቅሶ ሲያመለክት፣ በኢራቅ ለሚገኘው ተፈናቃይ ሕዝብ ከቅድስት መንበር ሰብአዊና መንፈሳዊ ድጋፍ እየቀረበም መሆኑ አስታውቀዋል።

በበዓለ ልደት ምክንያት ብፁዕ ካርዲናል ሳኮ በመሩት መስዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት የምኅረት ዓመት በቃልና በሕይወት በዚያ የጦርነት አመክንዮ በሚቃወም በተጫባጭ የተስፋ ምልከት እንዲኖር አደራ እንዳሉ የገለጠው ኤሺያን ኔውስ የዜና አገልግሎት አክሎ የሃይማኖት አክራሪነት ተወግዶ ሁሉም ሃይማኖቶች በሰላም ለመኖር የሚያስችለው መንፈስ በመመስከር በጋራ የሰላም መሣሪያ ሆነው እንዲገኙም ጥሪ ማቅረባቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.